December 11, 2019
15 mins read

አጨብጫቢነት ዴምሕት/ለማ ወዘተ – የመርሕ ድህነት እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ

ዴምሕት የተባለ የትግራዊ ፖለቲካ ድርጅት ኤርትራ በነበረበት ጊዜ እንደተለመደው ብዙ አጨብጫቢ ለማግኘት ችሎ ነበር። እንዴው ህወሓትን ሊጥል የሚችል ኃይል በሚል ብዙ ዜና ይሰራለት እንደነበር አሁንም ከዩቲዩብ ያልተፋቁ ዜናወች ይመሰክራሉ። የዜናው አቅራቢወች ስለ ድርጅቱ ምንነትም ይሁን ማንነት ግድ አልነበራቸውም እናም የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ እያውለበለበ የሚያሳይ የሰለጠነ ወታደር ከኤርትራ መሬት ያሳዩን ነበር። ኮማንደሮቻቸውንም ያስደምጡን ነበር። እንዴውም ጥብቅ እና ዋነኛ የትግል አጋርነቱን ጨምሮ ስለሚገልጹ ብዙ ደጋፊ ነበረው ብል አልዋሸሁም። ነገርን ነገር ያነሳዋል ይባላል የጄኔራል ኃይሉ ጎንፋን እና የጄኔራል ከማል ገልቹን እማ ብዙ ተብሏል። የዴምሕት ዋና ኮማንደር ሞላ አስገዶም በከዳ ማግስት ተመሳሳይ ዜናም ቀርቦ እርሱን የተካው በሚል ብዙ ተብሎለታል። ሲጀመር የኤርትራን የትግል መግቢያነት የተቃወሙ ወገኖች ለምን በሚል ተሰድበዋል። አንዳንድ ጋዜጠኞች ከቦታው ድረስ በመሄድም የኤርትራን መኮንኖች መልካምነት እና ለኢትዮጵያ ደግ አሳቢነት ዘግበዋል። የፈረደበት አጨብጫቢም ስለመርህ ግዱ አይደለም እና ብዙ ብዙ ለግሷል።

ይህን ስል ሂሳብ ለማወራረድ አይደለም ግን መርህ የሚባል ሁነኛ ሰውነትን ከሌላ የሚለይ ቃል አለ። ከማጨብጨብ ይልቅ መጠየቅ ቢቀድም የሚያመዛዝን ፈጣሪ ለሰው ልጅ የሰጠው አመዛዛኝ ልቦና ስለአለን ከስህተት ያድነናል። በይበልጥም አሁን ሀገራችን ከገባችበት ቀውስ እንድትወጣ ያግዘናል። ከመጣ ከሄደው። ጥሩ ከተናገረው እና ከሰበከው ሁሉ ጋር ማጨብጨብ ትቶን ሲሄድ መደናገጥ ከመፍጠሩ በላይ ጠላቶቻችንን ደግፈን ወዳጅን የምናጠፋበት ሁኔታ ደጋግሞ ታይቷል።

የዛሬ አመት “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” ስላለው ሰው ብቻ እንደምሳሌ ብንወስድ በእርሱ የአንድ ቀን ንግግር በፍቅር ተቃጥለን ያለቀስንም አንጠፋም። በጀንበር ያፈቀርነውን በአንድ ጀንበር አክ ብለን እንደተፋነው ደግሞ አይተናል ታዝበናል። እዚህ ከምኖርበት ሀገር አሜሪካኖች አንድ ጥሩ እና ጠንካራ ባህርይ ካየሁባቸው ከማወደስ ቁጥብ መሆናቸው ነው። በይበልጥም ሁሉን ነገር የመጠየቅ ባህርያቸው ጠንካራው እና መልካሙን ጎዳና የመራቸው ይመስለኛል። ከንቱ ውዳሴን አለማወቅ፣ መርህን ተከትሎ ይሉኝታ የለሽ ባህርያቸው ሁልግዜ ይማርከኛል። አሜሪካኖች ሁሉን ለምን ብለው ይጠይቃሉ። ለብዙ ግዜ አዝኘ የምሳ እያልሁ እሰጠው የነበረ አንድ ሰው (አዝኘለት ማለት ነው) መጥፎ ስራ ከአይሁበት በኋላ በአንዱ ቀን እንደተለመደው የምሳውን ሊወስድ ሲመጣ የማልሰጠው መህኑን ስነግረው አፋጦ ለምን ብሎ የጠየቀኝን ቀን አልረሳውም። ለክፉም ሆነ ለደጉ አንድ ነገር ከማድረግ በፊት ለምን ብሎ መጠየቅ ጥሩ ነገር ነው ማለቴ ነው።

በአንድ ወቅት ወይዘሪት ብርቱካን ሚዲቅሳ የቅንጅት መሪወች ከስር ተፈተው ወደዚህ ወደአሜሪካ የመጣች ቀን አውሮፕላን ሜዳ ሊቀበሉ ከሄዱት እየተንደረደሩ ከእግሯ ስር የወደቁት ሰወች ይታወሱኛል። ለምን ወደቁ ሳይሆን የመውደድ እና የመጥላት ልካችን ድንበር የለሽነቱ ከመስመር እንድንወጣ እያደረገን በማየቴ እና በመታዘቤ ነው። የሰርቬይ ጥያቄ ስትጠየቅ ከ 1 እስከ 10 ስምምነትህን ስጥ ይባላል። እንዳጋጣሚ የዘመናችን የእኛን የኢትዮጵያውያንን ሰው ከሌሎች በዚህ ምላሽ ብናወዳድር በእኛ ምላሽ ፣2፣ 3፣4፣ 5፣ 6፣ 7, 8 እና 9 የሚኖሩ አይመስለኝም። ለጠላነው 1 ለወደድነው 10 የምንሰጥ መስሎ ይሰማኛል።

ወደዋናው ነገር ስመለስ ህወሓት ትናንት ባወጣችው ዜና ዴምሕት የተባለው ትግራዊ ድርጅት። ያውም በኤርትራ ሜዳ ጠበንጃ ታጥቆ ለአመታት ወያኔን ላስወግድ ነው ያለ ድርጅት ሀገር ከገባ በኋላ ድምጹን ሰምቸው አላውቅም ነበር። በትናንትናው ዜና ድምሂት ከህወሓት ተዋሀደ የሚል በሰማሁ ግዜ የታየኝ ለዚህ ድርጅት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የገንዘብ እና ሌላም ድጋፍ ያደረጉ ወገኖቸ ታሪክ ነው። ከፍጥረቷ የምናውቃት ህወሓት በአድርባይ የፖለቲካ ፍልስፍናዋ ጠላቷን ሳይቀር ለእርሷ ግብ እንደምትጠቀምበት ያኔ 1969 ሻለቃ ገብረ ሕይወት የተባለ የመላኩ ተፈራ ምክትል እና የጎንደር አስተዳደር የደርግ ተወካይ የሆነ የህወሓት አባል የጎንደርን ወጣት አርሷደር እንዴት እንደጨረሰ ታሪካችን ነው። ከዚህ እና በቀዩ ሽብር ተሳታፊ የነበረችው የህወሓት ጥቁር ታሪክ እንደተማርሁት ዴምህት (የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያው ንቅናቄ) የህወሓት አገልጋይ እንደነበረ ጥርጥር አልነበረኝም። ይባስ ብሎ ያስፈራኝ የነበረው ገና ህወሓት በስልጣን ላይ በነበረችበት ግዜ ስብሀት ነጋ ወይንም አባይ ጸሀየ አለያም ጌታቸው አሰፋ ከህወሓት ተሳናበትን ብለው መጥተው ይህን ሕዝብ ገንዘቡን እንዳይሞሸልቁት ነበር። መቃወማችን ስለማይቀር እኛም እንዳንሰደብ ነበር። በፈጣሪ ድጋፍ አለፈ። ለዥህ አስተሳሰቤ ምክንያት የሆነኝ ዳዊት ከበደ የተባለ የአውራምባ ጋዜጠኛን ገንዘብ እየከፈሉ ከአገር ለአገር ያዞሩት የነበሩትን ስለአየሁ ነበር። ባጋጣሚ አንድ የታመመ ሰው ለመጠየቅ እቤቱ ስገባ ዳዊት ከማውቃቸው የከተማችን ተቃዋሚ ነን ይሉ የነበር ሰወች ጋር ተቀምጦ አገኘሁት እናም አስተዋውቀው የፖለቲካ አቋሜን ሲነግሩት (ለምን እንደነገሩት እስካሁን አይገባኝም) ዳዊት ግንባሩን እንደተመታ ሰላምታም በቅጡ ሳይሰጠን እንደቀረ ትዝ የለኛል። ይህን ለማለትም የፈለግሁ መርህ የሚሉት ነገር ከሀገራችን ተሟጦ የጠፋ ስለመሰለኝ ነው። ልሰሳት እችላለሁ ግን በአንድ የሰው ንግግር እንደቅርብ ወዳጅ ተሎ መጠምጠም እና በአንድ የአሉባልታ ወሬ መበርገግ የእኛ ስርአት ሆኖ እየታየኝ ተቸግሬአለሁ። በ1998 የህወሓትን ዜጎችን ኤርትራዊ ስለሆናችሁ ውጡ ስትል እና መለስ ዜናው ከህወሓግ አጋሰሶች ጋር ሆኖ አይናቸው ካላማረን ማባረር መብታችን ነው ሲለን ያጨበቸቡ እና ውስኪ የከፈቱ ልንታገር ኤርትራ ገባን ላለሉት ቀድመው አፋሽ አጎንባሽ እንደሆኑ የማልረሳው ተውኔት ሆኖብኝ ቆይቷል።

መርህ ከሌለን ሁሌም ድጋፋችን ለጠላት ብቻ እንጅ ሀገርን እና ወገንን ልናጠናክር አይቻለንም። እና ጥያቄ ምን ይሁን ምን ማድረግ ይገባናል? ነው። በበኩሌ ለመጣ ለሄደው አፋሽ አጎንባሽ መሆን ተገቢም አይደለም ሀገርን የበለጠ የሚጎዳ አጥፊ ጠላትን መተባበር ነው ባይ ነኝ። መርህ ስንል ሀገራችን ኢትዮጵያ ነጻ ሀገር ናት የዘር ፖለቲካ መወገድ አለበት ስንል ይህን ለማስወገድ ከምር ከሚሰሩት ጋር ማበር እና አምርሮ መታገል ይገባል ባይ ነኝ። የዘር ፖለቲካን እንቃወማለን ብለው ከኦነግ እና መስል ድርጅቶች ጋር የተለጠፉት በየትኛውም መልክ ነጻ ሊሆኑ አይችሉም።

ለአመታት ከጠላት ጎን ቆመው ሕዝብ የገደሉ ያስገደሉ ንስሀ ሳይቀበሉ በአንድ ጀንበር እፍ ያለ ፍቅር ውስጥ መግባት ለሀገርም ሆነ ለግል ጎጅ ባህርይ ነው። “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” ያለው ሰው ምን ያሕል ሰውን እንዳሳበደ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው። የማታ ማታ “ሕዝቤ” ያለው ያው ተጠምቆ ያደገበቱን የዘር መንደሩን ሰው ብቻ ነው። ይህ ሰው ስለኢትዮጵያም ሆነ ስለሏላዊነታ ግዱ እንዳይደለ በሰሞኑ በሰጠው የአሜሪካ ድምጽ ቃለምልልስ አስረድቷል። የመንጋ ፖለቲካ ይብቃ። ለአመታት ሀገር በባንዳ ጠባብ ብሄርተኛ ስትታመስ አንገት ደፍቶ ይሰራ የነበር እና ፖለቲካ እና ኤሌትሪክ በሩቅ ያለ በአንድ ጀንበር ብቅ ብሎ አራጊ ፈጣሪ ሆኖ ሲገኝ እና ተደማጭ ሲሆን በእውነቱ ዋ እንድንል አስገድጎናል። እንዲህ አይነቱ መብዛት እና መበረታታት ደግሞ ሀገር እና ወገን መሪ አልባ እንዳደረገ ግልጽ ነው። በክፉ ቀን ይህን መሰል ሰወች ልክ እንደበረዶ ክምር ሟሙተው ድራሻቸው ስለሚጠፋ ማለት ነው። የፈሪ መንጋን ስለተናገረ ማጀገንም ሌላው ጎጅ ዘመን አመጣሹ ክፉ ባህርይ ነው። ጠላት ውስጥ ለውስጥ እየተደራጀ እያደራጀ፤ እያስተጠቀ እያሰለጠነ ባለበት በባዶ ሜዳ ሰባራ ክላሽን ይዞ መፎከር ለቁርጥ ቀን ልጆች የሚጎዳ ነው። ገንዘብ እየሰበሰቡ ለማይረባ እና ለምናውቀው ፈርጣጭ ማሸከም ለኋላ ክህደት እና ትዝብ ካልሆነ ፋይዳው ብዙ አይደለም። ስለሌሎች ከማውራት እራስን ማደራጀት፣ እና ለክፉም ሆነ ለደግ መጭ ዘመን ዝግጁ ሆኖ መገኘት ለሀገር ለወገን እና ለእራስም መመኪያነት ነው።

ህወሓት ለኢትዮጵያ አትተኛም። ህወሓትን መከወን የወደፊት ከባዱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ስራ እና ተግባር ይመስለኛል የሀገሪቱን አንድነት በአስተማማኝ ለማስቀጠልም ሆነ ነጻ ሕዝባዊ መንግስት ለመመስረት። የህወሓት መሪወች ሸሽተው መቀሌ ስለገቡ ተወግደዋል ማለት ግን አለመሆኑን ልናውቅ ይገባል።፡የሀገሪቱ ደህንነት መዋቅር፣ የወታደራዊ እና የፖለቲካ ሰንሰለቱ ምን ያህል ከዚህች ጸረ ሕዝብ ድርጅት ነጻ ነው? Command post መቀሌ አድርጋስ ተዛዝ በእዝ ለማስተላለፍ አለመቻሏን እንዴት ልናውቅ እንችላለን። ይህ እና ብዙ መሰል ጉዳዮችን ማንሳት ይቻላል። ለሁሉም ከመንጋ ፖለቲካ መውጣት። እራስን ማደራጀት እና ከሚመስሉት ጋር ኃይል ሆኖ መውጣት ለነገ የማይባል የዚህ ትውልድ ግዴታ ነው። የያ ትውልድ እንቁወች እና ያልተንበረከኩ ዛሬም ስለአሉ ከነሱ ስህተት መማር። ጥንካሬአቸውን ደግሞ መውሰድ ይቻላል ይገባልም።

ከዚህ በተረፈ ለመጣ ለሄደ አፈኛ ማጨብጨቡን ትተን እራስ ግምገማ እና መደራጀት ላይ ብናተኩር ይገባል ባይ ነኝ። መርህ ይቅደም! ማጨብጨብ ይቁም!

Adios!

 

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop