ነቢዩ ሲራክ
ከሳውዲ አረቢያ
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከፍተኛ ሃላፊዎችን የያዘ ቡድን በአንባሳደር ውብሸት ተመርቶ ሳውዲ መግባቱን ሰምቸ ነበር ። ከፍተኛ ሃላፊዎችን የያዘው ቡድን ሪያድና ጅዳ የኮንትራት ሰራተኞችን ይዞታ ለማየት እንደመጣ መስማቴ ደግሞ ጉዳዩን እግር በእግር እንድከታተለው ምክንያት ነበር። የጅዳው ጉብኝት ዛሬ ማለዳ ከመድረሱ በፊት የኮባንያ ስራየን በጊዜ ሸካክፊ ወደ ጅዳ ቆንስል አመራሁ … ! በቆንሰሉ መጠለያ ድርሸ ወደ ግቢው በር ስገባ እንግዶቹ ከቆንሰሉ በር ወደ መጠለያው ወደሚገኝበት በር ሲንቀሳቀሱ ደረስኩ። ቀድሜ መጥቸ ስለነበር ቀድሜ የግቢውን በር ተሻገርኩ ። ዘልቄ ልገባ ስል የጅዳው ቆንስል ተሶርፈውም ቢሆን እንደመሳቅ እያሉ ጨበጡኝ ። ጨበጥኳች ። ትከሻየን እየደባበሱ ወደ ውስጥ መግባት እንደማይፈቀድልኝ አስታወቁኝ ። ” ለምን ተከልከልኩ? ” ስል ጠየቅኳቸው ” እሱን ሌላ ጊዜ እንነጋገራለን አሉኝና እንግዶችን እየመሩ ወደ ተፈናቃዮች የሚደርጉትን ጉብኝት ለመከወን በጥድፈት ረምድ ረመድ ብለው ጥለውኝ ሄዱ … እንቅስቃሴውን በርቀት እየተከታተልኩ እያለ የኮሚኒቲው ግቢ የጥበቃ በትህትና ጠጋ ብሎ ሰላምታ ካቀረበልኝ በኋላ እንዲህ አለኝ “
አቶ ነቢዩ ይቅርታ! ” ሰላምታ አቅርቤለት ምን ልታዘዝ አልኩት” አይ ምንም አይደለም ከይቅርታ ጋር ቆንስል ጀኔራል አቶ ዘነበ ከግቢው እንዳስዎጣት ትዕዛዝ ስለሰጡኝ ልነግርህ ነው! ” አለኝ!የወንድሜ ትህትና ልቤን ቢሰብረውም አቶ ዘነበ ማነጋገር እንደምፈግ በትህትና ጠየቅኩት ፣ በርቀት ሆነው በአይናቸው የሚቆጣጠሩኝን አቶ ዘነበን ጠራልኝና መጡ! ለምን እንደመከለከል አጥብቄ ሞገትኳቸው ፣ የሚመልሱት ባይኖርም በመረጃ ቅበላው ዙሪያ የምስራው ስራ አስነዋሪ እንደሆነ በደምሳሳው በመናገር ” ግድ የለም ግባ !” ሲሉ በገዛ ቤቴ የከለከሉኝ ሹም አቶ ዘነበ ፈቃድ ሰጡኝ!”ህግን ጠንቅቄ አውቃለሁ!” በሚሉት የጅዳ ቆንስል ጀኔራል አቶ ዘነበ የተላለፉት፣ የገሰሱትን መብቴን መልሰው ቢያከብሩትም የምሰራው የፖለቲካ ስራ እንጅ ለዜጎች በመቆርቆር እንዳልሆነ ጉብኝቱ አብቅቶ ከእንግዶቹ መካከል የመብቴን መገፋት ትክክል እንዳልሆነ ሳስረዳቸው ደጋግመው በሰጡኝ ምላሽ ገለጹልኝ !እንግዶችን ከበው እያነቡ በደላቸውን የገለጹትን ተፈናቃዮች እና መላሽ ይሰጡ የነበሩትን ሃላፊዎች ተመልክቻለሁ።
በአውላላው ሜዳ ላይ ጸጉራቸውን አንጨፍርረው የሚንቀዋለሉት ያበዱ እህቶችን ባስሙ ባያዩም ጩኽት ምሬታቸውን ያስተጋቡት ወደ መቶ የሚጠጉትን ተፈናቃዮች አቤቱታ ሰምቻለሁ!እመለስበትማለሁ !የእኒህን እህቶች በደል መናገር ፖለቲከኛ ካስባለ የምሰራው የፖለቲካ ስራ አለመሆኑን ለማሳየት የግፉአኑን በደል የሚያሳዩ ለማየት የሚሰቀጥጡ መረጃዎች ለማቅረብ ልገደድ ነው!! ይህን የማደርገው ከለመድኩት መቀመጫን ለመከላከል ከሚደረገው ተራ ውንጀላ ራሴን ከውንጀላ ለማጽዳት ሳይሆን እውነቱን ልነግራቸሁና ማን በህዝብ እና በሃገር ላይ ግፍና በደል እንደሚፈጽም ፍርድ ትሰጡ ዘንድ ለማሳየት ያህል ብቻ ነው!
ለሁሉም ከስሜት ወጥቸ በምቀጥልበት የማለዳ ወግ እናዎራለን!
ቸር ያሰማን ! ነቢዩ ሲራክ