October 31, 2018
5 mins read

ዶ/ር አብይ አህመድ “ኢትዮጵያ ማንም ትነስቶ እንደግል ቂጣ እንደፈለገው ጠፍጥፎ የሚጋግራት አይደለችም” አሉ

92273

(ዘ-ሐበሻ) ከአውሮፓ ከተውጣጡ ኢትዮጵያውያን ጋር ለመወያየት ወደ ጀርመን ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በፍራንክፈርት ኮሜርዝ ባንክ አሬና ስቴድየም ለተሰበሰቡ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት ንግግር “”ኢትዮጵያ ማንም ትነስቶ እንደግል ቂጣ እንደፈለገው ጠፍጥፎ የሚጋግራት አይደለችም” ሲሉ ተናገሩ::

“አሁን ያላየነውን የምናይበት፤ ያልሞከርነውን የምንሞክርበት ጊዜ ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ኢትዮጵያ ማንም ተነስቶ በወደደው ልክ እና ፍላጎት እንደ ቂጣ የሚጠፈጥፋት ሳትሆን ታላቅ ህዝብ የመሰረታት ታላቅ ሀገር ናት” ሲሉ ሕዝቡ በሆታና በጭብጨባ አስደግሟቸዋል::

“ሀገሬ አንቀላፍታ ይሆናል እንጂ አልሞተችም:: ኢትዮጵያ ደክማ ይሆናል እንጂ አልተሸነፈችም:: እምዬ ቀጥና ይሆናል እንጂ አልተበጠሰችም” በማለት ሕዝቡን ስሜት ውስጥ የከተተ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር አብይ ባለፈ ታሪክ ሕዝብ መነታረኩን አቆሙ “እኔ ለሀገሬ ምን ሰራሁ እንጂ እነእገሌ ሀገሬን ጉድ ሰሯት ከማለት ጠብ የሚል ነገር የለም፡፡
” ማለት እንዲቆም ጠይቀዋል::

በሃገሪቱ ውስጥ ዴሞክራሲና ሰላም ሰፍኖ ወደ አውሮፓ ቢመጡ ደስ ይላቸው እንደነበር የገለጹት ዶ/ር አብይ ሆኖም ግን በሂደት ከሕዝቡ ጋር በመተባበር ሰላምን እና ዴሞክራሲን ለማስፈን እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል::

የፍራንክፈርቱ ኮሜርዝ ባንክ አሬና ከተጠበቀው ያነሰ ታዳሚ ለተገኘበት ምክንያት አዘጋጆቹ ዝግጅቱ ረቡዕ ቀን መደረጉን እና በርካታ ሰዎች ስራ ስላላቸው ከተለያዩ አውሮፓ ሃገራት መምጣት ስላልቻሉ ነው ይላሉ::

“ሀገራችን ከአውሮፓውያን ጋር ከጥንት ጀምሮ የቆየ ታሪካዊ ትስስር ነበራት፡፡ ይህ ለዛሬው ግንኙነታችን መሰረት ጥሏል፡፡ ጀርመናውያን በዓለም ጦርነት ወድማ የነበረችውን ሀገራቸውን መልሰው ለመገንባት የወሰደባቸው ከ40 ዓመታት ያልበለጠ ጊዜ ነው፡፡ አውሮፓውያን እርስ በርስ ከመሸናነፍ ይልቅ ድህነትን ማሸነፍ በመምረጣቸው ዛሬ እዚህ ደርሰዋል፡፡ ይህ ለኛ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ትምህርት ይሰጠናል፡” ያሉት ዶ/ር አብይ “ኢትዮጵያዊነትን ከስሜት በዘለለ በስራ የምንገልፅበት ወቅት ላይ ነን፡፡

“ጠንክረን ካልሰራን ፍትሕና ዴሞክራሲ እንዲሁ አይመጣም፡፡ ተደምረን ተግተን ስንሰራ ብቻ ነው ይህ እውን ሊሆን የሚችለው፡፡ ለዚሁ ዓላማ ተቋማትን በመገንባት ኃላፊነታቸውንም በአግባቡ የሚወጡ ሰዎች በመመደብ ላይ እንገኛለን፡፡” ያሉት ዶ/ር አብይ “በምርጫ ቦርድ፣ መከላከያ፣ ፍትሕ፣ ትምህርት ወዘተ ተቋማት አስፈላጊውን ማሻሻያ በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡” ብለዋል::

“በቅርቡ በፍትሕ ዘርፉ ላይ ወሳኝ የሆኑ የማስተካከያ እርምጃዎች እንወስዳለን፡፡ ለነገው ትውልድ የምትሆን ኢትዮጵያን የመገንባት ፈታኝ ስራ ከፊታችን ይጠብቀናል፡፡” ያሉት ዶ/ር አብይ “እንደ ደቡብ ኮሪያው ጄነራል ፓርክ የወር ደመወዛችሁን አስይዛችሁ እንድትበደሩልን ሳይሆን በቀን ከአንድ ማኪያቶ 1 ዶላር እንድትሰጡን በድጋሚ እንለምናችኋለን፡፡” ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል::
https://www.youtube.com/watch?v=pkxOggM328g&t=7s

2 Comments

  1. I would like to stress that. I just observed, the majority of Ethiopian started blaming Dr.Abiy Ahmed, for the fact that when he visited Frankfurt. As usual undereducated Oromo farmers children who has been brainwashed for the last 20 years by NONE OTHER THAN TWO IDIOTS OLD FART OLF LEADER DAUD IBSA AND HIS STEP CHILD BLACK YEMENI REFUGE JAWAR MOHAMMED.

    Those undereducated, uninformed Oromo Ethiopian farmers kids sadly came with their 20 years Fake Flag to see our beloved Ethiopian transitional to democracy leader, at the same time tried to undermine Ethiopian more than 3000 years worldwide respected flag Green-Yellow-Red!

    I am here to let you know that. Dr. Abiy Ahmed nothing he could do to stop this fake flag with undereducated OLF followers parasites . However Dr. Abiy Ahmed has all the power to “BANNED OLF OROMO SEPARATIST FLAG FROM LAND OF ETHIOPIA” and brought to justice “OLD FART DAUD IBSA OROMO SEPARATIST KING OF ETHIOPIAN PEOPLE PARASITES AND JAWAR MOHAMMED” END OF STORY!!!

  2. የዶ/ር አብይ ንግግር በፍራንክፈርት ስታዲየም በርካታ ጥሩ ሃሳቦችና ለአገራችን መፂህ ጊዚ መልካምን የሚመኝ ቢሆንም በሁሉም ልብ ውስጥ የሚያጭረው ነገር አለ፡፡ ግን እንደዚህ አልጋ በአልጋ የሚሆን አይሆንም፡፡ ምክንያቱም አገራችን በብዙ ሰው ሰራሽ በሆኑ ችግሮች የተበተበች ስለሆነ ሁሉም በቅን መንፈስና ከግለኝነት በወጣ መንፈስ ለህዝቡ፣ ለቀጣይ ትውልድና ፈርዐ-እግዚአብሔር ባለው ስሜት ቀን ለሊት ሊሰራ ይገባል፡፡ አውሮፓ ውስጥ አሁን ዘንጦ መኖር የተቻለው በዛን ዘመን አገራቸውን ባስቀደሙ ትውልዶች ወገባቸው እስኪጎብጥ ቀን ለሊት ሰርተው እንደሆነ አይዘነጋም፡፡

    ስለዚህ የዶ/ር አብይ ተስፋ የቀድሞውን ታላቁኝ የጥቁሮች ሰብዓዊ መብት ታጋይ D/r Marthin Luther King “ I have a Dream” በወቅቱ ምፅአታዊ ትንበያና ንግግር የሚያስታውስ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝብም ከዚህ አንፃር ብዙ ስራ እንደሚጠበቅብን ልብ ልንል ይገባል፡፡ እስከመቼ ከአለም አገሮች በታች መሆን???

    ኢትዮጵያ ለዘላላም ትኑር!!

Comments are closed.

15
Previous Story

በአዲስ አበባ በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ 15 ተማሪዎች ራሳቸውን ስተው ወደቁ

92276
Next Story

አዲሱ የሱማሌ ክልል ፕሬዚደንቱ አቶ ሙስጠፋ ማህመድ ኡመር በክልሉ በርካታ ሰዎ በጅምላ የተቀበሩበት ጉድጓድ መገኘቱን ገለፁ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop