የዚህን ጨቋኝ ስረአት እድሜ እንድናሳጥር መረባረብ ይጠበቅብናል (ልኡል አለሜ)

ልኡል አለሜ ይድረስ ለተከበራችሁት ሁሉ!

አሁንም ወደፊትም በዚህ ገጽ ላይ የኔ ብቻ አመለካከት እና እኔ የማምንበትን ማንንም የማይወክል ሐሳብ እንደምሰነዝር እያረጋገጥኩ ከዚህ በታች አጠር ያለ መልእክቴን አስተላልፋለዉ። ዉድ የተከበራችሁ ወገኖቼ ህወሃት ወያኔ ቀንደኛ ጠላቴ ነዉ! ከዚህ ዉጭ ከማንም ጋር ችግር የለብኝም የአመለካከት ልዩነቶች በመነጋገርና በመወያየት እንደሚፈቱ አምናለዉ ህወሃት ከማንኛዉም ነገሮች ይበልጥ የሚፈራዉ መደራጀትን እና አንድነትን ነዉ ስትደራጅ ሽማግሌ ይልካል ስትደራጅ በጥባጭ ከነማማሰያዉ ያሰማራል በዚህ ምክንያት ብዙዎች ተደራጅተዉ ወድቀዋል አዳዲሶችም መደራጀት ተስኗቸዋል፡፡ በመሆኑም ህወሃት ወያኔ በተመሳሳዩ በ7 አመት ያህል ግዜ ዉስጥ ተደራጅቶ ስኬታማ የሆነዉን አርበኞች ግንቦት 7ን በሚችለዉ መልኩ ሁሉ ተዋግቶታል ዉጊያዉ ከሀገር ዉስጥ እስከ ባሕር ማዶ ተሻግሮ የመን ደርሶ የተከበሩ የነጻነት አባት አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌን እስከማሳፈን ደርሶ ነበር፣ ነገር ግን የድርጅቱ አወቃቀር እና የተጠቀመበት የትግል ስልት ከህወሃት የላቀ ሆኖ በመገኘቱ ዛሬ ወያኔን ለመጣል እየተደረገ ባለዉ እርብርብ ላይ አርበኞች ግንቦት 7 ቀዳሚዉን ስፍራ ይዟል። ይህንን ድርጅት ተሸክማችሁ እዚህ ያመጣችሁ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ክብር ይገባችኋል በተለይም የድርጅቱ ፕሮግራም ላይ በሰፈረዉ መሰረት አርበኞች ግንቦት 7 ህወሃትን ከመጣል የዘለለ አላማ እንደሌለዉ ለመረዳት ችለናል ህወሃትን ገርስሶ ስልጣን ለሰፊዉ ህዝብ በማስረከብ የተረጋጋች አንዲት ኢትዮጵያን አስከብሮ የሁሉም ብሐር ብሔረሰቦች የጋራ ቤት እንዲኖር የማረጋገጥ ሐላፊነትን ከመላዉ ህዝቦች ጋር በጋራ በሐላፊነት መቀበል የያንዳንዳችን ግዴታ ነዉ። ዛሬ የነጻነቱ ማእበል ጀግኖች ኢትዮጵያዊያንን አዋህዶ እየገሰገሰ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ላይ እርስ በእርሳችን ተከባብረን የዚህን ጨቋኝ ስረአት እድሜ እንድናሳጥር መረባረብ ይጠበቅብናል ካልተባበርን ወደፊት የሚመጣዉን አደጋ ለመቀበል የሚያስችል ሃይል አይኖረንም በማንኛዉም መልኩ በአምላክ ሳይሆን በሰዎች የተሰሩ ነገሮች ላይ ስህተት ሊፈጠር ይችላል ነገር ግን ስህተቶችን ለማረምና ለማስተካከል አብረን ካልተጓዝን አሁን እየተገኘ ያለዉን ድል በሙሉ ለህወሃት አሳልፈን በመስጠት ቋሚና ታሪካዊ ስህተት እንፈጽማለን። አሁን አርበኞች ግንቦት 7ን ለመዋጋት ያቃተዉን ሃይል መልሶ እንዲያንሰራራ በማድረግ ብዙዎች የሞቱለትን መሰዋትነት የተከፈለለትን የነጻነት ጮራ ከማጨለምና ከማቀጨጭ ዉጭ ምንም እርባና የለዉም። ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!! – See more at:

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዕንባ! (ሥርጉተ ሥላሴ 27.03.2014 (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)

 

Share