June 19, 2019
16 mins read

ትግራይ ማለት ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ማለት ትግራይ ናት፡ – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ኢትዮጵያ ትግራይ ትግራዋይ ኢትዮጵያ ነው
” በይ ደህና ሰንብቺ …አልተገናኘንም
ቻው!ቻው!  ደህና ሰንብቺ…ደብረ ፅዮንም፡፡
‘አልተገናኝቶም ‘ ባይ!ባይ! ነጋሽ መሥጂድ
ጠፍቷል በወያኔ ሰው ሆኖ ሰው መውደድ፡፡
ቋንቋ ናችሁ ብሎናል…ሰው ከቶ አይደላችሁም
አልነበረም እንዴ የሰው ሀገር…በዘመኑ አክሱም ?”
እያልን… ስንሞገት
ስንጮኽ… ለሰውነት
“ጉንደት ጉንዳጉንዴ…ዶጋሊ፣አባላጌ፣ ይቅሩና
የመቀሌው ተጋድሎ…የአደዋው ድል ይረሳና…
በኃይል እንገንጥላት…ትገራይን ከእናቷ
ጥቂቶቻችንን ከልጠቀመች ኢትዮጵያ ምን አባቷ !
ተፋቅረን፣ተዋደን፤ ተሻርከን ፣ከኤረትራ ጋር
እንሆናለን እኛ ወደብ ያለን – ሀብታም ሀገር፡፡…”
የሚለውን ዜና የሰማነው በህለማችን ይሆናል…
ኢትዮጵያዊው  ከኢትዮጵያ፣ ከቶስ እንዴት ይገነጠላል ?
“በሥመ አብ !” “ቢስሚላሂ !” ያሰኛል “ሆቸው ጉድ!”
“እገነጠላለሁ በል!” ህዝብ ሲባል በግድ ፡፡
ኩሩውን ኢትዮጵያዊ ፤”እንገንጠል!” ሲለው
ምንው አጣ ጎበዝ ፣አፉን የሚያሲዘው?
አኩሪ ታሪካችንን ፣በዋዛ ለመደምደም
የግል ሐሳቡን በአደባባይ ሲያወራ በህዝብ ሥም
ዝም ብለን አናዳምጥ ፣እውነቱን እንንገረው
ኢትዮጵያ ትግራይ፤ትግራዋይ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡
   ሰኔ 8/2011 ዓ/ም መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
የትግራይ ህዝብ በእውኑ  በገሃዱ ዓለም ውስጥ ሆኖ ይቅርና በህልም እና  በቅዠት ዓለም ውስጥ ሆኖ  እንኳን ቢሆን የማይናገረው  የድፈረት ቃል ቢኖር ” ከኢትዮጵያ እንገነጠላለን ፡፡”የሚለው መሆኑን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡፡ይህንን ፀያፍ ቃል ፣ ለታሪክ ደንታ የሌላቸው ሀገርን ለማሰከበር ሳይሆን ኪሳቸውን ለማስከበር የሚኖሩ ግለሰቦች ሺ ጊዜ በመደጋገም ሊናገሩት እንደሚችሉ ግን ማንም አያስተባብልም፡፡
      የትግራይ ህዝብ ግን እንደ ህዝብ በህልሙም በእውኑም የሚያስበው ሥለ ኢትዮጵያ ታለቅነት እንጂ ኮሥሣነትና አቅመ ቢስነት ከቶም አይደለም፡፡
     ማንም ሀገር ወዳድ ፣ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ሥለ ኢትዮጵያ ብልፅግና ሲያወሳ ሥለ ትግራይ ህዝብም ብልፅግና እና ልማት ጭምር እያወሳ መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ሥለ አትዮጵያ ህዝብ ጀግንነት እና ኩራት ሲያወሳም ሥለትግራይ ህዝብ ጀግንነትና የተጋድሎ ታሪክ ማውሰቱ እነደሆንም ማስተባበል አይቻልም።
  ያ የኢትዮጵያችን ክልል ለብዙ  ዓመታት የጦርነት ቀጠና ሆኖ እንደኖረ እና ኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንዳቸውን ጠላቶቻቸው ላይ በማሳረፍ ተደጋጋሚ ድልን የተጎናፀፉበት የጦር አውድማ እነደነበር መዘንጋት ከቶም የለበትም፡፡
     የትግራይ ህዝብ በግሉም፣ለዘመናት የባህር በር ጠባቂ በመሆን እንደኖረ ፣የጥንቱ ባህረ ነጋሽ (የአሁኑ የቀይ ባህር ስያሜ ነበር፡፡ ) ባለቤትም እንደነበር ማስታወስ ቅዠታሞቹን ከቅዠታቸው እንዲነቁ ያደርጋቸዋል ፡፡የትግራይን ህዝብም ሆነ የኢትየጵያን ህዝብ ከድህነት እነዳይወጣ ያንን የመበልፀጊያ ምነጩን ያሳጡት ለፍርፋሪ አድረው፣ ለነጭ ባንዳነት ተገዝተው፣ ያደሩ “ከራስ በላይ ነፋስ!” ባይ ፣ ሆድ አደር የሆኑት ወንድሞቻችን እነደሆኑ ከራሱ ፣ከትግራይ ህዝብ የተሰወረ ከቶም አይደለም፡፡ይህ ኩሩ እና ጀግና ህዝብ አሁን ያለችንንም ሀገር ያተረፈልን በየዘመናቱ ከባንዶች ጋር እየተናነቀ መሆኑንንም ወደኋላ ተመልሶ ከታሪክ መዛግብት መረዳት ተገቢ ይመስለኛል ፡፡ ይህንን ፈጽሞ  ባለመረዳት ፣እነሆ ዛሬም አንድ በህመም የናወዘ ትግራዋይ   ታሞ እነኳ በቅዠት ውስጥ  የማያስበውን “ከኢትዮጵያ የመንገጠል” ሃሰብ ፣ መሞታቸውን የዘነጉ ና ለታሪክና ለህዝብ ደነታ ቢስ የሆኑ የምቾት ና የድሎት አመላኪዎቹ “ልተገነጠል አስበሃል፡፡” በማለት ከቶም ያላሰበውን  እየነገሩት ነው፡፡ይገርማል፡፡     የሚገርመው ነገር የትግራይ ህዝብ “በወያኔ” አገዛዝ ጠብ ያለለት ነገር ሳይኖር፣ዛሬም አፈር መስሎ ከአፈር ጋራ እየታገለ መኖሩ እየታወቀ፣መሰረታዊ ፍላጎቱን እንኳ ያላሟሉለትን ምሥኪን ህዝብ ፣ ልክ እንደደላውና ሙቅ እንደሚያኝክ በመቁጠር፣ “ሊገነጠል አስቧል፡፡” መባሉ ነው።
      ዛሬም የትግራይ ህዝብ እንደተቀረው ወገኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ፣በከፋ ድህነት ውስጥ ነው እየኖረ ያለው፡፡መሰረታዊ ፍላጎቶቹ አልተሟሉለትም፡፡በቂ ፣ምግብ፣መጠለያ ና ልበስ የለውም፡፡ብዙሃኑ ደኸይቶ ጥቂቶች ስለተተረፈረፋቸው የትግራይ ህዝብ በወርቅ ፈራሽ ላይ እየተኛ ነው ብሎ ማውራት በቁም እንደ መቃዠት ይቆጠራል፡፡ በቅዠት ውሥጥም ሆኖ  ሥለመገንጠል ማውረት ፣በመላው ኢትዮጵያ ከተሞች ተፋቅሮ፣ተዋዶና፣ተጋብቶ ና ተዛምዶ የሚኖረውን የትገራይ ተወላጅ የሆነን ኢትዮጵያዊ ዜጋ ስጋት ውስጥ መጨመር ነው፡፡ትላንትና የኤርትራ ተወላጅ ወንድምና እህቶቻችን ከኢትዮጵያ ውጡ ሲባሉ ያነቡትን ደም እንባ ከቶም የምንዘነጋው አይደለምና ይህንን  ታማሚ ና ቅዠታም ሰው እንኳን የማያስበውን “የሴጣን ጆሮ አይስማው። የሚያሰኝን አፈራሽ ሃሰብ አንድ ኃላፊነት ያለበት ሰው መናገሩ በእጅጉ የሚሳፍር እና የሚሳዝን ነው፡፡
     ይህ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይበቀል ፡፡” በማለት ፣ለእኔ ያልተመቸችኝ ኢትዮጵያ ለምን 80 ሀገር በመሆን አትሸነሸንም በማለት፣ካለፉት ቅኝ ገዢዎቻችን በከፋ መልኩ ሥለኢትዮጵያ መበታተን አጥበቆ ወይም ተግቶ መስራት ነውና ልናወግዘው ይገባናል፡፡
    አባቶቻችን ህይወታቸውን ሳይሰስቱ ፣ለእኛ ክብርና፣ኩራት ፣በታለቅ የሀገር ፍቅር ሥሜት ተሰውተው ፣በደማቸው ያቆዩንን ሀገር፣እንደዋዛ ስትፈራርስ፣መመልከት እጅግ አሳፈሪ፣አስጠሊና አሳዛኝ ውርደት ነው፡፡ይህንን ውርደት ከምናይ ከባንዶች ጋር ተናንቀን መሞት ለእኛ ዘላለማዊ ክብር ነው፡፡
ይህቺ ሀገር እንደው እንደዋዛ እዚህ ደረጃ እንዳልደረሰችም የመናስመሰክረው ዛሬም ፣የትላንትናዎቹ ጀገኖች አባቶቻችን ደም በውስጣችን እንዳለ በተግባር ስናስመሰክር ብቻ ነው፡፡ይህቺ ሀገር እኮ እንዲሁ እንደዋዛ ኢትዮጵያ እየተበለች ለዛሬ አልበቃችም።
     ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እየተባለች ለዛሬ የበቃችው በትላንትና ልጆችዋ መሰዋትነት ነው፡፡ኢትዮጵያ የሚለውን ስያሜዋን ፣ከታሪክ ገፅ ለማጥፋት በሁሉም ዘመናት  የልተሸረበ ሤራ እነደልነበረ ታሪክ ይነግረናል፡፡ዛሬም በ 21ኛው ክ/ዘ ይህ የጠላቶቻችን ሴራ በረቀቀ መልኩ እየተከናወነ ነው፡፡ዓለም በስልጣኔ እየገሰገሰ በሚሄድበት ወቅት የእኛ እርስ በእርስ መነካከስ የሴራውን ተከታታይነት ያሣብቃል።
 ዓለም በሥልጣኔ በገሰገሰበት በ21ኛው ከ/ዘ እኛ ገና እንደ ጥንት ኃይማኖት አለባ ህዝቦች በቋንቋ ልዩነት ብቻ፣ጠመንጃ አንስተን በመገዳደል ላይ ነን፡፡ይህ ድርጊታችን ሰውን በሰውነቱ ብቻ ተቀብለው በሚኖሩ የዓለም ህዝቦች ዘንድ መሳለቅያ አድርጎናል፡፡ አንድ አንድ ወዳጆቻችንም “የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው፡፡” በሚል መርሃቸው መታለባችንን ብቻ ነው የሚፈልጉት፡፡ የእኛ መበላላትም ሰርግና ምላሻቸው የሆኑ እንዳሉ መዘንጋት የለብንም፡፡
    የጠበቀ ወዳጅነት ከቻይና ጋር ቢኖረንም ቅሉ፣የቻይናን ኮሚኒስት ፓርቲ ውሥጥ ያለው ከብረት የጠነከረ ዲሲፕሊን” በእኛ ፖለቲካ ውስጥ እነዲሰርፅ ባለማድረጋችን  እንደቻይና ህዝብ በአጭር ጊዜ ለመበልፀግ አልቻልንም፡፡
     የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ፣በማኦ ዘመን ያደረገውን ኩንን ተግባር ምዕራብውያኑ ቢያወግዙትም፤ ባራቀውም ጊዜ በቲያሚን አደባባይ የቻይና ወጣቶች እንደቅጠል ቢረግፉም ቅሉ … ቻይና  ዜጎቿ ሰው እና ቻይናዊ መሆናቸውን አውቀው ለሀገራቸው ጥቅም ሲሉ  ለመሰዋት ወደኋላ እንዳይሉ ከልጅነታቸው ጀምሮ በማሰተማር ሀገር አፍቃሪ ተውልድ መፍጠሯን ዓለም የመሰክርላታል፡፡እኛስ?
    እኛማ ዛሬም እንዳልሰለጠነ ህዝብ ሰውነታችንን በመካድ ፣ “እኔ ቅብርጥስዬ !አንተ ቅብርጥስዮ !ነህ።” እየተባባልን ፣ እንደ አውሬ እንበላላለን፡፡ (በአንድ ከተማ የሚኖር ድብልቅ ህዝብ ላይ አንድ ቋንቋ ተናጋሪ ፈላጭና ቆራጭ እንዲሆን በማድረግ የህግ የበላይነትን፣ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብትን ገደል እንከታቸዋለን፡፡ ከተሞች በኗሪዎቻቸው እንጂ በቋንቋ እንዴት ይስተዳደራሉ? ይህ አንዱን ቋንቋ አግዝፎ ሌሎቹን  ማንኳሰስ            አይደለም እንዴ? በዚህ ኢ ፍትሃዊ አሥተዳደርሥ የሚጎዳው አገልግሎት ፈላጊው ኗዋሪው ዜጋ መሆኑ መንግሥት አይገነዘብም ለማለት እንዴት ይቻላል???።)
 እርግጥ ነው። ነገ እኛ 80 ቦታ ብንሸነሸን ቻይና ጉዳዮ አይደለም ፡፡የኢኮኖሚ አቅም ስላላት ከ80 ዎቹ ጋር ተሸርካ ጥቅሞን ታስቀጥላለች።፡፡መጥኔ ለእኛ እና የታሪክ አተላ ላደረጉን ጥንባሳዎቻችን፡፡
     ዛሬ፣ዛሬ በየአቅጣጫው የታሪክ አተላ ለመሆን የሚሯሯጠው በዝቷል፡፡ጀግንነት ማለት እሰከ ህይወት መሰዋትነት ድረስ እነኳ ቢሆን ትልቅ ዋጋ በመክፈል ለሀገርና ለህዝብ ፋይዳ ያለው ቁም ነገር መስረት መሆኑ ተዘንግቷል፡፡በተገላቢጦሽ ሥንትና ሥንት ኢትዮጵያዊያን ታለቅ መስዋትነት ከፍለው ያቆዩልንን ሀገር፣ለማጥፋት ያለእረፍት የሜያሴሩ ጉዶች በጉያችን ተፈጥረዋል፡፡የህቺ ሀገር በጽዱ አጆቻቸው           በሚታወቁ፣ሌባ፣አጭበርባሪና ዘራፊ ባልሆኑ ፣በላብአቸው ፍሬ በሚደሰቱ ህዝቦቿ ትላንት እንደቆመች ሁሉ ዛሬም ያንን ማድረግ እነደማይሳነት ግን አለተገነዘቡም፡፡…ታሪክ እንደሚመሰክረው፣ “የኢትዮጵያ አምላክ ይፈርዳል ፣ ሳይውል ሳያድር ፡፡…”
 እናም፣ዛሬም የትግራይ ኩሩ ና ጀግና ህዝብ እንኳን በእውኑ በህልሙ የማየስበውን የቁም ቅዠታቸውን በትግራይ ህዝብ ላይ ለማጋበት ወይም ለማላከክ ቀና ደፋ የሚሉትን ፣የኢትዮጵያ አምላክ ሳይውል ሳያድር እንደሚፈርድባቸው አትጠራጠሩ፡፡

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop