በደቡብ ሱዳን ጁባ ውስጥ በተደረገ ግጭት በርካታ ወታደሮች የሞቱ መሆናቸው ተነገረ (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች)

ሐምሌ 02 ቀን 2008 ዓ.ም. ዜና (July 09, 2016 NEWS)
#ለሁለት አመት ጊዜ በወያኔ እስር ቤት ሲሰቃይ የነበረው አብርሃ ደስታ ተፈታ
#በደቡብ ሱዳን ጁባ ውስጥ በተደረገ ግጭት በርካታ ወታደሮች የሞቱ መሆናቸው ተነገረ
#ሙጋቤ በቅርቡ በአገሪቱ ውስጥ የተካሄደው የስራ ማቆም አድማ ምክንያቱ ምዕራባውያን ናቸው አሉ
#በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ በፈንጅ ስድስት ሰዎች ተገደሉ

ሐምሌ 2 ቀን 2008 ዓ.ም.

ርዕሰ ዜና

  •   ለሁለት አመት ጊዜ በወያኔ እስር ቤት ሲሰቃይ የነበረው አብርሃ ደስታ ተፈታ
  •   በደቡብ ሱዳን ጁባ ውስጥ በተደረገ ግጭት በርካታ ወታደሮች የሞቱ መሆናቸው ተነገረ
  •   ሙጋቤ በቅርቡ በአገሪቱ ውስጥ የተካሄደው የስራ ማቆም አድማ ምክንያቱ ምዕራባውያን ናቸው አሉ
  •   በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ በፈንጅ ስድስት ሰዎች ተገደሉዝርዝር ዜናዎች
  •   በወያኔ ባለስልስልጣኖች ላለፉት ሁለት ዓመታት በግፍ ታስሮ ሲሰቃይ የነበረው አብርሃ ደስታ ዓርብ ሐምሌ 1 ቀን 2008 ዓም. ከእስር የተፈታ መሆኑ ታውቋል። የመቀሌ ዩኒቨርስቲ የፊሎሶፊ መምህር የነበረውና በተያዝበት ወቅት የአረና ትግራይ የአመራር አባል ሆኖ የነበረው አብርሃ ደስታ በወያኔ አገዛዝ አስከፊነት ላይ በመገናኛ ብዙሃን አማካይነት የሰላ ሂስ ሲያካሄድ መቆየቱ ይታወቃል። ከአብርሃ ደስታ ጋር የተያዙት የአንድነት ፓርቲ አባላት ሃብታሙ አያሌው እና ዳንኤል ሽበሺ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲው የሺዋስ አሰፋ ለተወሰነ ጊዜ በእስር ሲሰቃዩ ከቆዩ በኋላ ሲለቀቁ አብርሃ ደስታ ግን ፍርድ ቤቱን ተጋፍተሃል በሚል ክስ አንድ ዓመት ከአራት ወር ለሚሆን ተጨማሪ ጊዜ እንዲታሰር ተደርጓል። ሌሎቹ ሶስቱ ቀደም ብለው ቢለቀቁም አቃቤ ህጉ ይግባኝ በማለቱ ጉዳያቸው ተንጠልጥሎ ይገኛል። ሃብታሙ አያሌው በእስር ቤት በነበረበት ጊዜ በቶርቸር ምክንያት የደረሰበትን የጤና መታወክ ለመታከም ወደ ውጭ እንዲወጣ ቢጠየቅም አገዛዙ አሻፈረኝ በማለት ከልክሎታል።
  •   ትናንት ሐምሌ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ በሪክ ማቻር ወታደሮችና በመንግስት ወታደሮች መካከል የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ የዋለ መሆኑን ከቦታው የተገኘው መረጃ ይገልጻል። የተኩስ ልውውጡ በመጀመሪያ ለሰላሳ ደቂቃ ያህል የተደረገው ከፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግስት ቅጽር ግቢ ውጭ የመንግስት ወታደሮች የማቻር ወታደሮች የሚሄዱበትን መኪና ለማስቆም ሙከራ ሲያደርጉ መሆኑ ተገልጿል። ይህም ቀደም ብሎ በአንድ የመፈተሻ ጣቢያ
ተጨማሪ ያንብቡ:  ፋኖ ማን ነው? ፋኖ አስከብሯል

በተደረገ ግጭት አምስት የመንግስት ወታደሮች በሞቱ ማግስትና ፕሬዚዳንት ሳልቫኬርና ሪክ ማቻር በጉዳዩ ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ ለመስጠት በሚዘጋጁበት ወቅት መሆኑ ታውቋል። አርብ ቀንና ማታ በሁለቱ ወገኖች መካከል የተኩሱ ልውውጥ በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች የቀጠለ ሲሆን በርካታ ወታደሮች መሞታቸውን የሆስፒታል ምንጮች ይናገራሉ። በሁለቱም ወገኖች ያሉ አክራሪ ወገኖች በእርቅ ስምምነቱ ላይ እምነት ስለሌላቸው በደቡብ ሱዳን ተፈጠረ የተባለው ሰላም ብዙ ችግር ያለበት መሆኑ እየታየ ነው። የተመድ ዋና ጸሐፊ ባንኪ ሙን በሁለቱም በኩል በእርቁ ስምምነት ላይ እምነት ማጣት የሚታይ መሆኑን ገልጸው ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ በጣም ሊበላሽ እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል። ከጸጥታው በተጨማሪ አገሪቱ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ተዘፍቃ ትገኛለች።

  •   የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በቅርቡ አገሪቱ ውስጥ ለተካሄደው የስራ ማቆም አድማ ምክንያቱ የምዕራብ መንግስታት ናቸው በማለት ክስ አሰምተዋል። መንግስት የሰራተኞች ደሞዝ በወቅቱ ለመክፈል ያልቻለበት ምክንያት አሜሪካና የአውሮፓ አገሮች የኢኮኖሚ ማዕቀብ ስላደረጉብን ነው በማለት ወቀሳቸውን አቅርበዋል። ባለፈው ማክሰኞ የዚምባዊ የመንግስት ሰራተኞች፤ ዶክተሮችና መምህራን ደሞዝ በወቅቱ ስላልተከፈላቸው የስራ ማቆም አድማ ያደረጉ ሲሆን ሐሙስ ዕለት ደሞዝ ስለተከፈሉ ወደ ስራ ገበታቸው የተመለሰ መሆኑ ታውቋል።
  •   አርብ ሐምሌ ቀን 2008 ዓም በናይጄሪያ ሰሜን ምስራቅ ዳምቡዋ በሚባለው ቦታ አንድ አጥፍቶ ጠፊ በአንድ መስጊድ ውስጥ ባፈነዳው ቦምብ ስድስት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች በርካታ ሰዎች የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል። ባለፉት ሰባት ዓመታት በቦኮሃራም እንቅስቃሴ ምክንያት ከ20 ሺ ሰው የሆኑ ዜጎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን 2.6 ሚሊዮን ሕዝብ ቤት ንብረቱን ጥሎ እንደተሰደደ ተዘግቧል። የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች በአካባቢው 50 ሺ የሚሆኑ ሕጻናት በምግብ እጥረት እንደሚሰቃዩ ገልጸው አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንዲሰበሰብ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ:  ምክር ቤቱ በግራ አጥቅቶ ግብ አስቆጠረ
Share