አብይ አህመድ ከጌታቸው አሰፋ በምን ይሻላል? – ሰርፀ ደስታ

ዛሬ የአብይ አበበ ገላው ይዞት ነበር የተባለው የአብይ አህመድ ኢነሳ ውስጥ በነበረበት ጊዜ ምን ሲሰራ እንደነበር የሚጠቁመው መረጃ በብዙ ቦታ ተሰራጭቶ አየሁት፡፡ እኔን የገረመኝ ግን የአብይ ቲፎዞዎች አይናቸውን በጨው ታጥበው ሚስጢር ሲባል የነበረው ይሄ ነው ወይ አይነት ትችታቸውን እያዥጎደጎዱት በማየቴና ሕዝቡ ስለተባለው ነገር በደንብ ከማስተዋል ይልቅ በእነሱ ውዥንብር አብይን ጻድቅ እንዲያደርግ ያደረጉት ጫጫታ ነው፡፡ አበበ ቶላ የተባለ አብይ የሚደግፈው ቲፎዞ ኤርሚያስ ለገሰ ተዋረደ በሚል ርዕስ በስነሥርዓት ስለአብይ የተባለውን እውነት ለማስቀየስ የሄደባቸውን አካሂዶች ታዝቤ ስመለስ ጭራሽ በትልቁ ሙሴ ብቻ አይደለም አብይ ኖህ ነው ላገር የሚል ሌላ ዘመቻ ታዘብኩ፡፡ አስተውሉ እንግዲህ፡፡ እንዲህ የሚሉን አብይ አህመድ በእርግጥስ ማን ነው? የሚለውን ለመመለስ ያጣንው መረጃ ሳይሆን የለየለትን ወሮበላ አረመኔና የሕዝብ ጠላት ጭራሽ ከእነ ኖህ ጋር ሲመስሉት ፈዘን እነሱኑመ መስማታችን ነው፡፡

እውነታው አብይ አህመድ ከጌታቸው አሰፋ በምን ይለያል ብሎ መጠየቅ ነበር? ብዙ ኢትዮጵያውያን የታረዱትና ብዙ መከራ የደረሰባቸው በአብይ አህመድ ለወያኔ ተቀጥሮ ኢንሳ በተባለው የአሸባሪዎች መረብ በሚሰራበት መሆኑን ነው መረጃው በግልጽ የነገረን፡፡ ይሄን እውነት ነው በማሳከር ሌላ ገጽ ሊያላብሱት የሚሞክሩት፡፡ አብይ አህመድ በወያኔ እንዳደገና ዛሬም ድረስ የወያኔ ታማኝ መሆኑን ጭምር ነው የሚነግረን መረጃው፡፡ አብይ አህመድ ከጌታቸው አሰፋ ያነሰ ወንጀል በከፋ ወንል እንደሌለበት አደለም፡፡ ጌታቸው እንደ አብይ ማስመሰል ስላልቻለና ፊት ለፊት ላይ ስለታይ ነው፡፡  አበበ ቶላ የተባለው የአብይ ቅጥር ቲፎዞ ኤርሚያስ ለገሰን ተዋረደ ባለበት የቲፎዛዊ ሥራው አብይ ሥራውን ነው የሠራው ይለናል፡፡ አዎ ማንም ሥራውን አልሰራም አላለም፡፡ አው ሥራው ለወያኔ ያልተባበሩትን ማጥመድና ለሞትና ለሥቃይ መስጠት ነበር፡፡ ይሄን በሚገባ ተወጥቷል፡፡ ቀጣሪዎቹንም በሚገባ አስደስቷል፡፡ ለዚህ ውለታው ቀጣሪዎቹም ብዙ ከፍለውታል፡፡ የለቦታው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ሌሎችንም ቦታዎች ሰጥተውታል፡፡ አብይ የታላላቅ ኢንጂነሮችን እውቀት ለሴራው በመጠቀም ለወያኔ ትልቅ ባለውለታ ሆኗል፡፡  ይህ መረጃ የሚነግረን ይሄን ነው፡፡ እሺ አብይ ሥራውን ነው የሰራው ብለን የምንቀበልለት ከሆነ ጌታቸው አሰፋስ ከተሰጠው ሥራ ውጭ ምን ሠራ? የሚገርመኝ ነገር ቢኖር እንዴት የፈጠጠን እውነት ሊያስቀይሱ እንደሚዘምቱ ሳይ ነው፡፡

አብይ አህመድ እንዲህ አልጋ በአልጋ የሆነለት ለወያኔ በመታመኑ ወይስ በችሎታው፡፡ ከማንምና ከምንም በላይ ታማኝ አገልጋያቸው እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ ዛሬም ቢሆን የምናየው እውነት ይሄን ነው፡፡ ሰሞኑን ገንዘብ ቀየርኩ ብሎ ወያኔን አሽመደመድኳት አይነት ቀረረቶ ለቆልናል፡፡ አዝናለሁ፡፡ ወያኔ የዘረፈቸውን ያተመችውንም ሁሉ ወደ ዶላር ቀይራ ዝግጁ ነች፡፡ ወያኔ ብቻም ሳይሆን ራሱን አብይን ጨምሮ ሥልጣኑን ዛሬም በቁማር የተቀመጡበት ሁሉ፡፡ ከዚህ በኋላ የሚከስር ካለ ምን አልባት ከእነ አብይ ቡድን ያልሆነ ይሄ ግባ የማይባል ገንዘብ በእጁ የተገኘ ሊሆን እንደሚችል እንታዘባለን፡፡ አብይ አህመድ ልጆቹንና ሚስቱን ከወደ አሜሪካ ያመጣው አሁን የያዘው ሥልጣን ላይ ሲቀመጥ ነው፡፡ ለመሆኑ የትኛው ኢትዮጵያዊ ሐብታም ነው ሚስቱንና ልጆቹን አሜሪካን አገር አስቀምጦ በፈለገ ጊዜ ከኢትዮጵያ አሜሪካ እየተመላለሰ ሲኖር የነበረ? ግልጽ ነበር፡፡ ሚስኪኖች ለሥራ እንኳን  ወደ ውጭ ሲሄዱ ሥንት የደህንነት ግልምጫ አልፈው ነው፡፡ ይሄ ግለሰብ ነው እንግዲህ ዛሬ በወያኔ ቦታ ተተካሁ እያለ የሚቆምርብን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ስለእግራቸው ውጤት (የስንኝ ቋጠሮ ለብሔራዊ ቡድናችን ተጫዋቾች) - ከፋሲል ተካልኝ አደሬ

አብይ አህመድና ወያኔ በደንብ ይግባባሉ፡፡ የማይገባን እኛ ነን፡፡ ዛሬ እያደረገ ያለው ከወያኔ የተማራትን አንድ በአንድ ነው፡፡ የኢትዮጵያን የመንግስ መዋቅሮች በፍጥነት በጴንጤ ኦሮሞዎች ካልሆነ ደግሞ ቢያንስ በኦሮሞ ሲያሲዝ ሁሉም ፈዞ ጭራሽ አብይ አብይ እያለ ሲዘፍንለት ነበር፡፡ የኢትዮጵያን ንግድ ባንክ በጴንጤ ኦሮሞነት መስፈርት ብቻ እንዲመራ ሲያደርግ ኧረ ይሄ ነገር ጥሩ አደለም ስንል የሚገርመው ማንም ሰው ትኩረት የሰጠው አልመሰለኝም፡፡ አዝናለሁ፡፡ ባንኩ  ከገንዘብ ኪሳራ በላይ ዛሬ በየቦታው ለሚከሰቱ አረመኔያዊ ጭፍጨፋዎች ዋና የገንዘብ መተላለፊያ እንደሆነ እንታዘባለን፡፡ በዘረፋ ሥምም ብዙ ገንዘብ ሆን ተብሎ ለገዳዮች ተላልፏል፡፡  ይሄን ያደረገው ጌታቸው አሰፋ ሳይሆን አብይ አህመድ ነው፡፡ ይሄን ሁሉ ዘረፋና ወንጀል ሲያንቀሳቅስ የነበረውን የባንኩን ሹመኛ አሁን አምባሳደር አድርጎ ሾሞታል፡፡ አሁን ባንኩን የሚመራው ግለሰብም የተመረጠው ከአደገኛው ከኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ና፡፡ በግል አቤ ሳኖ (የአሁኑ የባንኩ ሥራአስኪያጅ) የችሎታ ችግር ያለበት አይመስኝም፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክንም ለመምራት ከዚህም በፊት ተሹሞ ነበርና፡፡ ችግሩ ያለው ከባንኩሰ የውስጥ ሰዎች ለአብይ የሚታመን በመጥፋቱ ከኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ የመመደቡ ነገር ነው፡፡ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ የፀረ-ኢትዮጵያ እንቅስቃሴ ደጋፊዎች ባንክ እንደሆነ እኔ አውቃለሁ፡፡ ይህ ባን በኢትዮጵያ ትክክለኛ መንግስትና ሕግ ቢኖር ሊኖር የማይገባው ባንክ ነው፡፡ የአሁን ስራ አስኪያጅ የዚህን ባንክ ከመሠረቱት አንዱ ነው፡፡ ያም ባይሆን እንኳ በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ይሄ ግለሰብ ሼር ስላለው ተፎካካሪውን የኢትዮጵያን ንግድ ባንክ ለመምራት በየትኛውም መስፈረት ባልተመረጠም ነበር፡፡ ሆኖም የአብይ አህመድ ሴራ ኢትዮጵያን የመጣል ስለሆነ ይሄ የተፈለገውም እንደዛ እንዲሆን ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የቅዱስ ፓትርያርኩና የማኅበረ ቅዱሳን ልዩነት ወደ ሃይማኖት አደገ

ሌላው አሁን ወጣ ሚስጢር ነው ከተባለው መረጃ ጋር በተያያዘ ኤርሚያስ ለገሰ ላይ ትልቅ ዘመቻ ተከፍቶ አየሁ፡፡ ኤርሚያስ ድሮ የተናገረው ነግር ሳይሆን ሰሞኑን የሆነ ነገር ሳይናገር አይቀርም መሰለኝ፡፡ ለእኔ አብይ አህመድና ኤርሚያስ አንድ ናቸው፡፡ ኤርሚያስም የወያኔ ቅጥረኛና ብዙ ወጣቶችንም ሲያጠምድ ከነበሩት እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡ ችግሩ ምን አዚም እንደሆነብን አላውቅም የምናውቀውን የፈጠጠ እውነት በሆነ በሆነ ነገር ሲቀባቡልን ጻድቅ እናደርጋቸዋለን እንጂ፡፡ የሆነ ሆኖ ይሄን መረጃ ተከትሎ በኤርሚያስ ላይ የተከፈተው ዘመቻ ያቺ ኤርሚያስ አበበ ገላው ጋር መረጃ አለ ካላት ንግግሩ ጋር ሳይሆን ከሌላ ሰሞኑን አብይን ከከነከነችው ነገር ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ገመትሁ፡፡ በመጀመሪያ ኤርሚያስ አበበ ጋር መረጃ አለ ያለው በትክክለም መረጃው እንዳለ ይሄው አየን፡፡ መረጃው አብይን ጻድቅ አደረገው የሚሉት የአብይ የኮንፊውዥን ሠራዊት በአለ በሌላ አቅማቸው መረጃውን ለማሳከር እየሞከሩ ቢሆንም መረጃው በግልጽ የሚነግረን ግን ለብዙዎች ሞትና መከራ አብይ አህመድ ዋና እንደነበር ነው፡፡ ምን አልባትም ከጌታቸው አሰፋ በከፋ፡፡ በዚህ መረጃ የ1997 ምርጫን ተከትሎ አሳምነው ጽጌንና ሌሎች ሰዎች በመፈንቅለ መንግስት ሥም እንዲታሰሩና እንዲሰቃዩ አብይ ጠቋሚ ነበር ሲባል የነበረው እውነት ግልጽ ሆኖ ነው፡፡ በ1997 ለብዙዎች ዜጎች መታሰር፣ መሰቃየትና ሞት ዋናው አብይ እንደነበርም ነው፡፡ በዚህ መረጃ አምባቸው የሚል ሥምም ተጠቀሷል፡፡ ሌላው በዚህ መረጃ የታዘብኩት ከብዙ ትግሬዎች ይልቅ በገንዘብ የተገዙ ኦሮሞዎች ለወያኔ ታማኝ መሆናቸውን ጭምር ነው፡፡ አብይ አህመድ ከእነዚህ ታማኝ ቅጥረኛ ኦሮሞዎች አንዱ ነበር፡፡ በአንጻሩ ወያኔ ብዙ ትግሬዎችን ከማንም በላይ እንደጠላት አጥምዳቸው እንደነበር ነው፡፡ አማራ ግልጽ ነበር፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የታዘብኩት የኦሮሞ ቅጥረኞች ከሕዝባቸው ይልቅ ለቀጣሪዎቻቸው እጅግ ታማኝ እንደሆኑ ጭምር ነው፡፡ የሚገርመኝ ነገር ይሄ ነው፡፡ እነ በቀለ ገርባ ለካ አስረዋቸው የነበሩትን ወያኔን መቀለ ድረስ ሄደው የመሳለማቸው ሚስጢር ይሄው ነበር፡፡ አሳፋሪ ነው፡፡ ኦሮሞ ምሁር አላጣም፣ ጀግናም አላጣም፣ ግን ዛሬ ቦታውን ሁሉ ቀድመው የያዙት በወያኔ ቅኝት የተቃኙ ቅጥረኞች እንደሆኑ እንታዘባለን፡፡ ከጅምሩ ጀምሮ ለወያኔ ጉልበቷ የኦሮሞ እንዲሆን ዋና ሚና የነበራቸው የኦሮሞ ፖለቲከኛ ነን የሚሉ የወያኔ ቅጥረኞች እንደሆኑ አገምት ነበር፡፡ ሐጫሉ ከእነዚህ የቅጥረኛ አስተሳሰብ በማፈንገጡ ኢላማ እንደሆነም እታዘባለሁ፡፡ አዝናለሁ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዛሬ ምን ማድረግ አለብን ? - 2 ዋና ዋና ጉዳዮች

ሌላው ጀዋር በሽብር  ወንጀል ተከሰሰ ተብሎ ታላላቅ ሚዲያዎች በሰፊው አናፍሰውታል፡፡ እነዚህ ሚዲያዎች ያ ሁሉ ሰው ሲገደል ምንም አላሉም፡፡ ዓላማቸው ምን እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ጀዋር መሐመድ በግልፅ አሸባሪ እንደሆነ ብዙ መረጃዎች አሉ፡፡ ደግነቱ የመንግስታት ባለስልጣናትን ጨምሮ አሁን የዚህ ግለሰብ መረጃ ደርሷቸዋል፡፡ እድሜ ለኢትዮጵያውያን፡፡ እነኢሳትማ ምንም ያልሆነን ወሮበላ አግዝፈው እዚህ አድርሰውታል፡፡ አበበ ገላውንም ሚስጢር ብሎ ለአብይ በያዘለት መረጃ ታዝቤዋለሁ፡፡ አበበ ገላው ጀዋርን ትልቅ ቦታ ከሰጡት አንዱ ነው፡፡ የጀዋርን የዊኪፒዲያ ፕሮፋይል ላይ በሰታንፎርድና ኮሎምቢያ የተማረ ይላል፡፡ ይሄ ግለሰ በሰታንደፎርድ እንደነበረ ምስክር የሆነውም አበበ ገላው ነው፡፡ ቀልደኞቹ ሰታን ፎርድ ምን ይሰሩ እንደነበር እንጃ፡፡ እርግጥ ነው የሆነ ኮርስ መውሰድ ይችሉ ይሆናል፡፡ ከሰታን ፎርድ የተመረቁበትን የሚያሳይ ምልክት ግን የለም፡፡ ቢያንስ የፖለቲካል ሳይንስ ዲፓርተምነት አልሙናይ እንዳልሆኑ ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡  የሆነ ሆኖ የፈለጋቸውን መሆን ይችላሉ፡፡ ግን በአጭበረበሩት ዲግሪያቸው እንደገና ለሕዝብና አገር ሽብር  ሊያውሉት አይገባም፡፡ጸጋዬ አራርሳ የተባለው ግለሰብ እንዲሁ ነው፡፡ ያስ ፕሮፌሰር የተባለው ግለሰብ ቢሆን፡፡ እርግጥ ነው እኔ የአሜሪካ ፕሮፌሰርነት ግራ እያጋባኝ ነው፡፡ ክላስ ገብቶ የሆነ ኮርስ ስለሰጠ ፕሮፌሰር ተብሎ መጠራት እንደሚችል ነው የታዘብኩት፡፡ ፕሮፌሰርነት በትምህርት ዘርፍ በሰሩት የምርምርና የማስተማር አገልግሎት የሚሰጥ ማዕረግ ነው፡፡ እነ ሕዝቅኤል የተባሉት ግለሰቦች ግን የትኛውን ምርምር እንደሰሩ ምንም ምልክት የለም፡፡ ፕሮፌሰርነት እንዲህ ከሆነማ አንዳንዶች የት በደረሱ ነበር፡፡ የሆነ ሆኖ ያ የራሳቸው ጉዳይ ነው፡፡ ግን የኦሮሞ ምሁር ነን የሚሉ ፖለቲከኞች ቅጥረኞች እንጂ ምሁራን አደሉም፡፡ ይሄ ሙያና ዕውቀት የማይጠይቀውን የአክቲቪስትና የሽብርተኛ ፖለቲካንም የመቀላቀላቸው መሠረታዊ ምክነያቱ በእውቀትና ችሎታ ተወዳዳሪ ስላልሆኑ በትክክለኛው የአካዳሚክ ቦታዎች ቦታ ስለሌላቸው ነው፡፡  ይሄን ስል ከላይ እንዳልኩት ነው ኦሮሞ ምሁርም፣ ጀግናም አጥቶ አልነበረም፡፡ ወሮበላ ቅጥረኞች ቀድመው ቦታዎችን መቆጣጠራቸው እንጂ፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን! አሜን!

 

4 Comments

 1. ጁዋር መሀመድ ከቋንቋ አጠቃቀሙና ከሀሳብ ጥራቱ አንጻር ሲታይ የhigh school ዲፕሎማ ሊኖረው ይችላል ህዝቅኤል ጋቢሳ በዚህ የዘረኝነት ትብታብ ተተብትቦ ነው መሰለኝ ምንም የጻፈው ያስመዘገበው አርቲክል የለም እርሱ የሚኮራበት ጽሁፉ ስለ ጫት የጻፋት ነች የታሪክ ምሁርነቱ ስለ ጫት ታሪክ መሆኑ ነው ማለት ነው እዚህ ላይ ፕሮፌሰሩ የተስፋዬ ገ/አብ አድናቂ ከመሆኑ አልፎ ተከታዩም ሁናል። እንግዲህ እነዚህ ግለሰቦች የአካዳሚክስ ጉልበት በማጣታቸው ተሰሚነት ልናገኝ የምንችለው በዚህ መንገድ ነው ብለው ስለገመቱ ህዝብን ቁም ስቅል ያሳዩታል ለዚህ ስራቸውም ከግብጽና ከወጣቶች በተዋጣ ገንዘብ ኑሯቸውን ይገፋሉ።

 2. As the writer of this comment (Desta) did , I have tried to go through what the audio released by Abebe Gelaw and other counter comments that made Ermias Legese their target , more specifically by Abebe Tola (Tokichaw) .
  Well, anyone has the right to say about the very self evidently clear story of what Abyi Ahmed did as the head of an agency (INSA) did do or did not do. But, it is a terribly stupid argument to deny what that Agency was all about . Yes, it is a total idiocy to argue that the head of that Agency had and has nothing to do with the very orchestration of spying on innocent citizens for the simple reason that they were against the bloody ethnocentric political game . It is a very common knowledge that agencies of this kind are used by African oppressive ruling circles including TPLF/EPRDF to silence voices for freedom and justice in the name national security . And there is no doubt that to be the head of these kinds of criminal state machinations is to be part and parcel of the very oppressive and bloody political behavior and practice .
  There is nothing wrong with what Ermias argues because the very Isis we are talking about is self-evidently clear and undeniable at all.

  I do not know how any truly concerned Ethiopian can have any grain of trust on Abyi’s claim that he had done nothing wrong and criminal at all where as he was the head of that machination which helped the criminal ruling circle to hand down innocent citizens ?
  We may try to defend this criminal behavior and act by the Agency led by Abyi Ahmed . But we cannot defeat and kill the very reality that happened on the ground !

 3. Abiy Ahmed not only jammed but hunted down those who wrote the information, until the use of cell phones , social medias made his hunting down and jamming spy work less effective.

  In 2013 Abiy finally reached the conclusion it is easier for him to exterminate all the Amara Orthodox because most of them speak their minds making jamming and hunting just the source of the information was not bringing the desired result as it did in times before cell phones ,social media and internet were available in Ethiopia.

  So Abiy appeased Oromo Querros anyway he can to use them as instrument for his plan to exterminate the Amara Orthodox. He also perpetrated the so called Amara Coup De Tat’ to finish those who he and his bosses call “timkhitegnas”.

 4. በጎበዙና ከበሰለ ጭንቅላቱ በሚወጣው የማስተማር ችሎታውና በማይሽመደመደው አቋሙ የምንወደወ ኤርምያስ ለገሰ ላይ ያነጣጠረው ዝግጅት ፡ቅንጅትና ከንቱ ተንኮል የማን እንደሆነ ለማናችንም ግልጽ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ እነ ስዩም ተሾመ ፡ ከአሜሪካ የተሸጡት እነ ሲሳይ አጌና እና በስም ለጊዜው ያልተጠቀሱ የኢዜማ ጀንፈሎች ጭምር ያሉበት አብይን ለመደገፍ በጥቅማ ጥቅም የተገዙ የሆዳሞች የድምር ውጤት ነው፡፡ መደመር ለጥፋትም ይሰራልኮ፡፡ አበበ ገላውን እንወደዋለን ፡፡ ታሪክ ሰርቷልና፡፡ በአበበ ገላውና በኤርምያስ ለገሰ መካከል ለታዳሚወቻቸው የመበላለጥ ፉክክር አይነት ነገር ሊታይ ይችል ይሆናል፡፡ የፖለቲከኞች ስራና ሴራ ለህዝቡ የሚገባው በእያንዳንዱ ታዳሚ የብሰለት ልክ ነው እኮ፡፡ ስለዚህ አብይም፡ ኤርምያስም፡ አበበ ገላውም በእውነት ለመናገር የአብይ ተከፋዩ ሲሳይ አጌናም ለታማሚዋ ኢትዮጵያ በተለይ በአሁኑ ወቅት ሁላችሁም ታስፈልጓታላችሁና እንወዳችኋለን፡፡ የኔ ምክር ከሁላችሁም ይልቅ አብይ ላይ ጠንከር ይላል፡፡ በውነቱ ወቀሳም ጭምር ነው፡፡ አብይ ለኢትዮጵያ ራእይ ያለህ ሰው ትመስለኛለህ፡፡ የሰራህውን ስህተትም ማረም የጀመርክ ትመስላለህ፡፡ የምን ሁሉ ኬኛና ኦሮሙማ ይቅደም፡ የምን ሌባውን ወያኔን መለማመጥ፡ የምን ጸረ አንድነት ሀይሎችን መታገስ፡፡ ለዚህ ለአሁኑ ውድቀት ያደረሰህ ይህን መሰሉ ስህተቶችህ ናቸው፡፡ አሁንም ስላልመሸብህ በግልህ በቸልተኝነትህ የተደቀኑትን መሰናክሎች በቶሎ ታስተካክላለህ ወይስ በጥቁር መዝገብ ላይ ትጻፋለህ?? በምድር ላይ ከምንም ነገር በላይ ስልጣን ብትወድም የአገሪቱን ሰው ሁሉ ሳታበላልጥ በእኩል አይን በማገለገል አገሪቱ በአንድነቷና በክብሯ በነጻነቷ እንድትቀጥል ካደረግህ እሰየው፡፡ በስልጣን ቀጥል፡፡ ካልሆነ ከላይ የጠቀስኳቸው ሁሉም በሚያምኑበት መንገድ እንድገባህ ለማድረግ በሚያደርጉት ጥረት የሚስተዋልን ሙከራ በተናጠል የአንተ ሰዎች እንዱ በአንዱ ላይ እንድነሳ እያደረጉ ለዚሁም ስራቸው አንተ እየከፈልካቸው ክቀጠለ በመጨረሻ “የፍጻሜው የህዝብ አሸናፊነት” ስለሚሆን እወ ቁት ሰልፋችን ከእነኤርምያስ ጋር ነው፡፡ Ethio 360 የወቅቱ ወንጌላችን ነውና አንተም ብታዳምጠውና አካሄድህን ብታስተካከልበት ገና ብዙ ብዙ ጥሩ ጥሩ ነገሮች ለአገሪቱ እንዲትሰራ ትማርበታለህ፡፡ አትሞኝ፡፡ ይጠቅመሃል፡፡
  ኤርሚ፦ ቦታ አትስጣቸው፡፡ ከቻልክ እርሳቸው፡፡ ወንዝ አይሻገሩምና፡፤ ህዝቤ ያውቃ ቸዋልና፡፡ ፍርድም የህዝብ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share