Hiber Radio: ጽዋ ለመጠጣት የተሰባሰቡ ሰዎች ኦነግ ያደራጃችሁ ናችሁ ተብለው ተከሰሱ – ኦነግ ምላሽ ሰጠ * ረሃቡ 2.2 ሚ. ሕጻናትን እያጠቃ ነው

/
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 2 ቀን  2008 ፕሮግራም

<… በድርቁ ከሰቆጣ ተሰደው በደብረ ብርሃን የሚገኙትን በአምስት መኪና ጭነው ብዙዎቹን ወደመጡበት መልሰዋቸዋል። ድርቁ ጎድቷቸዋል ወገኖቻችንን ተጎሳቁለው አፈር መስለው ማየት ይረብሻል ይሄሳያንሳቸው አትለምኑ ብሎ በፖሊስ ማሳደድ ግን ምን አይነት… >

አቶ አበበ ውቤ የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ በደብረ ብርሃን በድርቁ ሳቢያ ተሰደው ከሰቆጣየመጡትን ወደ ነበሩበት ለመመለስ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ አይቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ    (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…ለማህበር ተሰበሰቡ ሰዎችንም ሆነ ሀሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ አደባባይ ወጥተው በኦሮሞ ሕዝብላይ የሚፈጸመውን በደል የሚቃወሙትን ኦነግ አስታጥቋችሁ መንግስት ልትወጉ ነው ማለት የወያኔ ሸፍጥነው። ወጣቶቹ የወገናቸው ብሶት ቆጭቷቸው ለመብታቸው የተነሱ ናቸውየኦሮሞ ሕዝብ ለመብቱመቆምን  የወያኔ ጥይት፣እስር ሆነ  የፈጠራ ክስ አያቆመውም አንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ ቢል እንኳመስዋዕትነቱን ከፍሎ ለነጻነቱ የሚያደርገው ትግል ይቀጥላል ተዳፍኖ የሚቀር አይደለም ትግሉንሌላውም ሊቀላቀለው ይገባል።የተቃዋሚ ድርጅቶችም …>>

አባ ጫላ ለታ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የውጭ ግንኙነት ሀላፊ በአገር ቤት ባለፈው ሀሙስ ፍርድ ቤት ቀርበውክስ ስለተመሰረተባቸው የኦሮሞ ሰላማዊ ታጋዮች ላይ በመንግስት ላይ ጦርነት ልትከፍቱ  ነበርስለተባለባቸው ክስ ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

የግንቦት 7 አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የመን ላይ አፍኖ ለወሰደው የኢሃ አዲግ መንግስት የደህነነትሰራተኞችን ለማጠናከር  ከሎንዶን መንግስት  የሚጎርፈው የገንዘብ እርዳታ  በተመለከተ  የእንግሊዝመንግስት፣የሰበዊ መብት  ተሟጋቾች እና የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት የሰጡት አስተያየትን ያካተተው  ታዋቂው የእንግሊዝ ጋዜጣ ( ስንድየ  ሚይል ) ያወጣው ወቅታዊ  ዘገባ ሲዳሰስ (ልዩ ሬፖርታዥ)

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: በአሜሪካ 3 ሥራዎች ትሰራ የነበረች ሴት እንደተኛች ሕይወቷ አለፈ፤ ከመከላከያ የከዱ 11 ወታደሮች በእስር ላይ ናቸው

ከአፍሪካ አገሮች እስከ ምዕራባውያን አገሮች የተዘረጋው ዓለም አቀፍ የጉቦ የማቀባበል ቅሌትና ግንባርቀደም ተጠያቂው ዩኒ ኦይል ኩባንያ ገበና ሲፈተሽ (ልዩ ጥንቅር)

<…ከሰቆጣ የመጣነው ረሃቡ አሰድዶን ነው። አሁን ወደ ሰቆጣ ካልሄዳችሁ ያሉት ለሁለት ወር ለአንድቤተሰብ አስራ ሁለት ጣሳ እህል ዕርዳታ እንሰጣለን ከዚያ ውጭ የለም ብለዋልእምቢ ብለን ያልሄድነውአሁን በደብረ ብርሃን ሚስቶቻችን ወጥተው እንዳይለምኑ ፖሊስ እያሳደደድ ነው። ትታሰራላችሁ ብለውያባርሩናል ችግር ላይ ነው ያለነው…> አቶ ይትባረክ ጻድቁ ከድርቁ ተፈናቃዮች አንዱ ለህብር ሬዲዮከሰጡት ቃለ ምልልስ በከፊል(ሙሉውን ያዳምጡት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ 2.2 ሚሊዮን በላይ ህጻናትን ለከፋ አደጋ መጣሉ አለማቀፋዊ  ሰጋትፈጥሯል

በአዲስ አበባ ለማህበር ጽዋ የተሰባሰቡ የኦሮሞ ወጣቶች ኦነግ ልኳችሁ መንግስትን ልትወጉ ነበር ተብለውክስ ቀረበባቸው

የኦነግ ጉዳዩ የወያኔ የፈጠራ ክስ ነው የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄ በዚህማዳፈን አይቻልም ብሏል

አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ  በስልጣን ኮርቻ  ላይ መቆየት ከፈለጉ የባህሪይ ለውጥ እንዲያሳዩ አንድ የአውሮፓህብረት የሕዝብ አንደራሲዎች መሪ ሰሞኑን ተግሳጻዊ ምክር  ሰጧቸው

ከኤርትራ  የከዳው ሞላ አስግዶም መቀሌ ሙስና ሰፈር ላይ ሕወሓት ኢንቨስተር አድርጎ ቦታ መስጠቱተገለጸ

የኬኒያ  አየር መንገድ ፓይለቶቹን ለኢትዮጵያ  አየር መንገድ በተውሶ አሳልፎ ለመስጠት መወሰኑ የናይሮቢ ነዋሪዎችን አነጋገረ

ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቁ የኢትዮጵያ ታጣቂዎች  ኬኒያዎችን አባረው መሬት  መቆጣጠራቸው ተዘገበ

/ ነጋሶ ጊዳዳ የኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ የሚል አዲስ የታሪክ መጽሐፍ ጻፉ

ተጨማሪ ያንብቡ:  አዲስ ዜና - ሰላማዊ ትግል 101 መጽሐፍ በግርማ ሞገስ

የዙምባብዊው / ሮበርት ሙጋቤ  “ይሞታል ብላቸሁ በመመኘታቸሁ አፈርኩባችሁበማለትተተኪዎቻቸውን በነገር ሸነቆጧቸው

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

1 Comment

  1. የትግራይ ፍሺስት መንግስት ኦሮሞን አስሮ እና ገድሎ ለመጨረስ ተንስቷል.

Comments are closed.

Share