ለተከበራቹህ ወገኖች ያገረሸው ወረርሽኝ የኮሮና ልምድ ከጀርመን – ፈጣኑ አራተኛው ማዕበል እና የክትባት ግዴታ 16.12.2021 ካለፈው በመቀጠል አራተኛው ማዕበል ጀርመንን እያጥለቀለቃት ይገኛል። ይህንንም አስመልክቶ አዳዲስ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው። በጀርመን እና በጎረቤት አገሮች የሚመዘገበው በወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው። በአለፉት ሰባት ቀናት ውስጥ ከ100,000 ነዋሪዎች መካከል የተገኘው ኢንፌክሽን በአማካይ እንደገና በመጨመር ከ340 በላይ አሻቅቧል። ይህም በአለፈው ጽሁፌ ላይ መስከረም ውስጥ 263 ነበር። በአንዳንድ ወረዳዎችም ከሺ በላይም ደርሷል። የሚያዙትም በቀን በሰኔ እና በሐምሌ ከመቶዎች፣ በመስከረም ወደ 15ሺዎች ጨምሮ የነበረው በህዳር መጨረሻ ላይ እስከ