«አንተስ…?»

( ወለላዬ )

ዓይኔን  በዓይኔ  ያየሁበት፣

በስተእርጅና  ያገኘሁት፣

የትናንቱ  ማሙዬ፣

ያሳደኩት  አዝዬ

የንግሊዞችን  ወረራ

ሰምቶ፣

በቴዎድሮስ ሞት

ተቆጥቶ፣

ለምን?  ለምን  ሞተ?

ብሎ  ሲያለቅስ፣

የዓይኑን  ዕንባ  ላደርቅ-

የልቡን  መሰበር  ላድስ፣

ጀግኖቻችንን  ቆጥሬ-

ታሪካችንን  ባወድስ፣

ዕንባውን  ዋጥ  አድርጎ-

በአትኩሮት  ዓይኔን  እያየኝ፣

«አንተስ…?» አንተስ!-

ምን  ሰርተሀል?  በማለት  ጠየቀኝ።

እድሜ  ቢደራረብ  ተግባር  ሳይላበስ፣

እንደዚህ  እንደኔ  ያስጠይቃል  ለካስ!

 

 

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  በዉጭ አገር ለምትገኙ ለተከበራችሁ የኢትዮጵያዉያን ሜዲያዎች -- ከሰሜን አሜሪካ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ግብረ ኋይል

1 Comment

Comments are closed.

Share