September 10, 2021
16 mins read

በጀርመን የገባውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በተመለከተ ያለው ቴከኒካዊና ተቋማዊ ልምድና አስተያየት – ፀጋዬ ደግነህ

ክፍል 17

ለተከበራቹህ ወገኖች                                                                           

የኮሮና ልምድ ከጀርመን –  የተሻሻሉ እርምጃዎች፣ ዴልታ ልውጥ ወረርሽኝ፣ የክትባት ውዝግብ   10.09.2021

ካለፈው በመቀጠል ሶስተኛው ማዕበልን መገታት እና “የፌደራሉ አስቸኳይ የአደጋ ጊዜ እገዳ” (emergency brake/Notbremse) መላላትን ከጠቀስኩ 3 ወራት አሳልፏል። በአውሮፓ በተለይም በጀርመን፣ ይመዘገብ የነበረው በወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ ቢመጣም የዴልታ ልውጥ ተህዋሲያን መጨመርን እያሳየ ነው። በአለፉት በሰባት ቀናት ውስጥ ከ100,000 ነዋሪዎች መካከል የተገኘው ኢንፌክሽን በአማካይ እንደገና በመጨመር ወደ 85 አሻቅቧል። የሚያዙትም በቀን በሰኔ እና በሐምሌ ከመቶዎች ወደ ከ15ሺ በላይ ወጥቷል።   ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በጀርመን ከ4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 3.8 ሚሊዮን የሚሆኑ አገግመዋል። ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የሟቾች ቁጥር 92,4ሺ ደርሷል። እስካሁን ድረስ የሰባት ቀናት የአዳዲስ የኮሮና ኢንፌክሽኖች መከሰት የወረርሽኙን ሁኔታ ለመገምገም እና ገደቦችን ለማስተዋወቅ ማዕከላዊ እሴት ነበር። አሁን ግን በክሊኒኮች/ሆስፒታሎች ላይ ያለው ውጥረት የበለጠ ትኩረት ተሰጥቶታል። ሮበርት ኮህ ኢንስትቲዩት  የአሉታ ስጋት  መለኪያውን ምን ያህል ሆስፒታል የገቡ ታማሚዎች  አሉ ወደሚል  መለኪያ (Hospitalisierungsrate hospitalization rate) ቀይሮታል። በዚህ መሠረት በ10.10.2021 ሆስፒታል የገቡት መጠን በመቶሺ ሰዎች 1.89 ሲሆን፣ ከወራቶች በፊት ከመቶሺ ሰዎች በቀን እስከ 15 ደርሶ ነበር።

  1. ማህበርዊ ግንኙነት

በዝግ ክፍሎች ውስጥ በግል ግንኙነቶች ላይ ገደቦች ከተነሱ ቆይተዋል። ቁጥራቸው ከበዛ ሰዎች ጋር ከቤት ውጭ ካሉ ሰዎች ጋር ከመገናኘት በፊት በኮሮኔቫቫይረስ ኢንፌክሽን አለመኖሩን ለማረጋገጥ ሙሉ በሙሉ መከተብ ወይም ፈጣን ምርመራ ይመከራል።  ለምሳሌ በበርሊን እንደ ሠርግ ፣ የልደት ቀን ግብዣዎች ወይም ጥምቀቶች ላሉ አስፈላጊ የግል ዝግጅቶች እስከ 50 ሰዎች በቤት ውስጥ እና እስከ 100 ሰዎች ከቤት ውጭ ሊሰበሰቡ ይችላሉ። ዕድሜያቸው እስከ 14 ዓመት የሆኑ ሕፃናት፣ የተከተቡ እና የተመረመሩ እዚህ ላይ አይቆጠሩም። በቀብር ስፍራዎች እና ለመታሰቢያ አገልግሎቶች የሰዎች ገደቦች የሉም። ሆኖም  ከ20 በላይ ሰዎች ከተሳተፉ ተጨማሪ መመሪያዎችን መከተል አለባቸው።

  1. ስብሰባ

ለግል ስብሰባዎች – ከፍተኛው የሰዎች ብዛት እና ከፍተኛው የቤተሰብ ብዛት ተነስቷል።

አየር በሚያስተላልፉ በቤት ውስጥ አዳራሾች ውስጥ ለሁሉም ክስተቶች ከ1ሺ ሰዎች መብለጥ የለበትም። በእነዚህም መሳተፍ የሚፈቀደው አሉታዊ ምርመራ ላደረጉ፣ ሙሉ በሙሉ ለተከተቡ ወይም ላገገሙ  ብቻ ነው።

ከቤት ውጭ የግል ስብሰባዎች ይፈቀዳሉ። ዕድሜያቸው ከ 14 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት እና ሙሉ በሙሉ ክትባት ያገኙ ወይም ያገገሙ ሰዎች እዚህ ላይ አይካተቱም። በአጠቃላይ ቁጥሩ ከ2000 አይበልጥም። በዝግጅቱ ከ 100 በላይ ሰዎች ከተሳተፉ አሉታዊ የናሙና ሙከራ ውጤት ማቅረብ ግድ ነው።  በስብሰባዎች ላይ ያልተከተቡ፣ ወይም አሉታዊ ምርመራ ያላደርገ ሰው ቋሚ መቀመጫ  / ወንበር ሊሰጠው ይገባል። እነዚህ ተሳታፊዎች ሲገቡ እና ሲነቃነቁ የህክምና ማስክ ማድረግ አለባቸው። ማስኩንም ሲቀመጡ ያወልቁታል።

 

  1. ክለቦች

ለምሳሌ በበርሊን ያሉ ክለቦች በአጠቃላይ እንደገና እንዲከፈቱ ተፈቀዶላቸዋል፣ ግን የተወሰኑ የጥበቃ እና የንፅህና አጠባበቅ መስፈርቶችን ማክበር አለባቸው። በቤት ውስጥ የዳንስ ዝግጅቶች ውስጥ እንዲሳተፉ የተፈቀደላቸው ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ወይም ያገገሙ ሰዎች ብቻ ናቸው። 1,000 ሰዎች የላይኛው ወሰን ሲሆን፣ ሜካኒካዊ የአየር ማናፈሻ መሳሪያ ከተጠቀሙ 2,000 ሰዎች የላይኛው ወሰን ነው። መከላከያ ማስክ መጠቀምም አያስፈልግም። አዘጋጆች የንፅህና አጠባበቅ ጽንሰ -ሀሳብ የማውጣት እና የምዝገባ ሰነዶችን የማቆየት ግዴታ አለባቸው።

  1. ትምህርት ቤቶች

ተማሪዎች እና መምህራን በሳምንት ሁለት ጊዜ የአሉታ ናሙና ምርመራ ያደርጋሉ። ይህ የግዴታ ምርመራ ሙሉ በሙሉ ለተከተቡ ወይም ከበሽታ ባገገሙት ላይ አይተገበርም።

 

  1. የ FFP2 ማስኮች

በኢንፌክሽን መከላከያ ድንጋጌ መሠረት የ FFP2 ማስኮች ንክክኪነት በአለባቸው ስራዎች፣ በህክምና አገልግሎት፣ በመታሻ አገልግሎቶች፣ በህዝብ ማመላለሻ ውስጥ ያሉ ተሳፋሪዎች መጠቀም ይጠበቅባቸዋል። በባቡር ጣቢያዎች፣ በታክሲዎች፣ በአውሮፕላን ማረፊያዎች እና በመርከብ ተርሚናሎች ውስጥም FFP2 ማስኮች መጠቀም አለባቸው። በሆስፒታሎች ውስጥ ጎብኝዎች የ FFP2 ማስክ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።

  1. ራስን ለይቶ መቀመጥ (ኳራንቲን) የሚያስገቡ ሀገሮች

የኮሮና ስርጭት ያልተገደበባቸው እና የልውጡ የዴልታ ተህዋሲ ከተስፋፋባቸው ሀገሮች የሚመጣ ወይም ጎብኝቶ የሚመልስ ሰው እስከ 10 ቀን የሚደርስ ኳራንቲን ይገባል። እነዚህ ሀገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ የለችበትም። ከታች በተጠቀሱት ከፍተኛ ተጋላጭ በሆነ አካባቢ የቆዩ ሰዎች ጀርመን ከደረሱ በኋላ ወዲያውኑ ወደ ቤታቸው በመሄድ እና ለአሥር ቀናት በቤት ውስጥ ራስን ለይተው መቆየት አለባቸው።  የክትባት ማረጋገጫ ወይም አሉታዊ የምርመራ ውጤት ያቀረበ ሰው በቤት ውስጥ ያለውን ገለልተኛነት አስቀድሞ ያለጊዜው ሊጨርስ ይችላል። ሀገሮቹም ፦

ግብፅ አልባኒያ አልጄሪያ አርጀንቲና ባንግላዴሽ ቦሊቪያ ቦትስዋና ብራዚል ኮስታ ሪካ ዶሚኒካ ኢኳዶር እስዋቲኒ ፊጂ ፈረንሳይ-(የኦሴቲያን ክልሎች ፕሮቨንስ-አልፕስ-ኮት አዙር ኮርሲካ ጓዴሎፔ ማርቲኒክ ሬዩንዮን ቅዱስ ባርቴሌሚ ቅዱስ ማርቲን ፈረንሣይ ጉያና እና የፈረንሣይ ፖሊኔዥያ) ጆርጂያ ግሪክ – (ክሬት ደቡባዊ ኤጌያን እንደ ሮድስ ኮስ ማይኮኖስ ወይም ናክስሶስ) ሄይቲ ሆንዱራስ ሕንድ ኢንዶኔዥያ ኢራቅ ኢራን አየርላንድ – ድንበር እና ምዕራባዊ ክልሎች እስራኤል፣ የፍልስጤም ግዛቶች ጃማይካ ካዛክስታን ኬንያ ኮሎምቢያ፣ ኮሪያ (ዴሞክራቲክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ) ኮሶቮ ኩባ ኩዌት ሌሶቶ ሊቢያ ማላዊ ማሌዥያ ሞሮኮ ሜክሲኮ ሞንጎሊያ ሞንቴኔግሮ ሞዛምቢክ ምያንማር ናሚቢያ ኔፓል ኔዘርላንድ – የአሩባ ኩራኦኦ ቦናይየር ሲንት ኤውስታቲየስ ሲንት ማርቲን ሳባ ሰሜናዊ መቄዶኒያ ኦማን ፓፓዋ ኒው ጊኒ ፓራጓይ ፔሩ ፊሊፒንስ ፖርቱጋል – አልጋሪቭ ክልል የሩሲያ ፌዴሬሽን ሲንት ኪትስ እና ኔቪስ፣ ቅዱስ ሉሲያ፣ ዛምቢያ ሴኔጋል ሰርቢያ ሲሸልስ ዚምባብዌ ደቡብ አፍሪካ፣ ሱዳን፣ ሱሪናም የሶሪያ አረብ ሪፐብሊክ ታጂኪስታን ታንዛኒያ ታይላንድ ትሪንዳድ እና ቶቤጎ፣ ቱርክ ቱኒዚያ ቱርክሜኒስታን ሰሜን አሜሪካ ኡዝቤኪስታን የታላቋ ብሪታንያ እና የሰሜን አየርላንድን ጨምሮ፣  ቬትናም ቆጵሮስ

  1. የክትባት ይዘት

2,34 ቢሊዮን (29,8 %) የአለማችን ህዝብ ሲከተብ፣ አፍሪካ እስካሁን 2,5% ብቻ ሰው ነው የተከተበው። ይህም አፍሪካ ገና 10% ሳይዳረስ ሌሎች ሀገሮች ጀርመንን ጨምሮ ሶስተኛ የማጠናከሪያ ክትባት መስጠት መጀመራቸው ሞራላዊ ትችትን አስነስቷል። ለቁጥር ያህል ጀርመን 51.5 ሚሊዮን (62%)፣ ቻይና ወደ 889 ሚሊዮን (64%)፣ ሕንድ 167 ሚሊዮን (12.2%)፣ ዩናይትድ ስቴትስ 177 ሚሊዮን (54.0%)፣ ብራዚል 68.4  ሚሊዮን (32,4%)፣ ስፔን 67.8 ሚሊዮን (74.0%) ሲከትቡ ከአፍሪካ ለመጥቀስ ሞሮኮ 16,3 ሚሊዮን (44%) ደቡብ አፍሪካ 6.6 ሚሊዮን (11.8%)  ኢትዮጵያ 2.7 ሚሊዮን  (2% – 2.5 %) ተከትበዋል።

 

  1. የክትባት ማህበራዊ ውዝግብ

የወረርሽኙ ክትባት ውዝግብ ማህበረሰቡን እና ፖለቲከኞችን ከፍሎ ይገኛል።

በአንድ በኩል ሰውን ተከተቡ ብሎ ማስገደድ እና ማዕቀብ ማድረግ  የሰባዊ/ ተፈጥሯዊ መብትን መድፈር እና ዲሞክራሲን የሚፃረር መሆኑን የሚገልፁ ሲኖሩ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በተከተቡት ዋጋ እና አገጋሚዎች በሚከፍሉት ጤና በመጠቀም ከዚህ በኋላ ወረርሽኙ አይደርስብንም የሚሉ ራስ ወዳዶች እና ከሶሊዳሪቲ መንፈስ ውጭ የሆኑ በወረርሽኝም ከተያዙ በማራባት የሌላውን የጤንነት መብት የሚያጠቁ ናቸው የሚሉ አሉ።

ብዙ አገሮች መከተብን የሚያስገድድ ወይም ባለመከተብ ጥቅሞች የሚታጣበትን መመሪያዎች ሲያወጡ፣ ጀርመን ላይ የመከተብ ግዴታ እስከአሁን ድረስ የለም። ቢሆንም በተለይም በተለያዩ ፌደራል ስቴቶች ያሉ ፖለቲከኞች ለመከተብ ለማይፈልጉት ጥቅም አስቀሪ መመሪያዎችን ለማውጣት እየተዘጋጁ ይገኛል።

  • ለምሳሌ በፈቃዱ ክትባቱን አልወሰድም ሰው ያለ ኳራንቲን በመግባት ከስራ የቀረ እንደሆነ፣ ኳራንቲን በነበረበት ወቅት ሳያቋርጥ የሚከፈለው ደሞዙ ከኳራንቲን ወጥቶ ስራ እሰከሚጀምር ድረስ ይቋረጣል።
  • ሌላው ደግሞ በፈቃድ ያልተከተበ ሰው የኮሮና የናሙና ምርመራ ሲያደርግ እንዲከፍል የሚጠይቅ ነው።
  • ለተከተቡት የተለያዩ የገንዘብ ድጉማ የታሰብም አለ። ለምሳሌ ለምግብ ቤቶች የሚሆን 50 ዮሮ ኩፖን እና የመሳሰሉት።
  1. ክትባት ለነፍሰ ጡር እና ለሚያጠቡ ሴቶች

የጀርመን የክትባት ኮሚሽን STIKO ለነፍሰ ጡር እና ለሚያጠቡ ሴቶች የኮቪድ -19 ክትባት እንዲሰጥ ረቂቅ ውሳኔ አቅርቧል። በተጨማሪም ባዮንቴክ ፋይዘር በቅርቡ እንደገለፀው ከአምስት እስከ አስራ አንድ ዓመት ለሆኑ ሕፃናት ተስማሚ የሆነ ክትባት በማዘጋጀት እና በሚቀጥሉት ወራት እንድሚለቀቅ ነው።

መልካም የጤንነት፣ የደስታ፣ የመርዳዳት እና የሰላም አዲስ አመት 2014!
እንዲሁም መልካም የዓለም የመጀመሪያ እርዳታ ሰጪዎች ቀን (11. September)

አዲሱ ዓመት ለመጻፉ በመጠባበቅ ላይ እንዳለ የአንድ መጽሐፍ መጀመሪያ ምዕራፍ ከፊታችን ቆሞልናል።
ግቦችን በማስቀመጥ ያንን ታሪክ ለመፃፍ እንችላለን!
ሚሊዲ ቢቴ

ከመልካም የጤንነት ሰላምታ ጋር
ፀጋዬ ደግነህ (ዶ/ር)

——-

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

Go toTop