June 22, 2019
1 min read

አስቀያሚው የኢሕአዴግ ድራማ የሽፍጥ ፖለቲካ

95733

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ላይ መፈንቅለ መንግስት ተደረገ የሚል የፌዴራል መንግስቱ ድራማ ሴራ የተቀላቀለባት መሆኗ ነጋሪ አያሻም። የክልሉ መንግስትና በባህር ዳር ያሉ ሚዲያዎች ሳይናገሩት የፌዴራል መንግስት ተዘጋጅቶ ይጠብቅ የነበረውን መግለጫ መስጠቱ የሽፍጥ ፖለቲካው አካል ለመሆኑ ምስክር አያሻውም። የመከላከያ ሰራዊት ዝግጁ ሆኖ በሰዓቱ በቦታው መገኘቱና ለተለያዩ ሃገራዊ ጉዳዮች መግለጫ ለመስተት አሻፈረኝ የሚሉ እነ ንጉሱ ጥላፉን በብርሃን ፍጥነት ስለመፈንቅለ መንግስት መደስኮራቸው የተሴረውን ተንኮል ፍንትው አድርጎ ያሳያል። መመታት መገደል መታሰር ያለባቸውን አፋፍሶ ለማሰር ያልተመቸው የፌዴራል መንግስቱ የወጠናት ሴራ መሆኑን ማንም የፖለቲካ ተንታኝ አያስፈልገውም። ኢሕአዴግ በእንዲህ አይነቱ የፖለቲካው ድራማ ይታወቃል። ይህንን ሴራ ተከትሎ በቁጥጥር ስር የሚውሉትን ኢሕአዴግ ጠላት ብሎ የፈረጃቸውን ሰዎች በመመልከት ብቻ በመፈንቅለ መንግስት ስም የጦዘውን ድራማ ውጤት ማረጋገጥ ይቻላል።

ምንሊክ ሳልሳዊ

5 Comments

  1. በዚህ እለት ይህንን ቅርሻት ስትለቀልቅ ትንሽ እንኳ አታፍርም:: ክርስቶስ ይታረቅህ:: ለአንተ ሚጢጢ ጭንቅላት የተገለጠው ለብዙዎቻችን አልተገለጠም ማለት ነው?

  2. ይህ የፖለቲካ ድራማ በሰውህይወት የቀለደ ሰፊውን ሀዘብ ለማሞኘት የተከወነ ግን በሃሰት የታጀለ የሴራ ፖለቲካ ውጢት ነው። ነገ ፀሃይ ትወጣለች እውነት ይገልጣል ሁሉም ፍርዱን ይቀበላል። የ አንድን ፓርቲ ሪፓርት ብቻ ሰምተን ለፍርድ የምንቸኩል ሞኞች ሙሆን የለብንም ምክንያትም ብዙ እውነት የማይመሰሉ ከስተቶቸ እያሰማን ስለሆነ ና በጣም ፈጣን ዜና የተሰራበት ነው።

Comments are closed.

Previous Story

ኢዜማ የሚወዳደረው አሜሪካና ካናዳ ነው እንዴ? – ሰርፀ ደስታ

95764
Next Story

“የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው ለአገራችን የማይመጥን ነው።” – አምባሳደር ትርፉ ኪዳነማርያም

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop