እስኪጣራስ – በልጅግ ዓሊ

ሃገር ውስጥ የተገኙ ዝሆኖች ሁሉ ይታሰሩ የሚል አዋጅ ይወጣል። አንድ አይጥ ከላይ ወደ ታች ትራወጣለች።  ምን ሆነሽ ነው ብለው ይጠይቋታል። በሃገር ውስጥ ያሉ ዝሆኖች ሁሉ ይታሰሩ ተብሎ የወጣውን አዋጅ አልሰማችሁም እንዴ? ብላ ትነግራቸዋለች። ታዲያ አንቺ አይጥ እንጂ ዝሆን አይደለሽ ብለው ሲጠይቋት ። እሲኪጣራስ ብላ መለስች አሉ።

እሲኪጣራ በዝሆንና በአይጥ መካከል ያለውን ልዩነት ጊዜ ይወስዳል። የተስፋዬ ገብረአብ ጉዳይም እንዲሁ ነበረ።

ልጅ ይታየዋል።

የአማርኛ ተረቶች አንዳንዶቹ እንዴት እንደተፈጠሩ ማጥናትና በጽሁፍ ማስፈር አስፈላጊ ነው። ተረቶቹ እውነትነታቸው በተግባር የተፈተነ ነው።  ብዙ ጊዜ ተረቶች ከልምድ ጋር የተያያዙ ናቸው።

በነፃ የተለቀቀልንን የተስፋዬ ገብረ አብን መጽሐፍ ሳነብ አንድ የሚገርም ጉዳይ አገኘሁ። ሰለ አንድ ማሊክ ሰለሚባል ሶማሌያዊ ሕጻን ፦

ገጽ 25 ፡ –

ማሊክ በእናቱ እንደታቀፈ አንገቱን ወዲያ ወዲህ ሲያሽከረክር እኔ ከሁዋላ ነበርኩና አይን ለአይን ተጋጨን። ልክ እኔን ሲያይ እንደገና ማልቀስ ጀመረ። እናቱ ልጇ ያለቀሰበትን ምክንያት ለማወቅ ነው መሰል ዘወር ስትል እኔን አየችኝ። ሰይጣዊ ክፉ መንፈስ እንዳየች ሁሉ እሷም ፊቷን ጭምድድ አድርጋ ዘወር አለች። እኔም ምንም እንዳልተፈጠረ መንገዴን በመቀጠሌ እናትና ልጅ ከሁዋላዬ ሆኑ።

ማሊክ ማልቀሱን አቆመ።

ልጁ ያለቀሰበትን ምክንያት ተስፋዬ የተለያየ መላምቶች አስቀምጧል።ከሰይጣናዊ ክፉ መንፈስ እስከ ሞቃድሾ እስከዘመቱት አበሾች ድረስና የሶማሊዎች በአበሾች ላይ ጥላቻ።

ተስፋዬ ስለ ማሊክ ማልቀስ ራሱ የመሰለውን ከእውነት የራቀ መላ ምት ይስጠው እንጂ በዓለም የተሰራጩ የሶማሌ ሕጻናት እኛን ባዩ ጊዜ አያለቅሱም። ስለዚህ ስለ ሃበሻ  የተሰጠው ትንታኔና ምክንያት ኩታ ገጠም አይደለም። ስለዚህም  ክፉ መንፈስ የሚለውን አጠንክረን ከሌላ መላ ምት ተቆጥበን እዚሁ ላይ እንተወው። ከላይ የጠቀስኩት ተረት ልክ ነው። ለልጅ ይታየዋል . . . ።

 

ንቆሮ የሰማ ዕለት ያብዳል። 

እንደ ዝሆኑና እንደ አይጧ ያለው ልዩነት  ተመልሶ አጀንዳ ሆኖ ሲያምሰን ከረመ። የተስፋዬ ገብረአብ ጉዳይ። መቼም ዛሬ እንዲህ የገነነበት ጉዳይ ምክንያት ይኖረዋል። እያደር መጋለጡ አይቀርም። ለትንሽ ጊዜ ኢንተርኔት በቀላል የማይገኝበት ቦታ ነበርኩ። ወደ ቦታው ከመሄዴ በፊት ስለ ተስፋዬ ገብረአብ የተገኘው መረጃ ለሕዝብ የተበተነበት ወቅት ነበር። ከሄድኩበት ተመልሼ ስመጣም ተሰፋዬ አጀንዳ ነው። ተስፋዬ እንደፈራው መድፍ አልተተኮሰበትም። ከውስጥ አዋቂ ከሆነ አገር ወዳድ የተጫረች ትንሽ ክብሪት ነች አቃጥላ የጨረሰችው። እኛም ብዙ ሲነገረን ያልገባን መረጃውን ስናይ አበድን።  ደንቆሮ የሰማ ለት ያብዳል እንዲሉ።ተስፋዬም የአጻፋውን መልስ ተኮሰ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አጨብጫቢነት ዴምሕት/ለማ ወዘተ - የመርሕ ድህነት እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ

http://tgindex.blogspot.co.uk/2013/10/blog-post.html

አንዳንዶቻችን  ሰላቢ ጸሐፊዎች ብሎ አማን። ደፍሮ ግን ሰለኔ የጻፉት ትክክል አይደለም ብሎ መጻፍ ተሳነው። ምን ብዬ እንደጻፍኩ ወደ ኋላ ተመልሼ አነበብኩት። “የማታውቅበትን . . .’’ በሚለው ጽሁፌ ላይ ትንቢት የመሰለ ጉዳይ ይገኛል።

“ተስፋዬ በአሁኑ ወቅት አንገብጋቢውን ጥያቄ መመለስ ሲያቅተው በሕይወት የማይገኙ ግለሰቦች እየጠቀሰ የተሳሳተ መረጃ ከሰጠ እኔም ባልሆን ሌሎች የሚታዘቡ ይቀጥሉታል።’’

ልክ ነው የተሳሳተ ግምት አልነበረም። ሌሎች ቀጠሉበት። በመረጃም አጋለጡት። ተስፋዬ ሁሉንም የመከፋፋያ ዘዴ ተጠቅሟል። ግን አልተሳካም። አባት ሃገሬ ብሎ የሚኮራባት ኤርትራም በቅርብ በልጆቿ ትግል ከኢሳያስ ጭቋና ነጻ ትወጣለች። እሱም ለአርባ አራቱ ታቦት የሚሳልበት የሃገራችን የእርስ በእርስ ጦርነት በጀግኖች ልጆቿ ይከሽፋል። የሃገራችን ትንታግ ጸሐፊዎች ዜጎቻችንን የሚከፋፍለውን ሳይሆን የሚያፋቅረውን የአንድነት ገድል ይጽፉታል። ሆ ብሎ የተስፋዬን ሥራ ያጋለጠው ሁሉ ሰደድ እሳቱን በቅርብ ቀን በወያኔም ይሁን በሻብዕያ ጓዳ ውስጥ ይለቀዋል። ያ ጊዜ ወዮላችሁ! ዘርን ከዘር ለማናከስ እንቅልፍ ያጡ እንኳን የሆላንድ ዜግነት መታወቂያ የሚያምኑበትም “የቆሪጥ’’ ግብር አያድናቸውም። እውነት እውነት እላችኋለሁ ጊዜው ሳይመሽ ንሰሃ ግቡ። ከሃያ ዓመት በላይ የጠበቃችሁት የርስበርሱ ጦርነት በራሳችሁ ምናብ ውስጥ ብቻ ተጽፎ ቀርቷል። ቢቻላችሁ የያዛችሁ የዘር ጋኔል ይለቃችሁ ዘንድ ከሃገራችን አዛውንቶች ጋር ቁጭ ብላችሁ ታሪክን ተማሩ። ስለአንድነት የተጻፉትንም ቢያንገፈግፋችሁም አንብቡት።

በድሉ ዋቅጅራ ለልጁ በጻፈው ደብዳቤ እንዲህ ብሎ ነበር።

 

የኔ ልጅ፣

አማራው አፋሩ ኦሮሞው ሲዳማው ፣ጉራጌኛሽ ባይሰማ፣

ያልገባው እንዳይመስልሽ ሀዘን ደስታሽን ያልተጋራ።

የየልቦናችንን ሀቅ ፍንትው አድርጎ እያሳየ

ህዝቦችን ከሰንደቃቸው አስተሳስሮ  ያቆየ፣

ሀገር ቋንቋ ነው ልጄ የሁለንተናሽ መስታወት፣

ሲከፋሽ ትሽሽጊበት ሲደላሽ ትኳኳይበት

 

የኔ ልጅ

አያት ቅም አያትሽ ፣ሰላም ሲሆን ከወልቂጤ አድማስ ማዶ ሸቅጦ፣

ሲያቀና ወረቱን

ለእኔና ለአንቺ መኖሪያ ሲያቀና ቀዬና ቤቱን

ሀገር ጠላት ሲደፍራት ጦሩን ሰብቆ እየፎከረ፣

ተጨማሪ ያንብቡ:  በካልጋሪ ከተማ የኮፈሌ ሰመአትን ለማሰብ በተደረገው ዝግጅት ላይ የቀረበ ማራኪ ግጥም - - በእዝራ ዘለቀ

ከኦሮሞው ከትግሬው ከአፋሩ ከወላይታው ከሁሉም የጦቢያ ልጆች

አጥንቱን እየማገረ

ሀገር ይሉት መግባቢያ ፣ሰንደቅ ይሉት መለያ ፣ሲያቆይልሽ

በጉራግኛ የማትገልጭው በጎጥ የማትገድቢው፣ ስንት አለ ታሪክ መስለሽ።

 

እነ በድሉ ዋቅጅራ ፣ እነ ዓለማየሁ ገላጋይ ፣ እነ ተሰመስገን ደሳለኝ ፣ እነ በእውቀቱ ስዩም . . .  ወዘተ እየገነቡ ያሉትን አንድነት ፣ እነ ተስፋዬ ንደው ይጨርሱታል የሚል እምነት የለኝም። ግና የሃገራችን ጠላቶች የሚያፈሱላቸውን ነዋይ በመጠቀም መድረኩን ሞልተው፣ በአሉባልታ ጽሁፋቸው ይታዩበታል። እውነተኛዎቹ የአንድነት ጸሐፊዎች ግን በውስጥ ወያኔ ፣ በውጭ ወያኔና ሻብዕያ በመተባበር መቆሚያ መቀመጫ እያሳጧቸው ነው። በቅርብ ቀን መስፍን ማሞ ተሰማ የገመገመውን  “ኢህአዴግን እከሳለሁ”  የሚለውን የዓለማየሁ ገላጋይን  መጽሐፍ የምናውቅ ስንት ነን? የአንድነት ተሟጋች ጸሐፊዎችን የምንረዳበት ምክንያት ስላለን ሁላችንም በያለንበት መጽሐፎቻችው በመግዛት መተባበር በትግሉ ውስጥ እርዳታ እንደማድረግ ይቆጠራል።

ወደ ተነሳሁበት ስመለስ ታዲያ ተስፋዬ ሰላቢ ጻሐፊዎች የሚለን እሱን የተጠናወተው እርኩስ መንፈስ፣ እኛን ስላልተጠናወተን አንታየው ይሆናል። ለእውነት ቅርበታችን ደግሞ ከማንኛው በላይ እንዳስፈራው ግልጽ ነው። ለወዳጆቻቸንና ዓላማ ለምንጋራው ግዙፍ ሆነን እንታያለን። እኛንና እሱን የቅርብ ሩቅ የሚያደርገን የዓላማው ከአጥናፍ አጥናፍ መሆኑ ነው። እውነት እውነቱን ስንናገር፣ ዓላማ ስንጋራ፣ የሚከፋፍለውን ትተን የሚያቀራርበውን ስንሰብክ  ቅርብ ነንና እንታየው ይሆናል። በተለያየ ዓላማ ግን አጠገባችንም ሆኖ ለመታየት አንችልም። ከከፋፋይና ሕዝብን እርስ በእርስ ለማዋጋት ከሚጥር እቁብ አንጠጣም፣ እድርም የለንም። ራሳችንንም ለማሳወቅ ብዙ ጥረት አናደርግም። ለሃገራችን ስንል ስንሰደብ ደግሞ ደስ ይለናልና የከፋን እንዳይመስልብን። ስለሆነም ለሻብዕያና ለወያኔ ሰላቢ ሆነን መቆየትን መርጠናል።

ሰለተስፋዬ “የማታውቅበትን የሰው . . . ’’  በሚለው ኀዳር / 2004  በተጻፈው ፅሁፌ ውስጥ የጠቀስኩት አሁንም እደግመዋለሁ።

ታሪክም ቋንቋም ቢሆን ባለቤት አለው። ማንም ሲመቸው እየተነሳ የሚደለቅበት የዛር ዘፈን አይደለም። ቋንቋ ደግሞ በረዥም የማህበረሰብ ሁለገብ ግንኙነት፣ እድገትና ውድቀት፣ እምነትና ፍልስፍና (እውቀት) አመራረትና አኗኗር .. የዳበረና በማኅበረሰብ ሕግ ሠፊ ተቀባይነት አግኝቶ በሁሉም ዘንድ በአወንታ ለዘመናት ሲሰራበት የኖረና የሚኖር ዓብይ የጋራ እሴት ነው።

የጨረባ ተዝካር ዓይነት፣ የቃላት የአሉባልታ ጋጋታ ላንድ ሰሞን ተባለ እንዴ……. ! ባዮች ቡና ማጣጫ ሊጠቅም ይበጅ እንደሁ እንጂ ሃገራዊ ጥቅም የለውም። ሃገር በአሉባልታ አትገነባም።ጦር ከፈታው፣ ወሬ የፈታውእንዲሉ። ተስፋዬ በለመደበትና ባደገበት ብእሩም በሚመጥነው ደረጃ ቢናገርም፣ ቢጽፍም ባልከፋ ነበር። ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ጠቃሚ ሀሳብ ማፍለቅ ከሰከነ አይምሮና ከተባ ብእር አንጀት ይወለዳል። የተማረ ሁሉ አያነበንብም፣ ያነበነበ ሁሉ አያዜምም፣ ያዜመ ሁሉ ደግሞ ቅኔ አይዘርፍም።  አንዳንዶች መንታ ልብና መንታ እግር ስለአላቸው የሁለት ዓለም ሠራዊት በአንዴ ማዝመት ያምራቸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:     ‹‹የቆላ አጋዘን የገደለ መቶ ከብት ወይም ተመጣጣኝ ካሣ እንዲከፍል አባ ገዳዎች ወሰኑ፡፡››    

በዚህ ዘመን በኢትዮጵያ ታሪክና ሕዝብ ላይ አረም የበዛበት ዘር ለማብቀል የሚፍጨረጨሩ በርካታ ጸሃፊዎች እንደአሸን እየፈሉ በአሉበት በአሁኑ ወቅት እንኳ፣ እንዲህ በገሀድ ፍጥጥ ያለ፣ ፈሩን የሳተና የተዛባ የሐሳብና የቃላት ትርጉም ደራሲ አላጋጠመኝም። የሁለት ዓለም ወግ ባንድ ምላስ ማስተናገድ ይቻል ይሆን? በተዛባ እውቀትና ትርጉም፣ አለያም በስውር ተልእኮ፣ እንዲያም ሲል ከመሰሪነት በሚመነጭ  ሀሳብ የሌሎችን ቀልብ ለማደፍረስ ከንቱ ቅኝት መቃኘት ነው የሚሆነው። እሱ ደግሞ መጨረሻው ቅሌት ነው የሚያተርፈው። የአሉሽ አሉሽ ወግ እንኳን ሀገር የግል ቤት አይገነባም። ወግ መጠረቅ ወይም መጻፍ፣ ታሪክን ከመቃኘትና ከመክተብ ጋር እጅግ የተራራቁ ግብሮች ናቸው።

ከተስፋዬ ጽሁፍች ብዙ ታዝበናል፣ አዝነናል ስቀናልም።  አንዳንዶቻችን ገና ከጅምሩ መዳረሻቸው ለመቃኘት ችለናል።የሱንም ማንነት ለማወቅም ቢሆን ብዙ ማጣቀሻ አላስፈለገንም።  ራሱን በዛው በጀመረው የወግ ጥረቃ (በተልእኮም ይሁን በግል አቋም) ዙሪያ ገድቦ ቢጫወት የሚያዋጣው ይመስለኛል።

ምክንያቱም አቶ ተስፋዬ ከምድር በላይ ሊያሳየን የሚሞክረው የጥላቻ ዛፍ ከምድር ውስጥ ከብዙ ከምንወዳቸው ዛፎች ጋር በሥሮቹ አማካኝነት ተጋምዶና ተጠላልፎ እየኖረ ስለመሆኑ አስቦ የሚያውቅ አይመስለኝም። የቡርቃ ዝምታ ሊቀጥል የማይገባው ለሕዝብና ለሃገር የማይጠቅም የባዕድ ተልእኮ ነውና ።

ዛሬም ዜጎቻችንን የሚስተሳስርልን ታሪክ አጉልተን፣ በሩዋንዳ የተደረገው ዓይነት አሳዛኝ ታሪክ እንዳይፈጸም የታሪክ አደራ አለብንና ሁላችንም ዘብ መቆም ይጠበቅብናል። ልንተርከው የሚገባ ሕዝባችን አንድ አድርጎ የቆየ ስንት ታሪክ በጎሣ ፖለቲከኞች ቢደበቅም አደባባይ አውጥተን ማሳየት ያሻል። አለበለዚያ ግን ለነተስፋዬ ቦታ መልቀቅ አደገኛነቱን የጎላ ነው።

 

ስለ ሕዝብ አንድነት የሚሰብኩ በሰላም ይክረሙ።

 

በልጅግ ዓሊ

14.10.2013

ለንደን Beljig.ali@gmail.com

 

 

 

 

9 Comments

  1. thnks Mr Belgig Ali

    Tesfaye is a poisnous cobra who will will use any moment to bite Ethiopians especially AMHARAS …. in his book he uses an old woman from HARARI( probably she is dead as he usually use dead people to preach hate and lie) to talk about the BRUTALITY OF AMHARAS and he claimed the lady told him THE AMHARAS wear KODA kkkk he mentioned kODA to insult AMHARAS just like OLFites OLFites usually insult AMHARAS as KODA LEBASH

    TESFAYE continue asking the HARARI LADY were there OROMOS in the MINILIK ARMY? she told him they were only AMHARAS who are Chekagn he put this line intentionally to make it look like MINILK army was made up of entirley from AMHARA

    TESFAYE is like a YE BISHEFTU KORIT who works day and night to see the destruction of a country of 80 million people, he must be possesed by a BAD SPIRIT, I am sorry for him sometimes

    last but not least I feel sorry by NEWS MEDIAs like EMF, ESAT, etc for not saying anything about this KOBRA

  2. I am surprised that why Amharas dont want to know about the true history of oromo? And why they hate the person who talk and write about oromo????come on amharas now we r in 21st century world. intellectal people speak aganist injustice and inhuman act through writting,that is where Tsfaye belong to. Tesfish never yield to these idiots,we will stand on your side no mater what. you are in the hearts and minde of the oromo people just like like prof.Asmeron Legesse.we know the march of amharas against you is due to their “oromo-phobia”;

    • Why is our brothers Amaras a target practice for us Oromos? When is a frothy something years old drunken man who is a so called exceptional writer by some foolish individuals becomes a historian? And we have to believe what ever he writes as a true event with out critical thinking? Any one who reads that book knows that the person in question here is a genocide instigator. End of story. Nonetheless, he has not written what is being done by tplf at this moment. We have yet to see that writing. Oromos, Amaras, Afars, Gurages, Gambelas, and Ogadens are suffering now under tplf. Where is the uproar far that? Can you answer this Mr. gebeyaw?

  3. TESFAYE ERKUS as his usual approach tried to tell Sick OLFites that only Oromos are teased by people from Addis Abeba or only Oromo names are teased by Amharas the fact of the matter is that people from GOJJAM are the once who are teased and ridiculed by Addis Abebians and the name SHEWAYE is the most a used name in Ethiopia which happened to be an Amhara name

    TESFAYE ERKUS know very well this however his mission is to make Ethiopia be like SOMALIA that is why he writes to touch the soft spot of ignorant and hate filled OLFites who dream to persecute AMHARAS

    He even told us HARARIS do not feel as an Ethiopian and labelled GURAGES as collaborators of Menlik Army and went to say Amharas chased them away from Harar to make Amharas as betreyers

    Btw in his all books TesFaye portrayed ERITREANS as Smart, Confidient and complicated lol

  4. What is the use of Tesfaye’s fabrication to lie against Amharas and Oromos, why is he revolving aroung these two races because Ethiopia is a nation of 80 people.

  5. Look, all comments and critiques are about who is Tesfaye. So far, nobody has falsefied what he wrote in all his books chapter by chapter with tangible evidences. Based on my personal exposure I believe that what Tesfaye raised are facts and we shall discuss on them openly as the South Africans did at the end of Apartide regime. Favouring only good stories by hiding past mistakes as well as withstading opposite idea raisers can’t help for national consesus and Ethiopian unity as it was tried for long times but failed to bring the required consesus on the coutry’s unity. We have to learn from our past mistakes and do our best for the betterment of our future. Hence, we shall be true to ourselves and always listen to our consciousness to always stand against any oppression against anybody.

  6. ወረኛ ነህ እሱ እንኯን አንደኛዉን እራሱን ገልጦ እኔ ተስፋዬ ገብረ እባብ የድሮዉ የወያኔ ተላላኪ የአሁኑ የሻዕቢያ ወኪል ነኝ ብሎ የመሰለውን ለቅልቇል አንተም በአንተነትህ አትፈር የለበስከዉን ብርድ ልብስ አዉልቀው ።

  7. bejing….i have told you many times do not waste your freaking time wrtiting irrelevant and nonsense things which doesnt have any impact to the struggle instead just do a part time job to support the struggle finacially period….otherwise we ethiopians are tired of endless TERET TERET about weyane

  8. For Gebeyaw lew
    hey-Gebeyaw lew instead of writing ur history, why u like shabia’s fiction for u.This is most OLF people problem( Denkoro Yesemalete) Please write ur history

Comments are closed.

Share