በፊት የበቀለን ጅራት በዃላ የበቀለ ቀንድ በለጠው! – አገሬ አዲስ

አትዮጵያ ለዘመናት ህልውናዋን አስከብራ ፣የቅኝ ገዢዎችን ተደጋጋሚ ጥቃት ተከላክላና ድንበሯን ጥሰው ሲመጡም ቅስም ሰብራ የመለሰች፣ ለብዙ አገሮች የነጻነት ምሳሌ ሆና የኖረች አገር ናት።

በቅኝ አገዛዝ ሰንሰለት ስር የወደቁትን አገራት በተለይም ጥቁር ህዝብን ነጻ ለማውጣት ያላሰለሰ ጥረት አድርጋለች።ለብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች ነጻነት ያልከፈለችው ዋጋ የለም።ትግላቸውን በማስተባበርና በማገዝ፣በዓለም አቀፉም መድረክ ላይ ድምጽ አልባ ለሆኑት ድምጽ ሆና ብሶታቸውን አሰምታለች።ለናሚቢያ፣ለሮዴዝያ/ለአሁኗ ዚምባብዌ፣ለደftብ አፍሪካ ሕዝቦች ነጻነት በራሷ ወጭ ጠበቃ አቁማ በኔዘርላንድ ውስጥ በሄግ በሚገኘው የዓለም ፍርድ ቤት የተከራከረች አገር ናት።

በዚህ ተግበሯና አልበገር አቋሟ የነጭ የበላይነትን የሚያስተጋftና የቅኝ አገዛዝን የሚያስፋፉ አገሮች ቀዳሚ ጠላታቸው አድርገዋት ከውጭና በውስጥ ሲወጓትና ሰላም ሲነሷት ኖረዋል።ጥረታቸውም ተሳክቶ የዛሬ ሃያ ስድስት ዓመት ያንኑ የማፈራረስ ዓላማቸውን የሚያራምድላቸው ቅጥረኛ ባንዳ ftድን በመንግስት ስም ስልጣን ላይ እንዲወጣና የማፈራረሱን ተግባር ዳር እንዲያደርስላቸው አድርገዋል።በተከታታይ ስልት አገሪቱን እንደ ዳቦ እየቆራረሱ የማመንመኑ ስራ በኤርትራ ተጀምሮ አሁን በሌሎቹም ያገሪቱ ክፍሎች እንዲዛመት ተግተው በመስራት ላይ ናቸው።ቀላሉ የማፈራረስ ዘዴም የጎሳና የእምነት ልዩነት በመሆኑ ሕዝftን በዚያ የመነጣጠያ ስልት ውስጥ እንዲገባ የራሱን ሃይማኖት ተከታዮችና ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑትን አሰማርተዋል።ኢትዮጵያዊነትን በማዳከም በጎሳና በክልል አጥር ለያይተው እርስ በርሱ እንዲናቆርና አገሪቱ እንድትፈራርስ ስልት ነድፈው በመተግበር ላይ መሆናቸውን የማይረዳ ዜጋ የለም።

ይህንን መሰሪ ዓላማቸውን በመቃወም ሕዝft አደባባይ ሲወጣና ሲገደል እንዳላየ በመሆን፣ለገዳዩ ድጋፍና ሽፋን በመስጠት ሃጢያቱን በመሸፋፈን ለበለጠ ጥቃት እንዲዘጋጅ አስፈላጊውን እርዳታ እየሰጡ ዓለም አቀፍ ሕግን እረግጠው ከጎኑ ተሰልፈዋል።ለስሙ በሚካሄደው ምርጫ ተብየውም ድምጹን ሲያሰማ የምርጫው ውጤት የአገዛዙ መሳሪያ በሆኑት ፍርድ ቤቶችና የምርጫ ቦርድ በሚባለው የመንግስት ተብየው አፈቀላጤ ተቋም እየተሻረ ውድቅ ሲሆን አልፎ አልፎ የአዞ እምባቸውን ከመርጨት ያለፈ ተገቢ እርምጃ ሲወስዱ  አልታዩም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወያኔና የብልፅግና ጦር አበጋዞች የጦርነት ንግድና የ2.5 ቢሊዮን ዶላር የመሠረተ-ልማት ውድመት!!!

የኢትዮጵያ ሕዝብ የራሱን ጉዳይ በራሱ ለመፍታት የዜግነትና ሕገመንግስት በሚፈቅድለት መንገድ መብቱን ለማስከበር ከመጠየቅ ቦዝኖ አያውቅም።መብቴ ይከበር፣የምርጫዬ ውጤቱ አይዛባ!ብሎ ሲጠይቅ የሚሰጠው መልስ በጠራራ ጸሃይ በጥይት መደብደብ፣መሞት፣መቁሰል፣መታሰርና መሰደድ ነው።ለሌሎች አገር ሕዝቦች መብትና ነጻነት የታገለችው አገር የራሷ ሕዝብ የሚሰቃይባት፣መብትና ነጻነቱ ያልተከበረባት አገር ሆናለች።ያም ብቻ ሳይሆን እንዳገር የመቀጠሏ ነገር ከአደጋ ውስጥ ገብቶ ይገኛል።

ለነጻነታቸው የታገለችላቸው አገሮች ለሕዝባቸው የዴሞክራሲ ስርዓትን ለማስፈን ሲበቁ አትዮጵያ በአምባ ገነኖች መዳፍ ስር በየተራ እየወደቀች ከእድገት ይልቅ ውድቅት ጎልቶ የሚታይባት፣ሰላሟና አንድነቷ ተናግቶ የአገሮች ማስፈራሪያ ሆናለች። ለነጻነታቸው የታገለችላቸው አገሮች ለሕግና ለፍትሕ የሚያድር መንግስት ሲበቁ ኢትዮጵያ ሕግና ፍትህን የሚጥሱ ወንበዴዎች በጉልበት ስልጣን የሚቀባበሉባት አገር ሆናለች።በስነ አስተዳደርና የፖለቲካ ችሎታ ሳይሆን በነፍጥና በጎሳ ማንነት ስልጣን የሚጨብጡባት አገር ሆናለች።

ለነጻነታቸው የታገለችላቸው አገሮች ለፍትሕ በቅተው ሕዝብ አምባገነንነትን በመቃወም የምርጫ ማጭበርበርን በፍርድ ቤት ሲረታ ለማየት ችለናል።ለዚህም በቅርባችን የምትገኘው የጎረቤት አገር ኬንያ አንዷ ናት። በ08-08-2017 ምርጫ ተካሂዶ አሸነፍኩ ብሎ የወጣው በስልጣኑ ላይ የነበረው መንግስት ሲሆን ያንን በመቃወም የተቃዋሚው ፓርቲ ደጋፊዎች አደባባይ ወጥተው በመቃወም የደም ግብር እስከመክፈል ድረስ ደርሰዋል።የብዙ ሰዎች ህይወት ለመጥፋትም ምክንያት ሆኗል።የሕዝft ተቃውሞ በይፋ እንዳይወጣ የውጭ ዜና አቅራቢዎች ቢያድሙም የሕዝft ትግል ያገሪቱን የፍርድ ተቋም ወጥሮ በመያዙና የምርጫ ቦርድ የተባለውንም አካል አላላውስህ ስላለው እውነቱን ከመቀበል የተሻለ አማራጭ ባለመኖሩ ያገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የምርጫ ውጤቱ ትክክል አለመሆኑንና የተጭበረበረ መሆኑን በማመን ሌላ ምርጫ እንዲካሄድ ወስኗል።ለረጅም ዘመናት የመንግስት ስርዓት ባለቤት ሆና ለፍትሕ ባዳ ሆና ለኖረችው አገራችን፣ለኢትዮጵያ ትልቅ ምሳሌ ነው።የኬንያ ሕዝብ መብቱን እስኪያረጋግጥ ድረስ ግንባሩን ለጥይት ሰጥቶ ያላሰለሰ ትግል በማድረጉ የድሉ ባለቤት ለመሆን መብቃቱም ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ አርአያ ነው።በነጻነት የቀደምናት ኬንያ በፍትሕ በኩል ቀድማን እንደሄደች ይህ

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጃርት ጉባኤ ርደት (ሥርጉተ ሥላሴ ሲዊዘርላንድ -ዙሪክ)

 

ጉልህ ማስረጃ ነው።በስልጣንም ላይ ያሉት ፕሬዚደንቱ ኬንያታ ያገሪቱን ሰላምና አንድነት ከስልጣናቸው በላይ እንደሚያዩት የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንደሚያከብሩት በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።ይህ እራሱ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ መሪዎች እራሱን የቻለ መልእክት ነው። በዚህ ጎዳና የተጓዙ ሌሎች ያፍሪካ አገሮችም እንዳሉ መዘንጋት የለብንም።በኤዝያም ውስጥ ወር ባልሞላው ጊዜ የፓኪስታኑ ጠ /ሚኒስቴርና የደftብ ኮሪያ ፕሬዚዴንት የነበሩት በሙስና ምክንያት ከስልጣን ተወግደው እጃቸው በካቴና ታስሮ ለፍርድ እንደቀረft ያየነው የሰሞኑ የፍትሕ ውጤቶች ናቸው።ማንም ከሕግ በላይ ሊሆን እንደማይችል ያረጋገጡ ክንውኖች ናቸው።ያገራችን ዳኞችና የፍትሕ ባለሙያዎች ፊታቸውን ወደነዚህ አገሮች የፍርድ አሰራር መለስ ብለው ቢያዩ ከብዙ ስህተት፣ ወቀሳና የታሪክ እርግማን ድነው ብሎም አገራቸውን ከመበታተን ባዳኑ ነበር። አሁንም አልመሸም።ንስሃ ገብተው ለእውነት ሊፈርዱ የሚችሉበት በሩ አልተዘጋም። በጎንደርም ፍርድ ቤቶች ዙሪያ ዳኞች ያሳዩት አቋም የሚመሰገን ሲሆን ሌሎቹም አርአያውን መከተል ይኖርባቸዋል።

በፊት የበቀለን ጅራት በዃላ የወጣ ቀንድ በለጠው ማለትም አትዮጵያን ሌሎች ከዃለዋ ነጻ የሆኑት አገሮች በፍትህና በመልካም አስተዳደር ብሎም በአገር ወዳድነት እንደቀደሟት ለማሳየት የተሰነዘረ ምሳሌ ነው።አሁን አገራችን ቀድማ የሄደችበት ነገር ቢኖር በሙሰኛነት የአገር ሃብት መስረቅና ማሸሽ፣ በጎሰኝነት ሰልፍ አገር የማፈራረሱ ርብርቦሽ ዙሪያ የሚታየው ውድድር ነው።

ለኬንያ ሕዝብ መጭው ምርጫ የተሳካና የሚፈልገውን መንግስት የሚያገኝበት፣የአገሩ ሰላምና አንድነት የማይናጋበት እንዲሆንለት እየተመኘን እኛንም ወደዚያው ጎዳና የሚያመራንን ሁኔታ ለመፍጠር እንድንበቃ ምሳሌነቱን መውሰድ ይኖርብናል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለፉት ብዙ ዓመታት ለመብቱ መከበርና ለአገሩ አንድነት ያደረገው ትግል የከፈለውም መስዋእትነት በጣም ብዙ ቢሆንም ባለመቀጠሉና ባለመያያዙ ጥያቄው መልስ ሳያገኝለት ደመ ከልብ ሆኖ ለቀጣይ ጭቆና እየተዳረገ አሁን ካለበት የመኖር ያለመኖር ድንበር ላይ ደርሷል። ከስህተቱ ና ከሌሎች አገሮች የሕዝብ ትግል ተምሮ ትግሉን ከዳር ለማድረስ ቆርጦ መነሳት ይኖርበታል።ነካክቶ ከማለቅና የአልሞ ተኳሽ መማሪያ ከመሆን  አርፎ መቀመጡ ይመረጣል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከሞትንማ ቆይተናል!!! -    ማላጂ

የነብር ጭራ አይዙም ከያዙም አይለቁም።የኬንያ ሕዝብ ተተኮሰብኝ ብሎ ከትግሉ አላፈገፈገም፤አንዱ በጥይት ተመቶ ሲወድቅ ሌላው አልሸሸም፤ስልቱን እየቀያየረ የፍርድ ባለቤት እስኪሆን ድረስ ኬንያዊ ነኝ ብሎ ታገለ እንጂ ኩኩዩ፣ማሳይና ሌላም ጎሳ ነኝ ብሎ እርስ በርሱ ተፋጦ አገሩን ለመበታተን አልተሰለፈም።የውጭ ሃይሎች ግን ሳይሞክሩ ቀርተው አይደለም፤ለወደፊቱም ይሞክራሉ።ለጊዜው ግን አልተሳካላቸውም።ነገም  የድሉ ባለቤት እንደሚሆን አያጠራጥርም።

እኛም የአገርን አንድነትና ነጻነት ከአደገኛ የጎሳ መንጋጋ አውጥቶ ለማስከበር በኢትዮጵያዊነት መንፈስ የዴሞክራሲ ስርዓትን ለማስፈን የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ ትግል ከዳር ለማድረስ በግንባር የሕይወት ዋጋ እየከፈሉ ያሉትን ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ከቻልን እንቀላቀላቸው አለያም እንርዳ!ስንቅና ትጥቅ እናቅርብላቸው።ያንን የሚያቀናጅ አንድ ብሔራዊ አገር አድን ተቋም እንመስርት!በየፊናው መሯረጡ ይቁም። ለዚህ ቀውስ ያበቁንን ፈረንጆች ከመለመንና የነሱን በረከትና ፈቃድ ከመጠየቅ በራሳችን ተማምነን የሚገባውን እንስራ።የድርጅት ብዛትና ጋጋታ ችግር ያበዛል እንጂ ችግር አይፈታም።

ኢትዮጵያ ለዘላለም በነጻነትና በአንድነት ትኑር!!

አገሬ አዲስ

Share