January 4, 2022
6 mins read

የእርግዝና ጊዜያት አመጋገብ

semah2dd

semah2dd

የእርግዝና ጊዜያት አመጋገብ

  • ማንኛውም የተረገዘ ህፃን ምግብና ንጥረነገር ማግኘት የሚችለው ከእናቱ የምግብ ተዋዕጾ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ እርጉዝ ሴት

የሁለት ሰው አመጋገብ መከተል አለባት ማለት አይደለም፡፡ በሁሉ ንጥረነገሮች የተሟላ ጥሬና የታሸጉ ምግቦችን በጥቂቱ ብቻ

ያካተተ ከሆነ ጤናማ የአመጋገብ ክህሎት ይሆናል፡፡

 

ካልሽየም (calcium)

ካልሽየም ለተረገዘው ህፃን ጥሩ የአጥንትና የጥርስ እድገትና ጥንካሬ ይረዳል፡፡  አንዲት እርጉዝ ሴት ከእርግዝና በፊት ከምትወስደው እጥፍ

ካልሽየም በእርግዝና ግዜ ልትመገብ ይገባል፡፡ ስለዚህ አንደ አይብ ወተት እርጎ አረንጔዴ ቅጠላ ቅጠሎች እና ሰርዲን ያሉትን በመመገብ

ማግኘት ይቻላል፡፡ ታዲያ እነዚህን የወተት ተዋዕጾዎች ስትመገብ አብሮት ብዙ ቅባት የወጣላቸውን ወይም (Skimmed) የሆኑትን

ከሱፕርማርኬት ገዝቶ መጠቀም ተመራጭ ነው፡፡

cheese

ፕሮቲን

ለእርጉዝ ሴቶች በፕሮቲን  የበለፀጉ ምግቦች ለህፃኑም ሆነ ለሷ ሰውነት ጠጋኝና ገንቢ ናቸው፡፡ ታዲያ በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦች እንደ

እንቁላል አሳ እንደ ኦቾሎኒ አተር እና የወተት ተዋጾኦች ስትመገብ ብዙም የበሰሉ እና የቆዩ አለመሆናቸውን  ማረጋገጥ አለበት፡፡

meat

ቫይታሚን ሲ

ቫይታሚን ሲ የእንግዴልጅ ጠንካራና ጥሩ ዕድገት እንዲኖረው, የእናት ሰውነት ከበሽታ ለመከላከል, በሰውነቷ ውስጥ ያለውን የብረት

(Iron) መጠን ለመጨመር ይረዳል፡፡ ቫይታሚን ሲ ከአትክልትና ፍራፍሬዎች በብዛት ይገኛል፡፡ በየቀኑ ቢወሰድ ደግሞ በተመጣጣኝ

ሁኔታ ሙሉ እርግዝናውን እንዳይቀንስ ይረዳል፡፡ ታድያ ፍራፍሬዎቹ የቆዩ ያልሆኑ አትክልቶቹ ደግሞ በጣም ያልበሰሉ መሆን አለባቸው፡፡

 

ሆድ አለስላሽ ምግቦች (fiber)

ለእርግዝና ጊዜ ከጥሩ አመጋገብ የላቀ ድርሻ የያዙት በሆድ አለስላሽ የምግብ ክፍሎች የበለፀጉ ምግቦች መሆን አለባቸው፡፡ ዋናው ጥቅሙ

የሆድ ድርቀትን ለመከላከል ሲሆን ሌሎች ንጥረነገሮች ስላሉትም በተጔዳኝ ይረዳል፡፡ አንደ ጎመን ፣ቴምር፣ ባቄላ ፣ቡኒ ሩዝ፣ ያልተፈተጉ

የእህል ዘሮች እና አትክልት እና ፍራፍሬ በእነዚህ ንጥረነገሮች የበለፀጉ ናቸው፡፡

 

ፎሊክ አሲድ ( Folic acid)

ፎሊክ አሲድ የምንለው ለተረገዘው ህፃን የአእምሮ እና አንጎል እድገት ወሳኝ ንጥረነገር ነው፡፡ በተለይ በእርግዝና የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት

ሌላ ጊዜ ከሚያስፈልገው 3 እጥፍ በበለጠ ማግኘት አለባት፡፡ በምግቦች ይህን ንጥረነገር ማግኘት ቢቻልም በዶ/ር የታዘዙ እንክብሎችንም

ጨምሮ መውሰድ ተመራጭ ነው፡፡ አንደ ጥቅል ጎመን ቆስጣ፣ስፒናች፣ቱና እና ብሮክሊ ያሉ ቅጠሎች በፎሊክ አሲድ  የበለፀጉ ናቸው፡፡

 

የብረት ንጥረነገር (Iron)

አይረን ከቫይታሚን ሲ ከበለፀጉ ምግቦች ጋር ሲበላ ወደ ሰውነት የመዋሀድ አቅሙ ይጨምራል፡፡ ከ ቡናና ሻይ ጋር ግን መመገብ አቅሙን

ይቀንሳል፡፡ ስለዚህ አንደ ቀይ ስጋ ባቄላ ስንዴ ጥራጥሬዎች ሰርዲንና ስፒናች ያሉ ምግቦች ስንመገብ ይሄን ማስታወስ ጠቀሜታ አለው፡፡

 

ሌሎች

ከነዚህ ከተዘረዘሩት የምግብ ክፍሎች ጋር ተያይዞ ማስታወስ ያሉብን ነገሮች

  • የሻይና የቡና ወይም (Caffeine) ያዘሉ መጠጦች መቀነስ (በቀን ከ3 ስኒ ያላለፈ)
  • የታሸጉ እንደ ማርማራታ ኬኮች ብስኩቶች እና የለስላሳ መጠጦቸ መቀነስ ከተቻለም መተው፡፡
  • በቆርቆሮ የታሸጉ፣ ተጨማሪ ምግብ ቀለማት የተጨመረባቸው ከምርጥ ዘር (processed) ምግብ የተዘጋጀ ምግቦችን መቀነስ ያስፈልጋል፡፡

እናቶች በእርግዝና ጊዜ አንዳንዴ በሽታ ወይም ምግብ በማየት የተለያዩ ምግቦች ሊያምራቸው ይችላል፡፡ ይህ ሲኖር ንፅህናው የተጠበቀ እንዲሁም

ያልቆየ እስከ ሆነ ድረስ ብትመገብ ምንም ዓይነት ችግር አይገጥም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ባልደራስ፤ የፌደራል መንግስት ህወሓትን “ያለበት ድረስ ሂዶ ማጥፋት አለበት” አለ

Next Story

መንግሥት የትግራይ ሕዝብ አሸባሪውን ትሕነግ በአደባባይ ወጥቶ ሊቃወመው ይገባል አለ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop