ጵጵስናና ፈተናው – ክፍል ሁለት

በአለፈው ጽሁፋችን የቤተክርስቲያንን መከፋፈልን እንደመልካም አጋጣሚ ቆጥረው ክፍፍሉን የሚያጠናክሩ ሰዎችና፤ የጵጵስና ተግዳሮቶችን / ፈተናዎችን/ ለመዳሰስ ነጥቦችን በይደር ማስቀመጣችን ይታዎሳል ። ችግሮቹንና ከችግሮቹው ጀርባ ያለው በጎ ገጽታ በሁለት ምድብ ከፍለን እንቃኛለን። ለዛሬው ከችግሮቻቸው እንጀምር።
ችግሮቹና የችግሩ ባለቤቶች
የመጀመሪያዎቹ የአቢያተክርስቲያናት መከፋፈል የሚያመጣውን ጉዳት የማያውቁ ፤ ከክፍፍሉ በኃላ የተፈጠሩ ወይም የተገኙ በአንድም በሌላ ምክንያት ወደአካባቢው የፈለሱ ናቸው። እነዚህ በአሉበት አካባቢ ቤተክርስቲያን የሚገለገሉ ሁነው ያሉበት ቤተክርስቲያን በምንምክያት እንደመሰረተ የማያውቁ ናቸው። እነዚህ በተለምዶ ገለልተኛ የሚባሉት ናቸው ስለገለልተኛ ጥሩነት የተሰበኩ ሲሆኑ ካህኑን በገዘብ እየገዙ ማን ይሹመው፣ ከየት ይምጣ ፣ ሳያጣሩ የጳጳስ ስም መጥራት የሌለበት መሆኑን ነግረው የቀጠሩበት ቦታ ማለት ሲሆን ። ይህ ቦታ በባለ አባቶች ወይም የቦርድ ሜምበር የሚመራ የሚመስል ፤ አንዳዶቹ የእድሜልክ ፣አንዳዶቹ ሃላፊነትን በማሸጋሸግና ጊዜ በመቀያየር የሚያዙበትና የሚናዝዙበት ቦታ ነው። አገልጋዮችንም እንደ ቤተክርስቲያን ህግ ሳይሆን የሚመሩት መስሎ የመኖር ያዋቂ አጥፊ የሚባሉት አይነቶች ናቸው። የእነዚህ ሰዎች አባላት በቅዳሴው ላይ እግር ጥሏቸው: እነሱን ወደ ማይመስል በስደት ወይም በሀገር ቤት በአለው ሲኖዶስ በሚመሩት ቤተክርስቲያን ሲሄዱ መጠነኛ ለውጥ መኖሩን የሚሰሙና ያሉበት የተሻለ እንደሆነ አምነው የሚኖሩ ናቸው። ከእነሱ ውጭ በአሉት አቢያተክርስቲያናት የሚገለገል ሃጢያተኛ የሚመስላቸውም አይታጡም ። የሚበዙት የመሃል አገር የሚባሉት ሰዎቸ ቤተሰቦች ናቸው። እነዚህ በሃገር ቤትም ሆነ በውጭ ያለውን ሲኖዶስ በመንቀፍ የሚቀድማቸው የለም። አንድ ጳጳስ ተሳሳተ ተብሎ ሲነገር እነሱ ያለ ጳጳስ መኖራቸው እንደጄብድ የሚቆጥሩ ሁነዋል ። እነዚህ የችግሩ አካል የፈጠረውን ክፍተት የሚያሰፉ በእውቀትም ያለእውቀትም የቤተክርስቲያን አንድነትና ጽናትን የሚፈታተኑ ሁነዋል፡፡ ለነገው ትውልድ አንድነት ፈተና እንዲሆን ታስቦ በተከፈተው ጎዳና የሚጓዙ ናቸው።
ሁለተኛዎቹ በማህበራዊ ኑሮ አብረው የሚኖሩ ግን እኔበልጥ እኔበልጥ፤ እኔን ስሙኝ እኔ ስሙኝ የሚሉ ሰዎቸ ይበዙበታል:: ይህ ቡድን ቤተክርስቲያንን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰድ ፖለቲካውንም፣ በማሃበራዊ ኑሮውንም፣ በጋራ አጣምረው መምራት የሚፈልጉ የሚበዙበት ነው። ሃይማኖታቸውን ብቻ ማራመድ የሚፈልጉሰዎች በቁጥር አንሰው ግብግብ የሚፈጠርበት ቦታ ነው ማለት ይቀላል ። በዚህ ቦታ የሚነሳው ነገር በቀላሉ የማይበርድ ይሆናል ። የፓርቲውም የመንደሩም ጉዳይ ተጨማምሮ አብረው የኖሩት ለመቃብር እንኳን የማይቆሙበት ደረጃ ይደርሳሉ። ይህ ጉዳይ አሁን አሁን ነገር አዋቂዎች የሚያቀጣጥሉት እሳት እየሆነ ነው። በጥብቅናና በአስተርጓሚነት፣ በነገር አዋቂነት ስም ጠቀም ያለ ገንዘብ ማግኛና የጊዜ ማሳለፊያም ወደመሆንም እየተሸጋገረ ሂዷል ። እነዚህ ሰዎች ጳጳሳትን የሚፈልጉት ለቡራኬ ብቻ ነው። አስተዳደራቸውም መንፈሳዊም አለማዊም አይደለም ።
ሦስተኛው እጄ ረጅሙ እግረ አጨሩ መንግሥታችን የሚጫወተው ጌም ነው።
በስደት ያለው ህዝብ በሚሰማውም ይሁን በየጊዜው እያደገ በሄደው የዘር ክፍፍል መንግሥትን አጥብቆ እየጠላ ነው በመሆኑም ይህን ጥላቻ ለመቀነስ ብዙ አባላትን በውጭ ሀገር ማፍራት እንደ ትልቅ ግብ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ነው። አባላቱን የሚመለምልበት ስልት ደግሞ እየረቀቀ ሂዷል። አሁን ጠንካራ ሰዎችን ለመልመል በቀላሉ አልተቻለም በመሆኑም በዋናነት በህዝቡ ውስጥ አለመተማመን እንዲኖር አሉቧልታ የሚያወሩ ሰዎችን በቀጥታም በተዘዋዋሪም ማብዛት ነው።ይህ በተሳካ ሁኔታ የሄደ ይመስላል ለመንግሥት የሚቃዎሙ የሚመስሉ አውቀውም ሳያውቁም ለመንግሥት የሚሰሩ በርካታ ናቸው። መጀመሪያ ሀገርቤት የሚመጣው በሙሉ የወያኔ ቅጥረኛ እንደሆነ አድርጎ ማስወራት ከተቃዋሚው ጎራ እንዳይቀላቀል ቢቀላቀልም እንዳያምኑት የሚያደርግ ነው። ሁለተኛው እከሌም እከሌም ወያኔ ነው ብሎ ማውራት ይህ የተወራበት ሰው እየቆየ ሲሄድ በእልህም ቢሆን በማህበረሰቡ በሚደርስበት ጫናና መገለል የወያኔ አባል እንዲሆን ማመቻቸት ነው። ይህን የሚያደርጉት ሰዎች ለረጅም ጊዜ ተቀዋሚ የሚመስሉ፤የሀገር ፍቅር አለን የሚሉ ናቸው እነዚህ ሰዎች የነሱን ሃሳብ የማይደግፈውን በሙሉ ወያኔ ነው ብለው ማውራት እንደልምድ አድርገውታል። በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚሰሩት ለመንግሥት ነው። የሚበዙት ቤተክርስቲያን የሚሄዱት ቅዳሴ አልቆ ቡና ሊጠጣ ሲል ነው ተሎ ወደቤታቸው አይመለሱም፣ ነገር ይፈልጋሉ ጊዜ የሚያሳልፉበት። እነዚህ የቤተክርስቲያን አንድነትን ከሚፈታተኑት ዋናዎቹ ሁነዋል ። ቤተክርስቲያኒቱን የሚፈልጓት ሰዎች ለማግኘት ብቻ ነው ሰላሟና አንድነቷ ለእነሱ ፋይዳ አይሰጣቸውም። ጳጳሳቱን ለማዘዝ እንጅ ለጳጳሳቱ ለመታዘዝ አያስቡም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Sport: እግርኳሳችን ጀርባ…

አራተኛው የጳጳሳቱ አቀም ውሱንነት የሚፈጠረው ነው፡፡
ብዞቹ አባቶች ህዝቡን እንዴት እንደሚመሩት አያውቁም። የአስተዳደር ልምድ ብቻ ሳይሆን እውቀትም ያሳቸዋል ።ቸግር ሲከሰት እንዴት ማለፍ እንዳለባቸው አልተረዱም፣ ከችግሩ ጋር አብረው ይነጉዳሉ ፡፡ ፖለቲካውን አያውቁትም ለምን እነደሚፈልጋቸው እንኳን አይገነዘቡም። በመሆኑም ከፖለቲከኞች ጋር የማይመጣጠን ጋብቻ ይፈጥራሉ። ጓደኛቸውን የገፋውን ወንበር ይሻማሉ ፡፡ ለህጉ ሳይሆን ለሥልጣኑ የሚያደርጉት ግብግብ በህብረተሰቡ ዘንድ የነበራቸውን ክበር ቀንሶባቸዋል። ቃላቸውን የማይሰማና የማይታዘዝ አማኝ እንዲበዛ አስተዋጾ አድርጓል። የአስተዳደር ብቃታቸውም ዘመኑን ያማከለ አይደለም። ይህ ሃይማኖቱን ለማዳከም ለሚሰሩ ሰዎች እንደጥሩ አጋጣሚ ሁኖላቸዋል። እነዚህ አባቶች እነማናቸው? ምልክታቸው ምንድ ነው? በምን እናውቃቸዋለን? ለምትሉ እንመለስበታለን። እነዚህ ጳጳሳት ከእነሱ ተሽለው ሊሰሩ የሚችሉ ጳጳሳትን ሥራ በማደናቀፍ ይታዎቃሉ። አለመቻል ብቻ ሳይሆን ሊሰራ የሚችለውንም አያሰሩም። የሚበዙት ደካማ ቢመስሉም ጠካራና የሰራ ሰዎች ግን አሉን ይኖራሉም፡፡
አምስተኛው በውጭ ሲኖዶስና በሃገር ቤት ሲኖዶስ የሚተዳደሩ አቢያተከርስቲያናት መዘዝ።
በሀገር ቤቱ ሲኖዶስ የሚተዳደሩት የሚበዙት ትግረኛ ተናጋሪዎችና ያለውን ሥራዓተ-መንግስት የሚደግፉ ናቸው ።ትግረኛ ተናጋሪዎቹ ሥራዓተ-መንግሥቱን የሚቃዎሙ ቢሆኑም እንኳን ወደነዚህ መሄወዱን ይመርጣሉ። ጉዳይ ከፖለቲካ አልፎ ጎሳዊ የመሆን ዝንባሌን ያሳያል፡፡ ጳጳሳቱንም ከፋፍለው ነው የሚቀበሉት ፡ ሃይማኖትና ፖለቲካ መለየት ተስኗቸዋል ። ለትግረኛ ተናጋሪ ጳጳሳት የማድላት አባዜም ይዟቸዋል ። አኩስም የክርስትና ማእከልነቷንና መሪነቷን በዘመን አመጣሽ ፖለቲካ ወደመንደር ይዛው የገባች ትመስላለች ።
በውጭ ሲኖዶስ የሚተዳደሩ አቢያተክርስቲያናት አብዛኛዎቹ አማረኛ ተናጋሪዎችና ሥራዓተ-መንግሥቱን የማይደግፉ ብሉም ጎንደሪዮች ይበዙበታል አማረኛ ተናጋሪዎቹ የመንግሥት ደጋፊዎች ቢሆኑም እንኳን መሄድ የሚፈልጉት ወደእነዚህ ነው። ይህም ከላይኛው አስተሳሰብ የተለየ አይደለም። ከዚህ ላይ የሚደነቁት ኦሮሞኛ ተናጋሪዎቹ ናቸው ቁጥራቸው ያነሰ ቢመስልም ቦታ አይመርጡም ወደአቀረባቸው ቤተክርስቲያን ይሄዳሉ። ፖለቲከኞቻቸው ቤተክረስቲያን የነፍጠኞች ናት ቢሉም፤ ፕሮቲስታቶቹም ኦሮሞ የጴጤ ነው እያሉ ቢወተውቱም፤ እነሱ ግን አልሰሟቸውም እንዴውም ጥንካሪያቸው ጨምሮአል ፡፡ ከላይ የተጠቀሱት፣ በሁለት አቅጣጫ የቆሙ አቢያተክርስቲያናት፡ የሚመሩት በጳጳሳት ቢመስሉም ስደቱ የፈጠረው የፖለቲካ መተራመስና የባህል ተቃርኖ ሚዛናቸውን አዛብቶታል። ያለ ጳጳስ ከሚኖሩትና በሦስተኛ ወገን ከቆሙት ግን በእጅጉ ይሻላሉ
ስድስተኛው ማኀበረ ቅዱሳንና አንቲ ማኀበረ ቅዱሳን ብሎም ተሃድሶዎቹ እየሄዱበት ያለው መንገድ ነው
ማኀበረ ቅዱሳን የሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያለው እንቅስቃሴው የተለያየ እንድምታ አለው:: በውጭ ያለው ፖሊሲው ብዙ ተቃርኖ የበዛበትና ብስለት በሌላቸው ሰዎች የሚመራ የሚመስል ፤ ጥንካሬውም የተሻፈፈ ከነገሮች ጋር የተላተመ ነው። ማኀበሩ በተጀመረ ጥቂት ዓመታት ውስጥ የተከተላቸውና ጥቂት የማይባሉ ጣላቶችን ያፈራበትን ዓመታት ዋጋ ያስከፈሉት ይመስላል። የማኀበሩ የውጭ አመራር በአርቆ አሳቢነት ቢሄድ ኑሮ በውጭ ያለችውን ቤተክርስቲያን ይበልጥ ይረዳ ነበር። ነግር ግን በጉንጭ አልፋ ክርክር ጊዜ አባክኗል። ብዙ ለቤተክርስቲያን አንድነት የሚጠቅሙ ሃሳቦችን በወጣቱ በኩል ማስረጽ ሲችል ቤተክርስቲያን በግል ወደመክፈትና ልዩነት ወደማጠናከር አጋድሏል። አላስፈላጊ ጥላቻዎችንም አትርፏል። በጅምላ ሰዎችን መክሰሱና ራሱን ብቸኛ የሃይማኖቱ ተቆርቋሪ አድርጎ ማሳየቱም አልተወደደለትም፡፡
ይልቁንም ተሰሚነት ያላቸው አባቶች ይዞ ከመስራት ይልቅ እራሱን ለማስቀደም የሄደበት መንግድ አደገኛ ሆኗል ።በሀገር ቤት ከሚሰራው አንጻር ሲገመገም የውጭው የተሳካ አይመስልም።አንቲ ማኀበረ ቅዱሳን የሚባሉት ደግሞ…
ይቀጥላል
ከሊቀ መራህያን
ማንኛውም ሰው እውነቱን ማወቅ ከፈለገ በንጹህ አይምሮ በዚህ እሜል ሊያገኘኝ ይችላል jemis1968@gmail.com

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሃላፊነት የጎደለው ስር አትን  ሃላፊነት በጎደለው መንገድ ለማስወገድ መሞከር አደገኛነቱ  አጠያያቂ አይደለም - ጊሸይ ጊሻ
Share