July 7, 2019
11 mins read

ከጸጥታና ፍትህ የጋር ግብረ ሃይል በቅርቡ በባህርዳር እና በአዲስ አበባ በተፈጸመው የግድያ ወንጅል ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ 

ሰኔ 15 ቀን 2011 በባህርዳር ከተማ እና በአዲስ አበባ ከተማ የመፍንቅለ መንግስት ለማድረግ በተፈጸመ አሰቃቂ የወንጅል ድርፈጊት ከፍተኛ የክልል እና የመከላካያ ሃላፊዎች ህይወት እንዳለፈ እንዲሁም ሌሎች የጸጥታ አካላት እንደሞቱና የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ከጸጥታና ፍትህ የጋር ግብረ ሃይል መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

በወቅቱ የተጠነሰሰው ሴራ በአማራ ክልል ህዝብ በክልሉ እና በፌደራል የፀጥታ ሃይሎች የተቀናጀ ጥረት የከሸፈ ሲሆን ÷ ወንጀል ፋፃማችን ለህግ ለማቅረብ የወንጅል ምረመራ ቡድን በማቋቋም የተጠናከረ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ግብረ ሃይሉ ሰኔ 20፣ 2011 በሰጠው መግላጫ በክልል 212 በአዲስ አበባ 43 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና በቀጠይ የሚደረስበትን ውጤት ለህበረተሰቡ በተከታታይ እንደሚያሳውቅ መገለጹ ይታወሳል፡፡

በዚህ መሰረት ግብረ ሃይሉ ከባር ዳር እስከ አዲስ አበባ በተዘረጋ ትስስር የተፈጸመውን ውስብስብ የወንጀል ሂደት በማጣራት ያገኛቸውን ውጤቶች ለህብረተሰቡ ማሳወቅ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል፡፡

በዚህም ይህ መገለጫ አስከጠተቀረበት ጊዜ ድረስ በባህርዳር 213 በመፈንቅለ መንግስቱ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር እንዲውሉ ተደርጓል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥም የክልሉ ልዩ ሃይል አመራር አባላት የክልሉን የጸጥታ መዋቅር የሚመሩ ከፍተኛ ሃላፊዎች እና አባላት እንዲሁም ሌሎች ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው ተጠርጣዎች መከተታቸውን በተካሄደው ምርመራ ታውቋል፡፡

ከዚህ በፊት ከተገለጸው መግለጫ በተጨመሪ ግብር ሃይሉ በአደረገው ክትትልና ምርመራ ከተጠርጣሪዎቹ 59 ክላሽ እንኮቭ ጠመንጃዎች እና በርካታ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ወንጀል ፋፃሚዎቹ የጠነሰሱትን ሴራ የሚመሩባቸው የተለያዩ የስልጠና መንዋሎች እና የደህነነት አደረጃጃት መዋቅሮችም ተግኝተዋል፡፡

በመፈንቅለ መንግሰቱ ተሳትፈዋል ተብለው የተያዙ ተጠርጣሪዎች ድርጊቱን ሲመራው እና ሲያቀነባብረው ከነበረው ብርጋዴል አሳምነው ጽጌ ጋር ቀጥታ ግንኙነት እንደነበራቸው ተረጋግጧል፡፡

ብርጋዴል አሳምነው ጽጌ ቀደም ሲልም በህ ገወጥ መንገድ ለመወቀሳቀስ እና ራሱን ለመደበቅ በማሰብ የራሱ መኖሪያ ቤት እያለው በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የቤት ቁጥር 288 በአቶ ወዳጆ ማሞ ተመዝግቦ በሚታወቀው ቤት17ኛ የቤቱ ነዋሪ በመምሰል የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የመታወቂያ ካርድ በማውጣት የተለያዩ የወንጀል ድርጊት ፈፃሚ ቡድኖችን ስያደራጅ እንደነበረ በምርመራው ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በተያያዘም በኦሮሚያ ክልል ቡራዩ ከተማ ኖኖ ቀበሌ የሚገኘው የብርጋዴል ጀኔራል አሳምነው ጽጌ መኖሪያ ቤት ሲበርበር አንድ ክላሽ እንኮቭ÷ እንድ ራቫ ፎር ተሸክርካሪ የተለያዩ ሰነዶች ወደ ፊት የሚጣራ ሆኖ የከበሩ ድንጋዮች የተቀመጡበት የባንክ ደብተር በማስረጃነት ተይዘዋል፡፡

ሃምሳ አላቃ ፈቃዱ ሃብታሙ የታባለ የቀድሞ መከላከያ አባል የነበረ የአማራ ክልል ልዩ ሃይል አሰልጣኝን የብርጋዴል ጀኔራል አሳምነው የቅርብ ሰው ከጀኔራሉ ባለቤት ወይዘሮ ደስታ አሰፋ ጋር በተጠቀሰው መኖሪያ ቤት ተሸሽጎ መያዙን እና ሁለቱም በቁጥጥር ስር ውለው ምራመራው እየተጣራ እንደሚገኝ ግብረ ሃይሉ አስታውቋል፡፡

በዚሁ በቡራዩ ከተማ በሉ ከታ ቀበሌ በብረጋዴል ጀኔራል አሳማነው የተመዘገበ ሌላ መኖሪያ ቤት እና በቦሌ ክፍል ከተማ በተለምዶ ሃያት ተብሎ በሚጠራው አአካባቢ በስሙ ተመዝግቦ የተገኘው ባለ 3 መኝታ ቤት ኮንዶሚኒየም ውስጥም የተለያዩ ሰነዶች እና ክላሽ እንኮቭ ጠመንጃ ተገኝቷል፡፡

በሰበታ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ አንድ ማካሮቭ ሽውጥ ከበርካታ ጥይቶች ጋር እና በአዲስ አበባ ከተማ የፈጠረውን የአደረጃጀት ትስስር በአስረጅነት ከሚጠቅሱ ሰነዶች ጋር በግብረ ሃይሉ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በብርጋዴል ጀኔራል አሳምነው ጽጌ እና ሌሎች በቁጥጥር ስር በዋሉት አመራሮች ተሞክሮ ከከከሸፈው መንቅለ መንግስት የደህነነት እና ውትድርና ስልጠና የወሰዱ መኖራቸውም ታውቋል፡፡

ይህን ስልጠና የወሰዱ ሃይሎች በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች ግድያ እና የተደረጃ ዘረፋ ለመፈፀም እና ለማስፈፀም ብሎም ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦችን ለማጋጨት ተልዕኮ እንደተቀበሉ ለማዎቅ ተችሏል፡፡

በተለይም በአማራ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች እና በአዲስ አበባ ከተማ ረብሻና ሁከት ለመፍጠር ህዝብን ለማሸበር እንዲሁም በተለያዩ የመንግስት ሃላፊዎች ላይ የግድያንጅል ለመፈፀም መሰማራታቸውም በምርመራው ተረጋግጧል፡፡

በሌላ በኩል ተጠርጣሪዎቹ ለወንጀል ድርጊታቸው ማስፈፀሚያ የሚሆን ገንዘብ ቁሳቁስ በማሰባሰብ ስራ ላይ እንደተሰማሩ ግብረሃይሉ ባአደረገው የማጣራት ሂደት አረጋግጧል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ግድያ ጋር እና ከባህርዳሩ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጋር በተያያዘ 60 ተጠራጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው የምርመራ እና የማጣራት ስራ እየተከናዎነ ይገኛል፡፡

በተደረገው ብረቱ ክትትል ለሽብር እና ዝርፊያ ሊውሉ የተዘጋጁ ብዛት ያላቸው የጦር መሳሪዎች መሰል ጥይቶች እና 84 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በተያያዘም 10 ተጠርጣሪዎች የተለያዩ ሀገራትን ገንዘብ ኖቶች በህገ ወጥ ሲዚዋውሩ እና ለወንጀል ድርጊት ሊጠቀሙ ሲንቀሳቀሱ በተደረገ ክትትል እና ፍተሻ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የጸጥታና ፍትህ የጋራ ግብረ ሃይሉ ከወንጀል ድርጊቱ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩትን ለፍርድ የማቅረብ ሂደት ተጠናክሩ እንደሚቀጥል እያሳወቀ የተጀመረውን የህግ የበላይነት የማስከበር እንቅስቃሴ በፍጹም ለድርድር እንደመያቀርብ ያስገነዝባል፡፡

ህብረተሰቡ በተለይም የአማራ ክልለ ህዝብ እና የፀጥታ ሃይል ሰላሙን በማስጠበቅ እንዲሁም ተጠርጣሪዎችን ለህግ በማቅረብ ላበረከተው ከፍተኛ ሚና ግብረ ሃይሉ ምስጋና እያቀረበ ማኛውም ስጋት ተወግዶ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲቀጥል ለሚካናዎነው ተግባር አሁንም ህብረተሰቡ እንደወትሮው የተለመደ ትብብሩን እንዲቀጥል የጋራ ግብረ ሃይሉ ማሳሰብ ይወዳል፡፡

መንግስት በቀጣይነት የሃገሪቱን ብሄራዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅ የተሟላ ቁመና እንዳለው እየገለጸ የዜጎችን ሰላም እና ደህነነት አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውንም የሽብር እንቅስቃሴ ለአፍታም ቢሆን እንደማይታገስ ግብረ ሃይሉ በድጋሜ ያረጋግጣል፡፡

ህብረተሰቡ ከጉዳዩ ጋር በተገናኘ ሆን ተብለው ከሚሰራጩ የሃሰት መረጃዎችና አሉባልታዎች እንዲጠንቀቅ ግብረ ሃይሉ እየገለጸ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በማድረግ ከተፈተሙ የወንጀል ድርጊቶች ጋር በተያያዘ ተካታታይ መረጃዎችን ለህብረተሰብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

የሀገር መከላከያ ÷የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ÷ ብሄራዊ መረጃ እና ደህነነት አገልግሎረት የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅነት ኤጄንሲ እና የፌደራል ፖሊስ በጋራ የሰጡት መግለጫ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30 ፣ 2011 ዓ.ም

1 Comment

  1. Shaky exhibits and do not prove anything! Professional incompetence or …….
    The integrity of the President of the Supreme court (Teklay fird bet, Meaza Ashenafi) and the new Human Rights Watch (Daniel Bekele) is around the corner.
    Millions are watching!

Comments are closed.

Previous Story

” እኔ ማን ነኝ ?! ” መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

66596558 716225795495925 660470836599193600 n
Next Story

አቶ መላኩ አላምረው ለዶክተር አቢይ አህመድ የሰጠው አጸፋዊ ምላሽ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop