” እኔ ማን ነኝ ?! ” መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

” ፈጣሪዬ እኔ እንደነሱ ማልጓጎም አልችልምና አንተው ራሥህ አልጎምጉምልኝ።” የአንድ አርሶ አደር ፀሎት
” ያለማወቅን ማወቅ ፣ለማወቅ ብቸኛው መንገድ ነው።”

የፈላስፎች ጥቅስ

ሰው” እኔ ማን ነኝ?” ብሎ መጠየቅ የጀመረው መቼ ነው?የጠየቀውስ መቼ ና የት ነው?ጥያቄውን እንዲጠይቅ ያደረገው ገፊ ኃይል ምንድ ነው ?በግለሰብ ደረጃ  የሚያረካ መልሥሥ አግኝቷል ወይ???

ሰው  ጥንተ ፍጥረቱን የሚያሥረዳ መታወቂያ ለማግኘት ብዙ ርቀት ተጉዞ ምርምር አድርጓል።አፋዊ ምርመራ ና ትንተና በመሥጠት “ሀ” ብሎ በመጀመር።  ለጠየቀውም ጥያቄ አከራካሪ ና ዛሬም የሚጠየቅ ምላሽ የሚፈልግ የቀድሞውን ጥያቄ የሚያለዝብ መልሥ በመስጠት።

ይህ የመጠየቅ እና በተመሥጦ አሥቦ የመመለሥ ብቃት ሃሳቢውን ግለሰብ ፈላስፋ ሲያሰኘው፣ክዋኔውንም ፍልሥፍና አሰኝቶታል።ፍልስፍና የመጠየቅ ና ጥያቄውንም በአሳማኝ መንገድ “በሎጂክ” የመመለሥ እና መልሱንም እንደገና የመጠየቅ ሳይንሥ ነው።

ሌላው ከፍልሥፍና በተፃራሪ ያለ ሣይንሥ ” ማየት ማመነው” የተባለ ሣይንሥ ነው። አንድ እና አንድ ሁለት መሆናቸው  ብቻ ሣይሆን አንድ ራሷ  ቢሊዮን ቦታ ተቆራርጣ ያላትን መጠን በተጠባጭ የሚገልፅ ሣይንሥ ነው።

ይህንን  በሂሣብ ፣በፊዚክስ፣ በባዮሎጂ፣ በኬሚሥትሪ፣ወዘተ በተባሉ ፣አይቶ በማመን የዕውቀት ዘርፎች አማካኝነት የሚገለፀውን ሣይንሥ፣ ሰው ተጠቅሞ ማንነቱን ለመረዳት እየጣረ ፣እግረ መንገዱን ኋላ ቀር አኗኗሩን አዘምኗል።

ይህቺ ዓለም በታላቁ ፍንዳታ “a great  big bang ” ነው የተፈጠረችው ፣ ብሎ የሚያምነው ሣይንሥ በሥልጣኔ በደመቀው ሀገር  የዚህን እውነት ለማሥረዳት የሚችል   ግዙፍ  የምርምር ተቋም ፈጥሮ እየተመራመረ ይገኛል።

ሰው የራሱን አፈጣጠር ለማወቅ ዛሬም በምርምር ላይ ነው።በሣይንሣዊ መንገድ ሰው ሥለራሱ አፈጣጠር እስከዛሬ ቁርጥ ያለ መልስ አላገኘም።ከዳርዊን ጀምሮ ብዙ ሣይንቲሥቶች የራሳቸውን መላምት በማቅረብ በመላምታቸው መሰረት  ሥለ ሰው አፈጣጠር በተጨባጭ ለማወቅ ጥረት አድርገዋል። በሚሊዮን ዓመት ዕድሜ ያለውን ዐፅም ከከርሰ ምድር ቆፍረው በማውጣት ፣ሰው ከሚሊዮን ዓመታት በፊት በምድር ላይ ሲኖር እንደነበር መሥክረዋል።ሆኖም  ተገኘች የተባለችውን አንዷን “ሉሲን” ወይም የኛዋን በአፋር ከርሰ ምድር በአርኪዮሎጂስቶች የተገኘችውን   ” ድንቅነሽን ” ብቻ ለምሳሌ ብንወሥዳት ሰውን የመሰለ ቅርፅ አላት እንጂ ፍፁም የዛሬውን ሰው አትመሥልም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሙስሊሙ መሪዎች የፍርድ ሂደት ለ10 ቀናት ተቋረጠ

ለዚህም ነው ፣ ሰው እኔ ማን ነኝ የሚለውን መልሥ ለማግኘት ዛሬም በሣይንሣዊ መንገድ በመጣር ላይ የሚገኘው።

እርግጥ ነው ፣ሣይንሥ በየጊዜው መላምቶችን የሚያሥቀምጥና የመላምቶቹን እውነትነት ለማጣራት ያላሠለሰ ምርምር የሚያደርግ ነውና ነገም በምርምሩ ሌላ ለጆሮ እንግዳ ነገር እንደሚያሰማን እንረዳለን። እኔ ማነኝ?ኬትስ መጣው?ማን ፈጠረኝ? የሚለውን ጥያቄ በተጨባጭ ለመመለስ ለሳይንሥ ከባድ ነው።

ይሁን እንጂ ሰው፣ሳይንሥን በመጠቀም ሰለሰውና ሥለምድር ውሥጣዊና ውጫዊ ተፈጥሮ በጥልቀት አጥንቷል።በጥናቱ፣በምርምሩ ና በፈጠራው፣ይኽቺ ምድር ጠፊ መሆኗን ተገንዝቧል።እናም ማምለጫውን እየፈለገ ነው። በጠፈር ላይ ባሰማራቸው ሳተላይቶች አማካኝነትም የአሁኗን ምድር የመሰለች ፣ ፕላኔት በጠፈር ውሥጥ ትኖራለች ብሎ ፣ፍተሻውን አጠናክሮ ቀጥሏል።

በ2050 ይህንኑ እውነት ማረጋገጥ እንደሚችልም ተስፋ አድርጓል።በ2050 እጅግ በጣም የሚደንቁ በአየር ና በምድር የሚንቀሳቀሱ በኤሌትሪክ የሚሰሩ አውሮፕላኖችና መኪናዎች እፈጥራለሁ ብሏል።ከዚህም በላይ  ሰው እጅግ የተራቀቁ የጠፈር መንኮራኩሮች በ2050  ይኖሩታል።

እኛ እዚህ በሀገራችን በነኤጄቶ፣ቄሮ፣ፋኖ ና ዘርማ ሥም ፣ዛሬም “ከለውጡ በኋላ” ወደ ነውጥ  ለመሄድ ና ሀገርን በማፈራረሥ ህዝብን ወደ ከፋ ድህነት ውሥጥ ለመዝፈቅ ፣በህቡ እና በግልፅ ” ያለአንዳች ህጋዊ ፈቃድ  ተደራጅተን ” አውቀንም ሆነ ሳናውቅ  ፣ ከትላንትናው በባሰ መንገድ ፣የታሪካዊ ጠላቶቻችንን የዘመናት ህልም ለማሳካት ፣ በቋንቋ በዘር፣በጎሣ በመንደር ተደራጅተን እርስ በእርሥ እንናቆራለን።

ከመናቆርም ባሻገር ሰው መሆናችንንም ክደን፣በቋንቋ አማካኝነት ላገኘነው ሥልጣን ሥንል  “በታላቅ ግብዝነት” እንደ ባቢሎን ግንበኞች ባለመደማመጥ ሥንባላ፣በዕውቀት የበለፀጉት አገሮች ይህቺ ምድር እንደጨርቅ ከመጠቅለሎ በፊት ፣ሌላ መጠጊያና ፣ህይወትን ማሥቀጠያ ዓለም ለማግኘት ያለእረፍት ሲጥሩ እናሥተውላለን። (በእኛ ሞኝነት ሆዳቸውን ይዘው እየሳቁ።)

ተጨማሪ ያንብቡ:  ራዕይ ነበረው፣ ተቀጥሎበታልም።

እንደነሱ ፣ እጅግ በመጠቀ ቴክኖሎጂ ታግዞ ሥለጠፈር መመራመርና ሌላ ምድር መፈለጉን ባንታደል፣” በጠበቀ እምነታችን”  እንዴት ፣ የፈጣሪያችን ናት የምንላትን ምድር ፣በኃይማኖታችን አግባብ በመረዳት፣ ሁላችንም በፈጣሪ የተገኘን የአንድ እናት ና የአንድ አባት ልጆች መሆናችንን ለመገንዘብ ያቅተናል???

እኔ ማን ነኝ ?ማን ነው በመጀመሪያ  የፈጠረኝ ? የሚለውን ጥያቄ  በሃይማኖታዊ መንገድ  መመለስ ከባድ ባይሆንም እንደው በከንቱ ቤተ ክርሥቲያን ፣መሥጂድ ና ሌሎች ቤተ እምነቶች እየሄድን እንጂ የሁላችንም ፈጣሪ አንድ መሆኑን ማመን ከቶ እንዴት ይሳነናል???

ሰው የማንነቱ ጥያቄ በዓለማዊና በፍልሥፍናዊ መንገድ ሲታይ የመክበዱን ያህል በሃይማኖት መነፅር ሲታይ  እጅግ ቀላል ሆኖ ሣለ፣ለምን እምነተ ቢሥ ሆኖ፣ በሚገርም ሁኔታ  በማሥመሰል የተካነ ኃይማኖተኛ ሆነ???

እንደሚታወቀው የሃይማኖት እውነት ማመን ብቻ ነው። ያለአንዳች ማንገራገር የዕምነቱን የተፃፈና ያልተፃፈ የማንነት መልስ መቀበል ና በጥቅሉ “ሰው የፈጣሪ ፍጥረት መሆኑን ማመን ነው።

ሰው ፈጣሪ የሰራው ሸክላ ነው።” ብሎ ማመን ነው።እናም ሸክላ ነህና ፈጣሪህን  እግዜር ወይም አላህን መጠየቅ አትችልም። ያአንተ ኮፒዊተር ለምን እንዲህ አርገህ ሰራኸኝ ብሎ እንደማይጠይቅ ሁሉ አንተም ፈጣሪህን የመጠየቅ ማንነት የለህም።ማንነትህ ፈጣሪህ ብቻ ና ብቻ ነው። ይህንን የእምነት እውነት በምርምር እደርስበታለሁ ማለትም አትችልም።

ከቶም የምታመልከውን ፈጣሪህን ልትመረምረው አትችልም።ኃይማኖታዊ መፅሐፍቶችም ይህንን ይመሰክራሉ። የአንተ እና የእኔ፤የእሷ ና የእነሱ ግዴታ ሃይማኖታችን ስለሰውነታችን የሚገልፅልንን በፍፁም ልባችን እውነት እንደሆነ ማመን ብቻ  ነው።ካላመንን ሃይማኖቴ ነው ማለት አንችልም።ከተከራከርን እና ሃይማኖታችንን ከተጠራጠርን ደግሞ እምነታችን ከንቱ ነው።

መስጂድ፣ቤተክርስቲያን፣ሙክራብ፣ እንዲሁም የተለያየ ማምለኪያ ሥፍራ መመላለሳችንም ለታይታ ነው። ለታይታ ተመላላሽ ሰዎች፣  የፈጣሪን   መኖር ክደው፣በውስጣቸው ምንም እምነት ሳይኖር፣ ለድብቅ አላማቸው ስኬት ሲሉ  በየሃይማኖት ተቋማቱ ነጋ ጠባ የሚመላለሱ ናቸው። ፈጣሪ ኩንን   ድርጊታቸውን እያየ ብቻ ፣ሳይሆን ሃሳባቸውን እያወቀ ዝም የሚላቸው፣ ለምንድነው?የሚሉ ጠያቂዎች ቢኖሩም ፣ “ፍጥረቱን እንደፍጥርጥሩ የማኖር መብት ያለው እርሱ ነውና ዕድሜ ሥጠን  እያላችሁ የሱን እንከን አልባ ሥራ ለመመልከት ናፍቁ እንጂ በሐጢያተኞች አትቅኑ። እላችኋለሁ። “የሐጥያት ደሞዙ ሞት ነውና !”

ተጨማሪ ያንብቡ:  በእውቀቱ ስዩም ስለ ድምፃዊዉ ኢዮብ መኮንን

ደሞም  በዕምነት ተቋማቱ  እንደሚያምኑ ለማስመሰል ዘወትር  መመላለሳቸውም፣  ቀድሞ የነበራቸውን የሃይማኖተኝነት መታወቂያ ላለማጣት የሚከውኑት አሳዛኝ የማሥመሰል ድራማ መሆኑን ተገንዘቡና እዘኑላቸው።

ፈጣሪያቸውን በሚያመልኩበት  የሃይማኖት ተቋም እንደነሱ የሚመላለሱ፣በሥራ የተተረጎመ እምነት ያላቸው፣ የሃይማኖቱ ቤተሰቦች ”  ምን ይሉኛል?ከዕድር፣ከሰንበቴ፣ከማህበር፣ከጥዋቸው ፣ባሥ ሢልም ከጉርብትናቸው ቢያገሉኝስ???” በማለት ነው፣በትወናው  የሚገፉበት ና — ሊታዘንላቸው ይገባል።

አንዳንዶችም፣  በየዕለት  ኑሯቸው፣ ስለማይኖሩበት የፅድቅ መንገድ ያለመታከት ሲያወሩ ና የሃይማኖቱ ተቆርቋሪ መሥለው ለመታየት የሚጥሩ ሆነው እናገኛቸዋለን። ይህ ድርጊታቸው ፣ ምን ያህል የስነ ልቡና ችግር እንዳለባቸው ያሰብቃል። ጥቂት የማይባሉትም ጨርቃቸውን ያልጣሉ እብዶች መሆናቸውን ድርጊታቸው  ይመሰክራል።

እንደነዚህ አይነቶቹ ሰዎች ሳይጠይቁ የመቀበልን፣ የሃይማኖት ቀኖና እና ዶግማ ተከትሎ መጓዝን በውስጣቸው ገድለውታል። ፣በዓለም ና በመንፈሳዊ ህይወት መካከልም   በከንቱ የሚዳክሩ ናቸው። “እኔ ማነኝ?” የሚለውን መልሥ ከኃይማኖታቸው   ለማግኘት እንዳልቻሉ መንቀዠቀዣቸው፣ ለውሸት፣ ለሌብነት፣ ለማወናበድ፣ለመሥረቅ፣ለመዝረፍ ና ለመግደል ያለማመንታታቸው ይመሰክራል።

የእኛ ሰው፣እጅግ የቀለለውን የኃይማኖት እውነት እንኳን ያልተገነዘብ ምሁር ነኝ ባይ ይበዛበታል። ያልተማረውማ እምነቱ ጠንካራ ነው።በግእዝ ባያሥቀድሥ እና ከቅዳሴው ጋር ህብረት ባይኖረው “እኔ እንደቄሶቹና እንደ አንዳንድ የተማሩ መዕመናን ማልጎምጎም ሥለማልችል አንተው አልጎምጉምልኝ ” ይላል።ይህንን እውነት በመናገሩ ብፅእናውን ያገኛል። (በነገራችን ላይ ይሄ እውነተኛ የግለሰብ ንግግር  ነው። ይህንን ያሉት አንድ  ፊደል ያልቆጠሩ አርሶ አደር ፣በአንድ የገጠር ቤተክርሥቲያን  ለፀሎት ተገኝተው መሆኑ እርግጥ ነው።)

 

Share