September 21, 2020
18 mins read

አብይ አህመድ ከጌታቸው አሰፋ በምን ይሻላል? – ሰርፀ ደስታ

ዛሬ የአብይ አበበ ገላው ይዞት ነበር የተባለው የአብይ አህመድ ኢነሳ ውስጥ በነበረበት ጊዜ ምን ሲሰራ እንደነበር የሚጠቁመው መረጃ በብዙ ቦታ ተሰራጭቶ አየሁት፡፡ እኔን የገረመኝ ግን የአብይ ቲፎዞዎች አይናቸውን በጨው ታጥበው ሚስጢር ሲባል የነበረው ይሄ ነው ወይ አይነት ትችታቸውን እያዥጎደጎዱት በማየቴና ሕዝቡ ስለተባለው ነገር በደንብ ከማስተዋል ይልቅ በእነሱ ውዥንብር አብይን ጻድቅ እንዲያደርግ ያደረጉት ጫጫታ ነው፡፡ አበበ ቶላ የተባለ አብይ የሚደግፈው ቲፎዞ ኤርሚያስ ለገሰ ተዋረደ በሚል ርዕስ በስነሥርዓት ስለአብይ የተባለውን እውነት ለማስቀየስ የሄደባቸውን አካሂዶች ታዝቤ ስመለስ ጭራሽ በትልቁ ሙሴ ብቻ አይደለም አብይ ኖህ ነው ላገር የሚል ሌላ ዘመቻ ታዘብኩ፡፡ አስተውሉ እንግዲህ፡፡ እንዲህ የሚሉን አብይ አህመድ በእርግጥስ ማን ነው? የሚለውን ለመመለስ ያጣንው መረጃ ሳይሆን የለየለትን ወሮበላ አረመኔና የሕዝብ ጠላት ጭራሽ ከእነ ኖህ ጋር ሲመስሉት ፈዘን እነሱኑመ መስማታችን ነው፡፡

እውነታው አብይ አህመድ ከጌታቸው አሰፋ በምን ይለያል ብሎ መጠየቅ ነበር? ብዙ ኢትዮጵያውያን የታረዱትና ብዙ መከራ የደረሰባቸው በአብይ አህመድ ለወያኔ ተቀጥሮ ኢንሳ በተባለው የአሸባሪዎች መረብ በሚሰራበት መሆኑን ነው መረጃው በግልጽ የነገረን፡፡ ይሄን እውነት ነው በማሳከር ሌላ ገጽ ሊያላብሱት የሚሞክሩት፡፡ አብይ አህመድ በወያኔ እንዳደገና ዛሬም ድረስ የወያኔ ታማኝ መሆኑን ጭምር ነው የሚነግረን መረጃው፡፡ አብይ አህመድ ከጌታቸው አሰፋ ያነሰ ወንጀል በከፋ ወንል እንደሌለበት አደለም፡፡ ጌታቸው እንደ አብይ ማስመሰል ስላልቻለና ፊት ለፊት ላይ ስለታይ ነው፡፡  አበበ ቶላ የተባለው የአብይ ቅጥር ቲፎዞ ኤርሚያስ ለገሰን ተዋረደ ባለበት የቲፎዛዊ ሥራው አብይ ሥራውን ነው የሠራው ይለናል፡፡ አዎ ማንም ሥራውን አልሰራም አላለም፡፡ አው ሥራው ለወያኔ ያልተባበሩትን ማጥመድና ለሞትና ለሥቃይ መስጠት ነበር፡፡ ይሄን በሚገባ ተወጥቷል፡፡ ቀጣሪዎቹንም በሚገባ አስደስቷል፡፡ ለዚህ ውለታው ቀጣሪዎቹም ብዙ ከፍለውታል፡፡ የለቦታው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ሌሎችንም ቦታዎች ሰጥተውታል፡፡ አብይ የታላላቅ ኢንጂነሮችን እውቀት ለሴራው በመጠቀም ለወያኔ ትልቅ ባለውለታ ሆኗል፡፡  ይህ መረጃ የሚነግረን ይሄን ነው፡፡ እሺ አብይ ሥራውን ነው የሰራው ብለን የምንቀበልለት ከሆነ ጌታቸው አሰፋስ ከተሰጠው ሥራ ውጭ ምን ሠራ? የሚገርመኝ ነገር ቢኖር እንዴት የፈጠጠን እውነት ሊያስቀይሱ እንደሚዘምቱ ሳይ ነው፡፡

አብይ አህመድ እንዲህ አልጋ በአልጋ የሆነለት ለወያኔ በመታመኑ ወይስ በችሎታው፡፡ ከማንምና ከምንም በላይ ታማኝ አገልጋያቸው እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ ዛሬም ቢሆን የምናየው እውነት ይሄን ነው፡፡ ሰሞኑን ገንዘብ ቀየርኩ ብሎ ወያኔን አሽመደመድኳት አይነት ቀረረቶ ለቆልናል፡፡ አዝናለሁ፡፡ ወያኔ የዘረፈቸውን ያተመችውንም ሁሉ ወደ ዶላር ቀይራ ዝግጁ ነች፡፡ ወያኔ ብቻም ሳይሆን ራሱን አብይን ጨምሮ ሥልጣኑን ዛሬም በቁማር የተቀመጡበት ሁሉ፡፡ ከዚህ በኋላ የሚከስር ካለ ምን አልባት ከእነ አብይ ቡድን ያልሆነ ይሄ ግባ የማይባል ገንዘብ በእጁ የተገኘ ሊሆን እንደሚችል እንታዘባለን፡፡ አብይ አህመድ ልጆቹንና ሚስቱን ከወደ አሜሪካ ያመጣው አሁን የያዘው ሥልጣን ላይ ሲቀመጥ ነው፡፡ ለመሆኑ የትኛው ኢትዮጵያዊ ሐብታም ነው ሚስቱንና ልጆቹን አሜሪካን አገር አስቀምጦ በፈለገ ጊዜ ከኢትዮጵያ አሜሪካ እየተመላለሰ ሲኖር የነበረ? ግልጽ ነበር፡፡ ሚስኪኖች ለሥራ እንኳን  ወደ ውጭ ሲሄዱ ሥንት የደህንነት ግልምጫ አልፈው ነው፡፡ ይሄ ግለሰብ ነው እንግዲህ ዛሬ በወያኔ ቦታ ተተካሁ እያለ የሚቆምርብን፡፡

አብይ አህመድና ወያኔ በደንብ ይግባባሉ፡፡ የማይገባን እኛ ነን፡፡ ዛሬ እያደረገ ያለው ከወያኔ የተማራትን አንድ በአንድ ነው፡፡ የኢትዮጵያን የመንግስ መዋቅሮች በፍጥነት በጴንጤ ኦሮሞዎች ካልሆነ ደግሞ ቢያንስ በኦሮሞ ሲያሲዝ ሁሉም ፈዞ ጭራሽ አብይ አብይ እያለ ሲዘፍንለት ነበር፡፡ የኢትዮጵያን ንግድ ባንክ በጴንጤ ኦሮሞነት መስፈርት ብቻ እንዲመራ ሲያደርግ ኧረ ይሄ ነገር ጥሩ አደለም ስንል የሚገርመው ማንም ሰው ትኩረት የሰጠው አልመሰለኝም፡፡ አዝናለሁ፡፡ ባንኩ  ከገንዘብ ኪሳራ በላይ ዛሬ በየቦታው ለሚከሰቱ አረመኔያዊ ጭፍጨፋዎች ዋና የገንዘብ መተላለፊያ እንደሆነ እንታዘባለን፡፡ በዘረፋ ሥምም ብዙ ገንዘብ ሆን ተብሎ ለገዳዮች ተላልፏል፡፡  ይሄን ያደረገው ጌታቸው አሰፋ ሳይሆን አብይ አህመድ ነው፡፡ ይሄን ሁሉ ዘረፋና ወንጀል ሲያንቀሳቅስ የነበረውን የባንኩን ሹመኛ አሁን አምባሳደር አድርጎ ሾሞታል፡፡ አሁን ባንኩን የሚመራው ግለሰብም የተመረጠው ከአደገኛው ከኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ና፡፡ በግል አቤ ሳኖ (የአሁኑ የባንኩ ሥራአስኪያጅ) የችሎታ ችግር ያለበት አይመስኝም፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክንም ለመምራት ከዚህም በፊት ተሹሞ ነበርና፡፡ ችግሩ ያለው ከባንኩሰ የውስጥ ሰዎች ለአብይ የሚታመን በመጥፋቱ ከኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ የመመደቡ ነገር ነው፡፡ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ የፀረ-ኢትዮጵያ እንቅስቃሴ ደጋፊዎች ባንክ እንደሆነ እኔ አውቃለሁ፡፡ ይህ ባን በኢትዮጵያ ትክክለኛ መንግስትና ሕግ ቢኖር ሊኖር የማይገባው ባንክ ነው፡፡ የአሁን ስራ አስኪያጅ የዚህን ባንክ ከመሠረቱት አንዱ ነው፡፡ ያም ባይሆን እንኳ በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ይሄ ግለሰብ ሼር ስላለው ተፎካካሪውን የኢትዮጵያን ንግድ ባንክ ለመምራት በየትኛውም መስፈረት ባልተመረጠም ነበር፡፡ ሆኖም የአብይ አህመድ ሴራ ኢትዮጵያን የመጣል ስለሆነ ይሄ የተፈለገውም እንደዛ እንዲሆን ነው፡፡

ሌላው አሁን ወጣ ሚስጢር ነው ከተባለው መረጃ ጋር በተያያዘ ኤርሚያስ ለገሰ ላይ ትልቅ ዘመቻ ተከፍቶ አየሁ፡፡ ኤርሚያስ ድሮ የተናገረው ነግር ሳይሆን ሰሞኑን የሆነ ነገር ሳይናገር አይቀርም መሰለኝ፡፡ ለእኔ አብይ አህመድና ኤርሚያስ አንድ ናቸው፡፡ ኤርሚያስም የወያኔ ቅጥረኛና ብዙ ወጣቶችንም ሲያጠምድ ከነበሩት እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡ ችግሩ ምን አዚም እንደሆነብን አላውቅም የምናውቀውን የፈጠጠ እውነት በሆነ በሆነ ነገር ሲቀባቡልን ጻድቅ እናደርጋቸዋለን እንጂ፡፡ የሆነ ሆኖ ይሄን መረጃ ተከትሎ በኤርሚያስ ላይ የተከፈተው ዘመቻ ያቺ ኤርሚያስ አበበ ገላው ጋር መረጃ አለ ካላት ንግግሩ ጋር ሳይሆን ከሌላ ሰሞኑን አብይን ከከነከነችው ነገር ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ገመትሁ፡፡ በመጀመሪያ ኤርሚያስ አበበ ጋር መረጃ አለ ያለው በትክክለም መረጃው እንዳለ ይሄው አየን፡፡ መረጃው አብይን ጻድቅ አደረገው የሚሉት የአብይ የኮንፊውዥን ሠራዊት በአለ በሌላ አቅማቸው መረጃውን ለማሳከር እየሞከሩ ቢሆንም መረጃው በግልጽ የሚነግረን ግን ለብዙዎች ሞትና መከራ አብይ አህመድ ዋና እንደነበር ነው፡፡ ምን አልባትም ከጌታቸው አሰፋ በከፋ፡፡ በዚህ መረጃ የ1997 ምርጫን ተከትሎ አሳምነው ጽጌንና ሌሎች ሰዎች በመፈንቅለ መንግስት ሥም እንዲታሰሩና እንዲሰቃዩ አብይ ጠቋሚ ነበር ሲባል የነበረው እውነት ግልጽ ሆኖ ነው፡፡ በ1997 ለብዙዎች ዜጎች መታሰር፣ መሰቃየትና ሞት ዋናው አብይ እንደነበርም ነው፡፡ በዚህ መረጃ አምባቸው የሚል ሥምም ተጠቀሷል፡፡ ሌላው በዚህ መረጃ የታዘብኩት ከብዙ ትግሬዎች ይልቅ በገንዘብ የተገዙ ኦሮሞዎች ለወያኔ ታማኝ መሆናቸውን ጭምር ነው፡፡ አብይ አህመድ ከእነዚህ ታማኝ ቅጥረኛ ኦሮሞዎች አንዱ ነበር፡፡ በአንጻሩ ወያኔ ብዙ ትግሬዎችን ከማንም በላይ እንደጠላት አጥምዳቸው እንደነበር ነው፡፡ አማራ ግልጽ ነበር፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የታዘብኩት የኦሮሞ ቅጥረኞች ከሕዝባቸው ይልቅ ለቀጣሪዎቻቸው እጅግ ታማኝ እንደሆኑ ጭምር ነው፡፡ የሚገርመኝ ነገር ይሄ ነው፡፡ እነ በቀለ ገርባ ለካ አስረዋቸው የነበሩትን ወያኔን መቀለ ድረስ ሄደው የመሳለማቸው ሚስጢር ይሄው ነበር፡፡ አሳፋሪ ነው፡፡ ኦሮሞ ምሁር አላጣም፣ ጀግናም አላጣም፣ ግን ዛሬ ቦታውን ሁሉ ቀድመው የያዙት በወያኔ ቅኝት የተቃኙ ቅጥረኞች እንደሆኑ እንታዘባለን፡፡ ከጅምሩ ጀምሮ ለወያኔ ጉልበቷ የኦሮሞ እንዲሆን ዋና ሚና የነበራቸው የኦሮሞ ፖለቲከኛ ነን የሚሉ የወያኔ ቅጥረኞች እንደሆኑ አገምት ነበር፡፡ ሐጫሉ ከእነዚህ የቅጥረኛ አስተሳሰብ በማፈንገጡ ኢላማ እንደሆነም እታዘባለሁ፡፡ አዝናለሁ፡፡

ሌላው ጀዋር በሽብር  ወንጀል ተከሰሰ ተብሎ ታላላቅ ሚዲያዎች በሰፊው አናፍሰውታል፡፡ እነዚህ ሚዲያዎች ያ ሁሉ ሰው ሲገደል ምንም አላሉም፡፡ ዓላማቸው ምን እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ጀዋር መሐመድ በግልፅ አሸባሪ እንደሆነ ብዙ መረጃዎች አሉ፡፡ ደግነቱ የመንግስታት ባለስልጣናትን ጨምሮ አሁን የዚህ ግለሰብ መረጃ ደርሷቸዋል፡፡ እድሜ ለኢትዮጵያውያን፡፡ እነኢሳትማ ምንም ያልሆነን ወሮበላ አግዝፈው እዚህ አድርሰውታል፡፡ አበበ ገላውንም ሚስጢር ብሎ ለአብይ በያዘለት መረጃ ታዝቤዋለሁ፡፡ አበበ ገላው ጀዋርን ትልቅ ቦታ ከሰጡት አንዱ ነው፡፡ የጀዋርን የዊኪፒዲያ ፕሮፋይል ላይ በሰታንፎርድና ኮሎምቢያ የተማረ ይላል፡፡ ይሄ ግለሰ በሰታንደፎርድ እንደነበረ ምስክር የሆነውም አበበ ገላው ነው፡፡ ቀልደኞቹ ሰታን ፎርድ ምን ይሰሩ እንደነበር እንጃ፡፡ እርግጥ ነው የሆነ ኮርስ መውሰድ ይችሉ ይሆናል፡፡ ከሰታን ፎርድ የተመረቁበትን የሚያሳይ ምልክት ግን የለም፡፡ ቢያንስ የፖለቲካል ሳይንስ ዲፓርተምነት አልሙናይ እንዳልሆኑ ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡  የሆነ ሆኖ የፈለጋቸውን መሆን ይችላሉ፡፡ ግን በአጭበረበሩት ዲግሪያቸው እንደገና ለሕዝብና አገር ሽብር  ሊያውሉት አይገባም፡፡ጸጋዬ አራርሳ የተባለው ግለሰብ እንዲሁ ነው፡፡ ያስ ፕሮፌሰር የተባለው ግለሰብ ቢሆን፡፡ እርግጥ ነው እኔ የአሜሪካ ፕሮፌሰርነት ግራ እያጋባኝ ነው፡፡ ክላስ ገብቶ የሆነ ኮርስ ስለሰጠ ፕሮፌሰር ተብሎ መጠራት እንደሚችል ነው የታዘብኩት፡፡ ፕሮፌሰርነት በትምህርት ዘርፍ በሰሩት የምርምርና የማስተማር አገልግሎት የሚሰጥ ማዕረግ ነው፡፡ እነ ሕዝቅኤል የተባሉት ግለሰቦች ግን የትኛውን ምርምር እንደሰሩ ምንም ምልክት የለም፡፡ ፕሮፌሰርነት እንዲህ ከሆነማ አንዳንዶች የት በደረሱ ነበር፡፡ የሆነ ሆኖ ያ የራሳቸው ጉዳይ ነው፡፡ ግን የኦሮሞ ምሁር ነን የሚሉ ፖለቲከኞች ቅጥረኞች እንጂ ምሁራን አደሉም፡፡ ይሄ ሙያና ዕውቀት የማይጠይቀውን የአክቲቪስትና የሽብርተኛ ፖለቲካንም የመቀላቀላቸው መሠረታዊ ምክነያቱ በእውቀትና ችሎታ ተወዳዳሪ ስላልሆኑ በትክክለኛው የአካዳሚክ ቦታዎች ቦታ ስለሌላቸው ነው፡፡  ይሄን ስል ከላይ እንዳልኩት ነው ኦሮሞ ምሁርም፣ ጀግናም አጥቶ አልነበረም፡፡ ወሮበላ ቅጥረኞች ቀድመው ቦታዎችን መቆጣጠራቸው እንጂ፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን! አሜን!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop