February 16, 2020
17 mins read

አነጋጋሪው ሰባተኛው ንጉሣችን አቢይ አህመድ ዘብሔረ ኦሮሚያ – ግርማ በላይ

ግርማ በላይ ([email protected]) ዳንሳ

ይህችን ማስታወሻ ልጫጭር ስነሳ በቅድሚያ ስለውሸትና ውሸታሞች ጥቂት ነገር ለመዳሰስ ሞከርኩ፡፡ እንዲህ ያደረግሁት የአቢይ አህመድን ውሸታምነት ለመፈረጅ በመቸገሬ ነው፡፡ በሥነ ልቦናው ዘርፍ እንደሚታወቀው Pathological liar እንዳልለው የአቢይ ውሸት ዓላማና ግብ ያለው በመሆኑ በዚያ ስም መፈረጅ ከበድ አለኝ፡፡ የመዋሸት ሥነ ልቦናዊ ደዌ የተጠናወተው ሰው አለ ተጨባጭ ምክንያት ይዋሻልና ከአቢይ ዓይነቱ ቦጥራቃ ውሸታም ለየት የሚል ይመስለኛል፡፡ የሚመሳሰሉበት አጋጣሚም ሊኖር ይችላል፡፡ አንዳንዴ ተሰሚነትን ወይም ተደማጭነትን ለማግኘትም ሲባል ሰዎች ከሜዳ ተነስተው ያለ በቂ ምክንያት ሊዋሹ ይችላሉ፡፡ “attention seekers” ብዙውን ጊዜ በዚህ ይታማሉ፡፡

በመሠረቱ መዋሸት አንደኛው መጥፎ የሰው ባሕርይ ነው፡፡ መዋሸት ወንጀልም ኃጢኣትም መሆኑን ብናውቅም ለተለያዩ ዓላማዎች የምንዋሽ ሰዎች አለን፡፡ “እኔ በፍጹም አልዋሽም” የሚል ሰው ካለ እርሱ የመጨረሻው ጉረኛ ነው፡፡ ይነስም ይብዛም እንዋሻለን – ለውሸታችን ግን ምክንያት ልንሰጥ እንችላለን፡፡ “ሰውን ከሰው ላለማጣላት፤ ሰውን ለማስታረቅ፣ የሰው ስሜት ላለመጉዳት፣ ሥራየን ላለማጣት፣ ላለመቀጣት፣…” ወዘተ. የመሳሰሉ ሰበቦችን እየሰጠን ለውሸታችን ቅድስና ልንሰጥ ብንዳዳም ውሸት ያው ውሸት ነውና ዞሮ ዞሮ ስንተኛ ስለቀኑ ውሸታችን መጨነቃችን አይቀርም – ኅሊና አለን የምንል ወገኖች ለዚያውም፡፡ ኅሊናቢሶች ግን መተዳደሪያቸው ውሸት ራሱ ነውና ሲዋሹ አድረው ሲዋሹ ቢውሉ ጉዳያቸው አይደለም – እንደ ዶክተር አቢይ ያሉት ቆርጦ ቀጥሎች፡፡ ግን ታድለው!

ስለውሸት ዳሰሳ ሳደርግ አንድ ጠቃሚ ጽሑፍ አገኘሁ፡፡ ይህ ጽሑፍ ውሸትንና ውሸታምነትን በሰባት ቦታ መድቦ እንደሚከተለው ያስቀምጠዋል፡፡ ማን ወደየትኛው እንደሚያዘነብል መርምሩ፡፡

  1. Error—a lie by mistake. The person believes they are being truthful, but what they are saying is not true.
  2. Omission – leaving out relevant information. Easier and least risky. It doesn’t involve inventing any stories. It is passive deception and         less guilt is involved.
  3. Restructuring—distorting the context. Saying something in sarcasm, changing the characters, or altering the scene.
  4. Denial—refusing to acknowledge a truth. The extent of denial can be quite    large— they may be lying only to you just this one time or they     may be lying to themselves.
  5. Minimization—reducing the effects of a mistake, a fault, or a judgment call.
  6. Exaggeration—representing as greater, better, more experienced, more successful.
  7. Fabrication—deliberately inventing a false story.

ሀሰትን መናገር ፈጣሪ አምርሮ ከሚጠየፋቸው ነገሮች ውስጥ አንዱና ዋናው ነው፡፡ ማስረጃችንም አሠርቱ ትዕዛዛት ውስጥ ስምንተኛው ትዕዛዝ “በሀሰት አትመስክር” የሚለው ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ስለሀሰት ንግግር መጥፎነትና ኃጢኣትነት በብዙ ቦታዎች ተጠቅሷል፡፡ እነአቢይና ወንድሙ እስራኤል ዳንሳ ግን ምድባቸው ከሌላ በመሆኑ እውነትን ሲረመርሙና ሀሰትን ሲያነግሡ በዚህ ጠያፍ ተግባራቸው ይኮሩበታል – እንጀራም ይበሉበታል – ቆሻሻ ዝናም ያተርፉበታል እንጂ አያፍሩበትም፡፡ ጊዜው በክርስቶስ ላይ የሚቀለድበት ሆነና የአቢይ ዲቃሎች እነእዩ ጩፋ ሴኔኒዝምን በግልጽ የሚያስፋፉበት ሆነ፡፡

ለወትሮው ሀሰትን የሚናገር ሰው በቀላሉ ይታወቃል፡፡ ከፊት ገጽታው፣ ከሰውነት እንቅስቃሴውና ከአንደበቱ መርበትበት ማወቅ ይቻላል፡፡ እንዲህ የሚሆነው ግን ውሸታሙ ሰው ብዙ የመዋሸት ልምድ ከሌለው ነው፡፡ እንደ አቢይ ዓይነቱ የፍየል ዐይን በጨው ቀቅሎ የበላ ከሆነ ግን ራሱ በገደለው ሬሣ ላይ ቀብር ተገኝቶ ፊቱን በባና ቢነጭ አምኖት አብሮት የሚያለቅስ አያጣም፡፡ በሀገራችን እየሆነ ያለውም ይሄው ነው፡፡ ደግነቱ አሁን አሁን ለመድነው እንጂ አቢይ ሲዋሽ ልናውቅበት የሚያስችለን አንደበታዊም ሆነ ዐይነ ውኃዊ ፍንጭ የነበረን ለመሆናችን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ያገሬ ገበሬ ይህን ዓይነቱን ሰው “ኮኬ!” ይለዋል፡፡ እውነቴን ነው የምለው እኔ ልዋሽ ብል ከንፈሬ ይደርቃል፣ ትናጋየ ይለጎማል በብርድ ቆፈናም ወቅት ሳይቀር ነጭ ላብ ያልበኛል፡፡ ተፈጥሮ ለአንዱ ሌላ ለሌላው ደግሞ ሌላ ናት፡፡ መዋሸትም ቁም ነገር ሆኖ ከአቢይ ለየችኝ – ይቺ በአድልዖ የተመላች የማትረባ ተፈጥሮ! አፈር ደቼ ትብላ፡፡

ለማንኛውም ከአቢይ ውሸቶች መካከል ጥቂቶቹን ለአብነት ያህል ላስታውስና ልሰናበት፡፡

  1. ኢንጂነር ስመኘው ራሱን መግደያ ቦታ አጥቶ መስቀል አደባባይ ላይ ተገድሎ ሲገኝ አቢይ ከውጭ መጥቶ ኢንጂነሩ ራሱን በራሱ እንደገደለ በሚዲያ ተናገረ፡፡ አንድ በሉ፡፡
  2. የተወሰኑ ወታደሮች ወደ ቤተ መንግሥት ሄደው “ፑሻፕ” አሰርቷቸው ሲያሰናብታቸው ለሆነ ጥያቄ እንደመጡ ከተናገረ በኋላ ትንሽ ቆይቶና ሁኔታዎች ሲረጋጉ ለመፈንቅለ መንግሥት እንደተላኩ ተናገረ፡፡ ይህ አይደለም ዋናው ነገር፡፡ በወቅቱ የመፈንቅለ መንግሥቱን ዜና ለሕዝብ ለምን ይፋ እንዳላደረገ ሲጠየቅ እጅግ የሚገርም መልስ ነበር የሰጠው፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ አፍንጫው ሥር የነበርን ሰዎች ምንም ሳንሰማ “የሰላሌና የሸኖ፣ የባሌና የበደኖ ኦሮሞ ፈረስ ጭኖ፣ ጋሻ ወድሮና ጦር ሰብቆ እየመጣ እንዴት ብዬ ሰውን ላስጨርስ ብዬ እምቅ አድርጌ በሆዴ ችዬ ሳልናገር ተውኩት” ብሎ ጥቂት ብልኆችን በሣቅ ገደለ፡፡ ያኔ በወረት ፍቅር ስለነበርን ጉዳዩን ከቁም ነገር ሳንጥፍ አሳለፍነው፡፡ የሚገርም ቲያትረኛ ነው፡፡ ከተሜው ሳይሰማ ገጠሬው መስማቱ አጃኢብ ያሰኛል፡፡ ከዋሹ አይቀር ደ’ሞ እንዲህ ነው፡፡ ሁለት በሉ፡፡
  3. በአንድ ስብሰባ ላይ ስለኦሮሞ ሁሉንም የሀገር ሥልጣን ለብቻ መቆጣጠር ሲጠየቅ “በኔ የሥልጣን ዘመን ኦሮሞ የተለዬ ጥቅም አግኝቶ ከሆነ ሥልጣኔን በ24 ሰዓት እለቃለሁ” በማለት በሕዝብና በሀገር ላይ ተዘባበተ፡፡ ከነደረጀ የበለጠ ኮሜዲያን አይደል? ሦስት በሉ፡፡
  4. አዲስ አበባ አካባቢ የተሾሙ የኦሮሞ ባለሥልጣናት አማራውንና ደቡቡን ከየመኖሪያው እየመነጠሩ ሲያባርሩና ሲያፈናቅሉ አጅሬ አውቆ እንዳላወቀ “አልሰማሁም” አለ፡፡ በቡራዩና በለገጣፎ ጋሞዎችና አማሮች በአክራሪ ኦሮሞዎች ሲያልቁ፣ የአዲስ አበባ መሬት በቄሮዎች እንደልብ ሲዘረፍ፣ ድሆች ከመናኛ ገቢያቸው አጠራቅመው ያሠሩት ኮንዶምንየም በነጃዋር ልጆች በጠራራ ፀሐይ ሲቀማ … በቺንዋ አቼቤ አገላለጽ a man of the people አቢይ አህመድ አሊ “አልሰምቼም” አለ፡፡ ተበዳዮች ወደርሱ ሄደው አቤት ቢሉ “ይህ ጉዳይ ክልሉን እንጂ እኔን አይመለከትም” በማለት አበሻቅጦ አባረራቸው፡፡ የሕዝቡ ሰው መልኩ ሁለት ነው – አንዱ ለታይታ የሚቅለሰለስ ሌላው የክቱ ጊንጣዊ ዐመል፡፡ ለማንኛውም አራት በሉ፡፡
  5. ሰኔ 15/2011 ባህር ዳር ላይ ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ የአማራ ባለሥልጣናትና የፌዴራል ጄኔራሎች ግድያ ከመፈጸሙ በደቂቃዎች ልዩነት በፋቲክ ልብስ ቲቪ ላይ ቀርቦ “በአማራ መንግሥት መፈንቅለ መንግሥት ተካሄደ” በማለት አንጀቱ ለጋ ቅቤ ጠጥቶ በፊት ገጽታው ግን እጅግ ያዘነ በመምሰል ለምቦጩን ጥሎ ዐወጀ፡፡ ኦፕሬሽኑ የተካሄደው በርሱ አመራር መሆኑ አለባበሱና ከመብረቅ የፈጠነ የዕለት እንቅስቃሴው አፍ አውጥቶ ይናገር ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ የሚታየው የአማራው አካባቢ ድንዙዙ እንቅስቃሴም የዚያው ኦፕሬሽን ታሳቢ ውጤት ፤መሆኑ አፍ ቢክደው የማንም ኅሊና አይስተውም፡፡ ራሱ አቅዶ ራሱ ባከናወነው ግድያ ሰበብም ንጹሓን ዜጎች በተለይም ከጉዳዩ ጋር በአጋምም በቀጋም የማይገናኙ የአብን አመራሮችና አባሎች ታስረው እስካሁንም እየተሰቃዩ ነው፡፡ አምስት በሉ፡፡
  6. የታገቱት የአማራ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከእገታው እንደተለቀቁ ከአንዴም ሁለቴ በቃል አቀባዩ አማካይነት እንዲነገር አደረገ፡፡ ውሸታም መዋሸቱን እንጂ የውሸቱ ውጤት ምን ይሁን ምን ማሰብ አይፈልግምና ልጆቹ ግና እስካሁንም የት እንዳሉ አይታወቅም፡፡ … ማለቂያ ስለሌለውና መጠነኛ የዳሰሳ ጥናትም ስለሚያስፈልግ ወደሰሞኑ ልምጣ፡፡ ግን ውሸታም ካልሆኑ ለካንስ መንግሥት አይኮንም?
  7. በነዚህ ሁለት ቀናት ይህ ጎበዝ ቲያትረኛ ወደ ዐረቡ ዓለም ጎራ ብሎ የተለመደ አፍዝ አደንግዙን በማሳደስ ላይ ይገኛል፡፡ ለወትሮ መተት የሚታደሰው ጳጉሜ አምስት ወይም ስድስት መስከረም ከመግባቱ ትንሽ ቀደም ብሎ ነበር – ባዲሱ ዓመት መባቻ እንዳይሽር ወይም እንዳይከሽፍ፡፡ አትርሱኝ ባዩ አጅሬም ሕዝብን በማስጨብጨብ የተለመደ ደንቃራውን ሊጥል ወጣ ብሏል፡፡ ሰሞኑን ሰዎች ቀድመው ያበሰሉትን እንጀራ ከምጣዱ በማውጣት ራሱ አቡክቶ እንደጋገረው ሀፍረትን በማያውቀው አንደበቱ እየወሻከተ ነው፡፡ የድል አጥቢያ አርበኛው አቢይ በሰው ደንደስ መወደስን ሥራየ ብሎ ተያይዞታል፡፡ ይሁን ግዴለም፡፡ ግን ስለ ጄኔራል አሣምነው ጽጌ ሲጠየቅ የሰጠው መልስ ብዙ ትችቶችን እያጎረፈበት ነው፡፡ አቻምየለህ ታምሩ እንደጻፈው ከሆነ አሣምነው ሲፈታ አቢይ ማንም የማያውቀው ድብቁ ሰባተኛ ንጉሥ ነበር፡፡ አቢይ ሥልጣን እንደያዘ ሣምንት ሳይሞላው አሣምነውን እንዳስፈታ በሀሰት ቢመሰክርም በአሣምነው መፈተታትና በአቢይ መሾም መካከል የቀደመ የአንድ ወር ከ14 ቀን ጊዜ እንደነበረ የሚያውቁ እየመሰከሩ ነው፡፡ ዐይነ ፈጣጣው አቢይ ግን ሰውን ከመጤፍ ስለማይቆጥር ይህንን ገሃድ እውነትም ሽምጥጥ አድርጎ ይዋሻል፡፡ ስድስት በሉ፡፡
  8. አሁን በቅርቡ ዘሀበሻ ዩቲዩብን ስመለከት ደግሞ አቢይ የመሪዎችን የውሸታምነት ሪከርድ የበጠሰበትን አስገራሚ ነገር ሰማሁ፡፡ እሱም ሰልፊና ሱኒ የሚባሉ ሙስሊሞች በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ መስጊድ የሰገዱት በእርሱ ሽምግልናና እርሱ አመጣሁት ብሎ ከሚኩራራበት ለውጥ በኋላ መሆኑን አንዳችም ሳያፍር ተናገረ፡፡ ሳዲቅ አህመድና አንድ ሌላ ታዋቂ ሙስሊም እንደተናገሩት ይህ የአቢይ ንግግር ነጭ ውሸት ነው፡፡ ለምን እስከዚህን እንደሚወርድ ለማንም ግልጽ አይደለም፡፡ ከዚህኛው ውሸቱ አኳያ የሥነ ልቦና ችግር እንዳለበት መረዳት አይከብድም፡፡ ስለዚህም የህክምና ዕርዳታ ያስፈልገዋል፡፡
  9. ለወደፊቱ እነዚህን ውሸቶች ከአቢይ እንጠብቅ፡፡
    • ቀንና ሌሊት የሚፈራቁት በርሱ ፈቃድ ብቻ እንደሆነ
    • ምድርን ያለካስማ የዘረጋው፣ ሰማይን ያለባላ ያቆመው እርሱ እንደሆነ
    • ኢትዮጵያውያን ያለርሱ ፈቃድ መውለድ አይደለም መሞትም እንደማይችሉ

“ዕድሜ ለጓድ ናፖሊዮን፣ በርሳቸው አብዮታዊ አመራር በሣምንት ሦስት ዕንቁላሎችን ከመጣል ስድስት ዕንቁላሎች ወደ መጣል ከፍ ብያለሁ” ነበር ያለችው ያቺ በጆርጅ ኦርዌል ምናብ ተፈጥራ “Animal Farm” በሚባል መጽሐፍ ውስጥ የምትገኝ ዶሮ?

“The truth always comes out in the end, no matter how hard anyone tries to hide it or stop it. Lies are just a temporary delay to the inevitable.” (Anonymous)

“The trust of the innocent is the liar’s most useful tool.”  (Stephen King)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop