ጎንደር ሕብረት እና ጎጃም ዓለም አቀፍ ትብብር የኦሮሞ ትግል አስተባባሪ በክብር እንግድነት በሚገኙበት በሚኒሶታ

ጎንደር ሕብረት እና ጎጃም ዓለም አቀፍ ትብብር የኦሮሞ ትግል አስተባባሪ በክብር እንግድነት በሚገኙበት በሚኒሶታ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አዘጋጁ

(ዘ-ሐበሻ) በሃገር ቤት በአማራው ክልል እየተደረገ ያለውን ሕዝባዊ ትግል ለመረዳትና ለማገዝ የሚያስችል ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በጎንደር ሕብረት እና በጎጃም ዓለም አቀፍ ትብብር መዘጋጀቱን አዘጋጆቹ ለዘ-ሐበሻ በላኩት መረጃ አስታወቁ::

ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ እንደሚጠቁመው ቅዳሜ ኖቬምበር 26 በሚደረገው በዚሁ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ አሁን ያለው የኦሮሞ ሕዝብ ትግል አስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ መሐመድ አደሞ በክብር እንግድነት የተጋበዙ ሲሆን በወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ገለጻ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል::

የጎንደር ሕብረት ሊቀመንበር አቶ አበበ ንጋቱ እንዲሁም የጎጃም ዓለም አቀፍ ትብብር ሊቀመንበር አቶ ደመቀ ገሰሰም ወደ ሚኒሶታ እንደሚመጡና የዚሁ ሕዝባዊ ስብሰባና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አካል እንደሚሆኑ ተገልጿል:: ይህን ታላቅ ዝግጅትም ከድምጻዊነቱም በተጨማሪ በትግሉ ውስጥ ከፍተኛውን ሚና እየተጫወተ የሚገኘው ፋሲል ደመወዝ እንደሚገኝ ታውቋል::

“የኦሮሞና የኣማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ” የሚለውን መጽሐፍ የጻፉት ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል::

ለበለጠ መረጃ ቭድዮውን ይመልከቱ::
https://www.youtube.com/watch?v=3zktkTvBEHI&feature=youtu.be

ተጨማሪ ያንብቡ:  በቓፍታ ሑመራ ከ2 ሺ በላይ ወጣቶች ታሰሩ
Share