November 14, 2016
4 mins read

ስለ አማራ መደራጀት [ ክፍል ፩]

አቻምየለህ ታምሩ

አማራ በአማራነት የሚደራጀው እንደ ኦነግ አይነት ኦሮሞነት ወይንም እንደ ወያኔ አይነት ትግሬነት ለመፍጠር አይደለም። እኛ የአማራ ወጣቶች በአማራነት የምንደራጀው ግራዝማች አፈወርቅ ወልደ ሰማያት ቆራሄ ላይ መስዕዋት የሆኑባትን ኢትዮጵያ፤ ጀኔራል ለገሰ ተፈራ ዋቤ ሸለቆ ደማቸውን ያፈሰሱባትን የአባቶቻችን ምድር ረስተን አይደለም። አማራ በአማራነቱ የሚደራጀው አፈወርቅና ለገሰ ዋጋ በከፈሉባት አገር በሰፊዋ ኢትዮጵያ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በእኩልነት ለመኖርና የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ ለመከላከል ብቻ ነው።
አንዳንዶች አማራ በአማራነቱ የሚደራጀው እንደ ኦነግና ወያኔ የራሱን መንግስት ለመመስረትና ለፖለቲካ ስልጣን እየመሰላቸው የአማራን መሰባሰብ በጥርጣሬ ሲመለከቱት ይስተዋላል። በርግጥ በብሔረሰብ መደራጀት ማለት እንደ ወያኔና ኦነግ አገር ለማፍረስ መሆኑን በተግባር ያየ ማህበረሰብ አማራው በአማራነቱ ይደራጅ ሲባል በጥርጣሬ አይን መመልከቱ ባይፈረድበትም፤ አማራው በአማራነቱ የሚደራጀው ከሌላው ጋር የሚያስተሳስረውን የወንድማማችነት ሰንሰለት የበለጠ ለማጠናከር እንጂ ለመበጣጠስ አለመሆኑንና ከኢትዮጵያም ሆነ ከህዝቧ አንጻር ለመቆም እንዳልሆነ ሲነገዘብ ግን የአማራውን መደራጀት ከተጋረጠበት የህልውና አደጋ አኳያ በጥርጣሬ ሊያየው አይገባውም።
ከፍ ብሎ ከቀረበው የአማራ መደራጃት አስፈላጊነት በተጨማሪ እኛ የአማራ ወጣቶች በአማራነት የምንደራጀው የግራ ፖለቲካ ያጠየማቸውን የአማራ ሰብዓዊ እሴቶች፤ምግባርና አስተሳሰቦች፤ አማራው ለፍቅር ገር፣ የቅንነት አሽከር መሆኑን አንደበት አውጥተን፤ ግዝፍ ነስተን መልክዓ ልቡናውን ልናሳይለትም ጭምር ነው።
ስለዚህ በአማራነት ስንደራጅ ሰብዓዊ የሆኑትን የአማራውን መሰረታዊ እሴቶች ተሸክመን፤ የአማራው የኑሮ አድማስ በስነ ምግባር ደንቦች የታሸ፤በስሜት የበሰለ፤ በእውቀትና ግንዛቤ የላቀ መሆኑን ማስመርከርና አማራው በሰርክ ህይወቱ ማህበራዊ ስርዓት ሳይናጋ፤ አገራዊ ቀውስ ሳይፈጠር ማህበራዊ ለውጥ የሚጠነስስ፤ የራሱንና የሌሎችን ባህልና ታሪክ ጠብቆና አክብሮ የሚኖር፤ በትህትና፣ በቸርነትና በይቅር ባይነት የተገነባ የምር ኢትዮጵያዊ መሆኑን እንድናሳይም ይጠበቅብናል።

habtamu05
Previous Story

Hiber Radio: የአማራ ገበሬዎች ተጋድሎ ተጠናክሮ ቀጥሏል፣ታጣቂዎች በደቡብ ኢትዮጵያ በቱሪስቶች ላይ ባደረሱት ጥቃት የሰው ህይወት ጠፋ፣አትሌት ፈይሳ ሌሊሣ በወያኔ አገዛዝ ሳቢያ አገሪቱ እንደ ሊቢያ እንዳትበታተን ስጋቱን ገልጿል፣አትሌቱ የሕወሓት መንግስት በቤተስቦቹ ላይ ብቀላ ማካሄዱን ተናገረ፣ከሰሜን ጎንደር ደባርቅ የታፈሱ ወጣቶች ወዳልታወቀ ስፍራ ተወሰዱ፣ጦማሪ በፍቃዱ በድጋሚ የታሰረው ኮማንድ ፖስቱን በሬዲዮ ተችተሃል ተብሎ ነው፣አረብ ኢሚሬት በአሰብ ወደብ ላይ እጅግ ዘመናዊ ተዋጊ አሮፕላኖችን ማስፈሯ ተነገረና ሌሎችም

68845
Next Story

አሁን የደረሰን ዜና

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop