ወልቃይት የማን ነው? የማይረባ ጥያቄ | ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

ነሐሴ 2008

አንድ

በነገረ አስተሳሰብ ወይም በአስተሳሰብ ሕግ (ሎጂክ) ትምህርት ላይ አንድ የማስታውሰው ምሳሌ አለ፤ ‹‹ሚስትህን መደብደብ ትተሃል ወይ?›› የሚል ጥያቄ ነው፤ ጥያቄው የሚነሣው ጠያቂው አውቃለሁ ብሎ ከያዘው እውቀት ወይም እምነት ነው፤ ስለዚህም ጠያቂው የሚፈልገው ጥያቄ ለማስተላለፍና መልስ ለማግኘት አይደለም፤ ጠያቂው የሚፈልገው በጥያቄ መልክ የራሱን ‹‹እውቀት›› ወይም እምነት ለተጠያቂው ለማስተላለፍና ተጠያቂውን የጠያቂው ደቀ መዝሙር ለማድረግ ነው፡፡

ሚስትህን መደብደብ ትተሃል ወይ? መልስ የሌለው ጥያቄ ነው፤ ‹‹አዎ›› የሚል መልስ ሰውዬው ሚስቱን ሲደበድብ እንደነበረ አመነ ማለት ነው፤ ‹‹አልተውሁም›› ከአለ በራሱ ላይ መሰከረ፤ ሁለቱም መልሶች ተጠያቂውን የሚያስወነጅሉ ስለሆኑ መልስ አይደሉም፤ ከዚያም በላይ ጥያቄው ትክክል አይደለም፤ የማይረባ መጥፎ ጥያቄ ነው፡፡
‹‹ወልቃይት የማን ነው?›› የሚለው ጥያቄ ትክክል አይደለም፤ የማይረባና መጥፎ ጥያቄ ነው፤ ጠያቂው የሚፈልገው መልስ የአማራ ነው፤ የጎንደር ነው፤ የትግሬ አይደለም፤ የሚል ነው፤ ነገር የሚገባው ተጠያቂ ጥያቄውን ጠያቂው በፈልገው መልክ አይመልስለትም፤ ሊመልስለትም አይገባም፤ ወልቃይት የኢትዮጵያ ነው የሚል መልስ አይፈለግም፤ የማይፈለግበትም ምክንያት ‹‹ወልቃይት የኢትዮጵያ ነው፤›› ማለት ወልቃይትን ከጎሠኛነት አጥር ስለሚያወጣ ነው፤ የትግራይ አይደለም፤ የአማራ አይደለም፤ የኢትዮጵያ ነው፤ አሁን ትግራይና አማራ የኢትዮጵያ ናቸው፤ ይህ ከተባለ በኋላ ወልቃይት የትግራይ ነው? ወይስ የአማራ? የሚለውን ጥያቄ ማንሣት የጎሠኛነት ጥያቄ ነው፤ የኢትዮጵያዊነት ጥያቄ አይደለም፤ ጥያቄው የማይረባ የሚሆንበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው፤ ሁለተኛው ምክንያት የጎሠኛ ጥያቄ በመሆኑ የወያኔን የጎሠኛ መመሪያ የሚያከብር መሆኑ ነው፡፡
ትልቁና መሠረታዊው ጥያቄ በአማራ ክልል ስር የነበረው ወልቃይት በወያኔ አገዛዝ ወደትግራይ ክልል መግባቱ ነው፤ እዚህ ላይ ጥያቄው የወልቃይት ወረዳ ወይም አውራጃ ነው፤ በውስጡ የሚኖሩት ሰዎች የጎሣ ዓይነት ወይም የጎሣ ስብጥር አይደለም፤ የፈለገውን ዓይነት አንድ ጎሣ ወይም የብዙ የጎሣ ስብጥር ሊኖርበት ይችላል፤ ክርክሩ መሆን ያለበት የወልቃይት አውራጃ ከጎንደር ክልል ወጥቶ ወደትግራይ የገባበት መንገድ ትክክል አይደለም፤ የአስተዳደር ለውጡ የተፈጸመው የፌዴራል መዋቅሩን ሥርዓት በጣሰ መንገድ አንዱ ክልል (ትግራይ) በሌላው ክልል ላይ የጉልበተኛነት ወረራ አካሂዷል ነው፤ ይህ ወረራ ሕጋዊ አይደለም፤ ይህ ወረራ ሊቀለበስ ይገባል፤ ዋናው መቋጠሪያ ይኸው ነው፡፡
ግን ጉዳዩን የጀመርነው ከመሀሉ ነው፤ ሲጀመር ወያኔ ከኦሮሞ ቡድኖች ውስጥ ኦነግን መረጠና አማርኛ ተናጋሪውን አለ እያለ እንደሌለ ቆጠረው፤ በዚያን ጊዜ ኦሮሚኛ ተናጋሪዎቹም ኢፈትሐዊነቱን አልተናገሩም፤ ዋና የፖሊቲካ ጉዳይ አድርገው አላነሱትም፤ ለምን? እነሱ በሎሌነት በመመረጣቸው በደስታ ተውጠው ስለነበረ ጌቶቻቸውን ለማስቀየም ፍላጎት አልነበራቸውም፤ ግን ወያኔ በእጁ ያሉትን ምርኮኞች ከአደራጀ በኋላ ኦነግ ተባረረና በኦሕዴድ ተተካ፤ የኦነግ መሪዎች አገር ውስጥ ሆነው ለመታገል የሚያስከፍለውን ዋጋ ላለመክፈል በአሜሪካና በአውሮፓ ተቀምጠው በስልክ ‹‹ትግሉን›› መምራት መረጡ፤ ወያኔ አነግን በብዙ መንገድ ተጠቅሞበታል፤ አንደኛና ዋናው አማርኛ ተናጋሪውንና ኦሮምኛ ተናጋሪውን ለመለያየትና በቅራኔ ለማጋጠም፤ ሁለተኛ የኦሮሞ መሪዎች ነን የሚሉ ሁሉ ለወያኔ ትሑት አገልጋይ ከመሆን ሌላ አማራጭ እንደሌላቸው አረጋገጠላቸው፤ ኦነግንና እስላማዊ ኦነግን አፋጅቶ በኦሕዴድ አጋዥነት ሁለቱንም ከትግል መድረኩ አስወጣቸው፡፡
አለ ተብሎ እንደሌለ የተቆጠረው አማርኛ ተናጋሪው በነታምራት ላይኔ፣ በነበረከት ስምዖን፣ በነህላዌ ዮሴፍ፣ በነተፈራ ዋልዋ፣ (ሁሉም ያለጥርጥር አማርኛ ተናጋሪዎች ናቸው፤ ነገር ግን ከየት ከየት እንደበቀሉ አጠራጣሪ ነው፤) ተወከለ፤ ከጎንደርም ይሁን ከጎጃም፣ ከወሎም ይሁን ከሸዋ የእነዚህን ሰዎች ውክልና የተቃወመ የለም፤ እንዲያውም ለአሽከርነቱ ውድድር ነበር፤ በሁለቱ ድርጅቶች — በብአዴንና በኦሕዴድ — አማካይነት ወያኔ ወደሰባ በመቶ የሚጠጋውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በቁጥጥሩ ስር አደረገ፤ ይሄ ሁሉ ሲሆን በአገር ውስጥ ያሉት የአማርኛ ተናጋሪውና የኦሮምኛ ተናጋሪው ወኪሎች ነን ባዮቹ ለፍርፋሪ ሲፎካከሩና ሲነታረኩ ወያኔ የራሱን ክልል በትምህርትና በልማት ለማሳደግ እየሞከረ ነበር፡፡
ለእኔ ፍሬ ነገሩ አማርኛ ተናጋሪውም ሆነ ኦሮምኛ ተናጋሪው ሃያ አምስት ዓመታት ሙሉ እየተፎካከሩ ወያኔን ከማገልገል ሌላ መብትና ሥልጣን ፈልገው አያውቁም፤ ስለዚህም ከማይናገር ከብቱን፣ ከማይራገጥ ወተቱን እንደተባለው ወያኔም በከብቱም በወተቱም ተጠቀመበት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፍትህ የተጠማች ነብስ (Video)

ሁለት

በ1996 ዓ.ም. የክህደት ቁልቁለት በሚል ርእስ ትንሽ መጽሐፍ አሳትሜ ነበር፤ በዚያ መጽሐፍ ውስጥ በገጽ 96ና 97 መሀከል ካርታዎች አሉ፤ ከነዚህ ካርታዎች አንዱ የኢጣልያ ምሥራቅ አፍሪካ (AFRICA ORIENTALE ITALIANA) 1928-1933 ዓ.ም. የሚል ነው፤ በዚያ ካርታ ላይ ፋሺስት ኢጣልያ ትግራይን በሙሉና አፋርን በሙሉ በኤርትራ ክልል ውስጥ አድርጎት ነበር፤ በደቡብም የኢጣልያን ሶማልያ ወደሰሜን ገፍቶ ኦጋዴንን በሙሉና ግማሽ ባሌን ጨምሮበት ነበር፤ ምዕራቡን ክፍል — ወለጋን፣ ኢሉባቦርን፣ ጋሞ ጎፋን፣ ሲዳሞን በአንድ ላይ አስሮ ጋላና ሲዳማ የሚል ስያሜ ሰጥቶት ነበር፤ ሀረር ሰሜን ባሌንና አርሲን ጠቅልሎ ነበር፤ ወያኔም ከፋሺስት ኢጣልያ የወረሰውን አስተሳሰብ ይዞ የጎሣ ክልሎችን ፈጠረ፤ በዚያን ጊዜ ግማሹ እልል እያለ ግማሹ እያጉረመረመ ተቀበለ፤ በዚህም ሥርዓት አንድ ትውልድ በቀለና በጫትና በጋያ አደገ፡፡
ወያኔ የበቀለበትን ትግራይን ሲያይ አነሰችው፤ በዚያ ላይ በሰሜን በቂልነት ደም ከተቃባቸው ከኤርትራውያን ጋር በደቡብ ደግሞ የሥልጣን ችጋሩ ጠላት በአደረጋቸው ኢጣልያ ‹‹አማራ›› ብሎ በከለላቸው ሰዎች በጎንደርና በወሎ በኩል ታፍኗል፤ በዚያ ላይ በትግራይ ውስጥ ካለው የእርሻ መሬት የተሻለ በጎንደርና በወሎ አለ፤ ጉልበተኛ ሆኖ መቸገር አይበጅምና በጊዜ፣ በጠዋቱ ከጎንደርም ቀንጨብ፣ ከወሎም ቀንጨብ አደረገና አበጠ፤ ሲያብጡ ቦታ ይጠብባል፤ ስለዚህ ወደቤኒ ሻንጉልና ወደጋምቤላ በመዝለቅ ሁለት ዓላማዎችን ማሳካት ይቻላል፤ አንደኛ ትግራይ ሰፊ ይሆንና በእርሻ ልማት የሚከብርበት ተጨማሪ መሬት ያገኛል፤ ሁለተኛ ጠላት ብሎ የፈረጀውን አማርኛ ተናጋሪ ሕዝብ የውጭ ንክኪ እንዳይኖረው ያፍነዋል፤ ከሱዳንም ጋር ጊዜያዊ ወዳጅነትን በመሬት ይገዛል፤ የወያኔ የእውቀትና የብስለት እጥረት ከብዙ ትንሽም ትልቅም ኃይሎች ጋር ያላትማቸዋል፤ ሱዳንን በመሬት በማታለል ሱዳንን ከደቡብ ሱዳን፣ ከኤርትራ፣ ከግብጽ፣ ከሳኡዲ አረብያ፣ ከየመን፣ ከሶማልያ … መለየት የሚችሉ ይመስላቸዋል (ልክ አማርኛ ተናጋሪውንና ኦሮምኛ ተናጋሪውን እንደለዩት)፤ የተዘረዘሩት አገሮች ሁሉ በሱዳን ላይ ከወያኔ የበለጠ ጫና ማድረግ የሚችሉ ናቸው፤ አሜሪካን ለብቻው ብቻ ሳይሆን ከነዚህ አገሮች ጋር አብረን ስንገምተው የወያኔን ደካማ ሁኔታ ለመገንዘብ ቀላል ነው፤ በአካባቢያችን ከአሉት አገሮች ሁሉ ወረተኛ የውጭ አመራር ያለው ሱዳን ነው፤ ሱዳን የኤርትራን መገንጠል የደገፈው በአሜሪካ ጫና መሆኑን አንርሳ፤ ለማንኛውም አሁን በወልቃይት የተጀመረው ውጊያ ከቀጠለ የወያኔና የሱዳን የጓዳ ጨዋታ ያበቃለታል፡፡
ጉዳዩ ሰፊ ጥናት የሚያስፈልገው ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጥያቄው ሃይማኖታዊ ነፃነት መብት ወይስ ፖለቲካዊ ……

ሦስት

ወደየጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ስንመለስ፡– ጥያቄው በቁሙ የወልቃይት-ጸገዴ ተወላጆች እንዳቀረቡት ሲታይ የወያኔ አገዛዝ ሃያ አምስት ዓመታት የደከመበት የጎሠኛ ሥርዓት ቢያንስ በአስተሳብ ደረጃ የተሳካ መሆኑን ያረጋግጣል፤ የኢትዮጵያ ሕዝብም ከጎሠኛ አስተሳሰብ ገና እንዳልወጣ የሚያረጋግጥ ነው፤ በሌላ በኩል ደግሞ ወያኔ በጎሣ ሥርዓት እየገዛ በጎሣ ሥርዓት የሚሸነፍ መሆኑ በግልጽ እየታየ ነው፤ ወያኔ ይህንን አዲስ ክስተት ገና አልተገነዘበውም፡፡
ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት ከመለስ ዜናዊ ጋር ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ ተገናኝተን ስንከራከር አማራ የሚባል ጎሣ አሁን የለም፤ ግን አንተ ትፈጥረዋለህ ብዬው ነበር፤ ገና በሕጻንነት ነው እንጂ አሁን ተፈጥሮአል!
በደቡብ አፍሪካ ኔልሰን ማንዴላ በእስር ላይ በሚንገላታበት ጊዜ ደ ክለርክ የሚባለው የደቡብ አፍሪካ መሪ ማንዴላን ከእስር አስወጥቶ እንደአኩያው በጠረጴዛ ዙሪያ ተነጋግረው የሁለቱ ተቃራኒ መሪዎች መተማመን የደቡብ አፍሪካን ችግር ለጊዜው ፈታው፤ ማንዴላ በክብር ሞተ፤ ደ ክለርክ በክብር ይኖራል፤ የሚያሳዝነው በወያኔ አመራር ውስጥ እንደደቡብ አፍሪካዊው ደ ክለርክ ያለ ሰው እንኳን ሊኖር ሊታለምም አይቻልም፤ እንኳን በወያኔ ውስጥ በአገሩም እንዲህ ዓይነት ሰው እንዳይኖር አረጋግጠዋል፡፡
የተጀመረውን ግብግብ ኢትዮጵያ ካላሸነፈች ማንም አያሸንፍም!
ኢትዮጵያ የድንክዬዎች አገር ሆናለችና የገጠማትን ችግር እግዚአብሔር በጥበቡ ይፍታላት!

21 Comments

  1. አመጽ በመጣ ቁጥር በረዶ ለመቼለስ መሯሯጥ አመልህ ነው። አማራ የለም ብለህ ስትከራከር ዕንዳልነበር ዛሬ ደግሞ አማራ አለ ብለህ አወናብድ ተባልህ መሰል አማራ አማራ ማለት ጄመርህ።፡ ነፍጠኛ ነው ወይስ ፖለቲካ ብለህ ማሽሟጠጥም ጄምረሃል! አንተ በጣም የዞረብህ ግትር ሰው ነህ።

    ኢትዮጵያና ሕዝቧ አንተን ዕንደ አንድ ምንደኛ ሰውጂ አንተ ለራስህ ዕንዳለህ ግምት አዋቂና አስተዋይ ብሎ አያስታውስህም። ለሚመጣው ትውልድም ም የአንተን ክፋትና አድርባይነት ግጥም አርገን ዕንነግረዋለን።

    • ልክ ብለሃል ይህን አድርባይ የአማራ ህዝብ ጠላትነቱን ሳይታክት የሚለፍፍ

    • በጣም የምትገርም አሽቃባጭ ነህ።እዉነቱ ሲገለፅብህ፣ የዘራኸዉ/ችሁት ቆሻሻ የዘረኝነትና የጎሳ ፖለቲካ ሲጋለጥባችሁ እንደ እብድ ዉሻ ያክለፈልፋችኋል።ሁሉ በእጁ የሆነዉ ጌታ ፈጥኖ የጃችሁን ይስጣችሁ።
      አሚይን።

  2. ኧረ ጉዱ ካሳ ምን ነካህ ደግመህ አንበው በጣም ጥሩ እና ሙሉ እውነትነት ያለው ነው። እንዴት እንዳየኸው አልገባኝም

  3. ይሄ ወልቃይት የ ኢትዮጵያ ነው የሚለው መልስ በጣም ኣደገኛና አሳሳች አቀራረብ ነው። ልክ ኢትዮጵያ፥ ባለለቤት የሌላት ባዶ ቤት እንደሆነች አስመስሎ በመሳል ማንም እየተነሳ ዕኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ መሬቱም የኢትዮጵያ ስለሆነ ያለ ጠያቂ መሬት መዉሰዴ ትክክል ነው የሚል መከራከሪያ አንዲያቀርብ ሁኔታዎችን ያመቻቻል። ፕሮፌሰሩ ዐማራ የለም የሚል ስብከት የጀመሩት ዛሬ አደለም። ውሸት መደጋገም ለምን እንደረጡ ግን ፈጣሪ ብቻ ይወቀው።

  4. If wolkayet is Ethiopia, why TPLF /WOYANE take snd demarcated wolkayet to Tigraye region from GONDER . therefore, Wolkayet is the GONDER tereitory and Ethiopia.

  5. prof. you have understood the situation correctly. the other commentee please read it agian. The guy is realy a thinker!

  6. I am so sorry for these people who insult this great man. If weyane had insulted him, it could be ok, because weyane is a sub human(dirty creature of God). But i didn’t expect such an isult from my another country men. The article is very good. Ethiopian people should respect and love each other.

  7. ye he sewye demo biq ale ?

    mesfin ere tewen pls !!

    edmehin mulu yetelat selay ena tsre Amara neh

    ahun Amara yemelewin kal atansa !!

    jajtehal eko man yesemahal ?

    wede gedam giba !!

  8. መስፍን ጩሉሌው እድሜ ይስጣችሁ ለሚመጣው መንግስት አማካሪ ይሆናል አክሮባት ነው ይችልበታል። አቶ አለማየሁ ሞገስ ስለሱ በትነው ነገሩን እሳቸው ሙተዋል እሳቸውን ያገኘ እየመሰለው አማራውን ይመትረዋል። ሰውዬው ኤርትራዊ ነው ይባላል ስራውም የሚያረጋግጠው ይህንኑ ነው ስንት ዘመን ያብጠን ይሆን? ችግሩ የሱ ሳይሆን ስንት አስፈላጊ ጽሁፍ ተጥሎ የሱ መውጣቱ ነው። በጥብጠን ይመችህ ትግሬዎችም ለዚህ ነው የሚወዱህ።

  9. My good professor. Every social, political and economic struggle emerges out of shear and unbearable oppression and brutality. It is not a philosophy generated from a comfortable desk with macciatto in the left and a pen in the right hand.

    Wolakait Tsegede and her people have been raped and pillaged by the brutal woyane cohort for a quarter of a century, indigenous people thrown out of their homeland without mercy nor justification, their (our) women and girls given to the marauding victor as a prize in order to dilute the Amahara blood, and now you philosophize about the order in which such demands should be presented.

    Yes, we need to ask that very question you rejected or rubbished in your article. Who is Tigre, Amhara etc. This is not racism nor is it following in the footsteps of woyane thinking. This is about an identity stolen by force, people prevented fromspeaking their Amharaic language and practice their beautiful culture. This doesn’t make me superior to any one. This is just my identity….A PROUD AMHARA ETHIOPIAN!

    There is a well defined cartographic boundary called the Tekeze river and no one has any right to cross that boundary to forcibly remove the people of Wolkait Tsegede from their homes and farms no matter how infertile the soil is on the other side as you claim. We too have got many millions of mouths to feed.

    So professor, the view from this side is different from yours. I respect you but differ completely in my understanding of the situation on the ground. We are at war. Genocide is being committed against the Amhara people and an urgent action is needed to stop it. Your article doesn’t contribute any substance to the objective situation. If you can add a bit of reality to your thinking we will all benefit. Long live Ethiopia.

  10. ጉዱ ካሳ አቦ ጉድ ይፍላብህ በል ሁለተኛ ምሁር አትዳፈር አንተ የሳምራ classmate

  11. የእኛ ቤት ጉድ!
    ” አለ ተብሎ እንደሌለ የተቆጠረው አማርኛ ተናጋሪው በነታምራት ላይኔ፣ በነበረከት ስምዖን፣ በነህላዌ ዮሴፍ፣ በነተፈራ ዋልዋ፣ (ሁሉም ያለጥርጥር አማርኛ ተናጋሪዎች ናቸው፤ ነገር ግን ከየት ከየት እንደበቀሉ አጠራጣሪ ነው፤) ተወከለ፤” አፍ ያለው ጥሬ ይቆላል!
    “ኢዴኃቅን ካጠፋን በኋላ ገብሬውን አማራ በፓለቲካው ያደራጀናቸውና ያነቃናቸው እኛ ነበርን የግድ የአማራ ብርሔር ባይሆኑም “በአመለካከቱ “የሚወክሉት መረጥንለት ብሎ ለገሠ መለሰ ዜናዊ ሲያናፋ አማራ አልነበረም !።
    ” ከጎንደርም ይሁን ከጎጃም፣ ከወሎም ይሁን ከሸዋ የእነዚህን ሰዎች ውክልና የተቃወመ የለም፤ እንዲያውም ለአሽከርነቱ ውድድር ነበር፤ “ታማኝ ጓዶች !”
    “ሰዶ ማሳደድ ሲያምርህ አገርህን በክልል ለውጥ ”
    *** በሁለቱ ድርጅቶች — በብአዴንና በኦሕዴድ — አማካይነት ወያኔ ወደሰባ በመቶ የሚጠጋውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በቁጥጥሩ ስር አደረገ፤ ይሄ ሁሉ ሲሆን በአገር ውስጥ ያሉት የአማርኛ ተናጋሪውና የኦሮምኛ ተናጋሪው ወኪሎች ነን ባዮቹ ለፍርፋሪ ሲፎካከሩና ሲነታረኩ ወያኔ የራሱን ክልል በትምህርትና በልማት ለማሳደግ እየሞከረ ነበር፡፡”
    እንደማጎብደድና ጭነት የመቻል አቅማቸው ልክ አዲስ ታሪክ እየፈጠረ ታሪክ ሰሪ (መሰሪ) በክልል አስሮ በጫካ ማኒፌስቶ አደንዝዞ በጡትና ወሸላ ሥር ባዶ ሆዱን ፡በባዶ እግሩ ባዶ ቂጡን እየመታ ሲያስጨፍረው በሕገ መንግሥታዊ ጥቅማጥቅም ልቡ ተደፍኖ ዓይኑ ታውሮ ፱፭ ዓመት ትውልድ መከነ ባከነ ።

    “ለእኔ ፍሬ ነገሩ አማርኛ ተናጋሪውም ሆነ ኦሮምኛ ተናጋሪው ሃያ አምስት ዓመታት ሙሉ እየተፎካከሩ ወያኔን ከማገልገል ሌላ መብትና ሥልጣን ፈልገው አያውቁም፤ ስለዚህም ከማይናገር ከብቱን፣ ከማይራገጥ ወተቱን እንደተባለው ወያኔም በከብቱም በወተቱም ተጠቀመበት!። “እያነቡ እስክስታ !”

    >> አሁን አማራ አለሁ እራሴን ወክዬ ሀገሬን ስጡኝ ቤተሰቤን ኦሮሞውን አትንኩ! አለ ኦሮሞ ቀበሌና መንደር የኔ(ኬኛ) ከማለት ጎንደር የእኔ ነው! አለ ውስጠ ወይራው “ኢትዮጵያ የእኔ ናት!” ማለቱ ነው ።አራት ነጥብ።

    = ኦሮሞ ከስህተቶቹ ተምሮ በሰላምና የዲሞክራሲ ግንባታ ቀዳሚውን ሥፍራ ይዞ ታሪካዊ ለውጥ እና የሕዝብን አመኔታን ያገኝ ይሆን ? ከእንግዲህ ኢትዮጵያ የኦሮሞ አደለችም የሚል ሻቢያ እና ህውሐት ይፈጥራሉን?
    ** አለሁ! ያለው አማራ በእርግጥም አንድ ሆኖ በዳግማዊ ብአዴን ሳይጠለፍ ይዘልቅ ይሆን ? ሞረሽ ወገኔ .. ቤተ ንፉጋን ..ቤተ አምሐራ የሚልም ዓርማው ምንም የኢትዮጵያ ሠንደቅ የሌለው ጭልፊት ይሁን ሲላ ወይም ንሥር ማንነቱንና ምንነቱን ያልተለየ በድረ ገፆች ላይ ሲያንዣብብ ይታያል :ያለው ከብዶናል ወንዝና ተራራ እየቆጠርን ጨርቅ በቀለም እየነከርን መንደራዊ ብሔርተኝነትን ቀፍቅፈን በጎጥ በነገድ ሻክላ እንዳንተባተብ አደራ በለው!

    የተማረ እያስተማረ ያልተማረ ይማራ
    ብርታትና ድል ለተገፋው አማራ!

  12. Professor jaju meselegne weys yegonder telacha new aferkubewet men yagergu mestewote tegri nate. Del lethiopia hezbe!

  13. Please guys. let#t keep this civilised. it is very simple to insult an old respected ethiopian intellectual but very difficult to think like him or at least follow his logic. he doesn’t say this fight in wolkayit is useless, what he saying ist simple. the question 2does Wolkayine belong to Amhara or Tigrea?” is that what the woyene wants to hear. the question should be who should administer Wolkayit not to whom belongs wolkayit? it belongs to all ethiopians. every ethiopian should be able to live, work and prosper in any part of our beloved country. there should be no restriction in this matter. This is what we are fighting for. Not to divide people according to their ethnicity. there has been and will be tigreans in wolkayite who are decent people who want to live and work there and prosper if they are lucky. they will do so also in the future but the adminstration should be under the Gonder zone. we have nationalize the question and not restrict it to one Awraja. it has been ignited now it has to broaden itself. be aware of those who still want to ride and ride the ethnic demon deguise themselves as the real fighters for wolkayite, they are not helping the national struggle for freedom and democracy. let’s keep discussing.

  14. እናንተ ምን ሆናችው ሀሣብ ካላችሁ ግለፁ ሥድብ ምን አመጣው ሥማችሁን በenglish መፃፋ ሣችሉ መሣደብ ተገቢ አደለም

Comments are closed.

Share