20 የዐማራ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ከሕዝብ ጋር ተቀላቀሉ

ከሙሉቀን ተስፋው

ከአዲስ አበባ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ቦሌ አየር መንገድ ሕገ ወጥ የእጽ ዝውውር ላይ አንድ ሻለቃ ውስጥ ይሠሩ የነበሩ ሃያ የዐማራ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው አገዛዙን ክደው ባለፈው ሳምንት ከሕዝብ ጋር መቀላቀላቸው ታውቋል፡፡ የፌደራል ፖሊስ አባላቱን ለዚህ ውሳኔ ያበቃቸው በሕዝባቸው ላይ እየደረሰ ያለው መቆሚያ ያጣ ፍጅት ነው ተብሏል፡፡
በፌደራል ፖሊስና በመከላከያ ሠራዊት የዐማራ ተወላጆች ተለይተው መሣሪያ እንዳይዙ እንዲደረግ ሀሳብ የቀረበ ቢሆንም ስምምነት ባለመኖሩ እስካሁን ተግባራዊ አልተደረገም፡፡ ሆኖም የዐማራ ተወላጆችን መሣሪያ ከሰጡ በኋላ ልዩ ክትትል እንደሚደረግባቸው የዐማራ ተወላጅ የሆኑ የፌደራል ፖሊስ አባላት ገልጸዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ደግሞ የአዋሽ አካባቢ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ሌሎች ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው አገዛዙን ከድተው መሄዳቸው ታውቋል፡፡
ዝርዝር ጉዳዮችን በቅርብ የምናሳውቅ ይሆናል!!
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!!

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያዊነትን እያጥላሉ እና እያገለሉ  ኢትዮጵያ ማለት እንዴት ይሆናል ?

2 Comments

  1. በአዋሽ አካባቢ ያሉት ከረዩ ኦሮሞዎች እንደ ቀሪዎቹ ኢትዮጲያውያን ኦሮምኛ እነ አማርኛ ተናጋሪዎች አገዛዙን ሳይሆን የሚታገሉት አብሯዋቸው ለዘመናት የኖሩትን ሌሎች ብሄረሰቦችን ነው፡፡እንደ አብነት ባለፈዉ ሀሙስ ጳጉሜ 3፣2008 ዓ.ም እለቱ በመተሀራዋ አዲስ ከተማ የገበያ ቀን መሆኑን ተከትሎ እንደወትሮ የከረዪ ብሄር ተወላጆችን ወደ ገበያ ለማድረስ መኪናይዘው የገቡትን ሹፌር በአራት ጥይት በመደብደብ ረዳቱን ደግሞ አንገቱን በጊሌ በማረድ ከመግደለቸው ባሻገር ከዛ ቀደም ብሎ ደግሞ ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን አጠናቆ ከተመረቀ በኋላ ወደ ቤተሰብ ሲመለስ የነበረን ወጣትም እንዲሁ በጊሌ አንገቱን በመቅላት ለሶስቱ ግለሰቦች ግድያ እንደ ምክንያት በገዳዮቹ የቀረበው አርጎባ መስለውን ነው የሚል ነበር፡፡where are we going guys?

  2. Tesfa,
    Work for a country, not for a tribe!
    Ethiopia is our beloved country that has 80 plus tribes living in it. So, please, say, struggle for freedom of Ethiopia and all its people will succeed. Amhara’s victory is not enough to save our country.

Comments are closed.

Share