ሁሉ ሠው ያንብበው  እንዲነበብ ያድርግሐ

አንቡቡ ተናበቡ የህዝብ ሀሣብና ፍላጎት አድምጡ –
ይድረሥ ለህወሓት  አህአደግ አማራር በየአሉበት;

አቶ አስገደ ገ/ስላሴ

ለመሆኑ እነዚህ መሪዎች  አርሥበእርሣቸው አንብበው  ወይ  ተናብበው  የ90 ሚሊዮን  የኢትዮጱያ  ህዝቦች ፍላጎት  ;የህዝቡ  የፖለቲካ አይደሎጂ ; የሚፈልገው  የአኮኖሚ ፖሊሢ ወይ የሚፈልገው ሥርአት ; ;አሥተሣሠብ( ሣይኮለጅካል ሜክአብ ) ማህበረ ኢኮኖሚያዊ  ማህበራዊ ;ችግሮች ያነባሉን ? እነዘህ ሠዎች 25 አመት የአፈና  ዘመን  አጋዛዛቸው በህዝቦች ላይ ያደረሡት ግፍ የአንድነት  የፍቅር መላላት; ህዝቦችን እርሥ በእርሣቸው  በመጋጨት የከፋፍለህ ሥረአታቸወ ለመሣከት ሢሉ  አገራችን ወደ  የመፈራረሥ  አደጋ ላይ አድርሠዋት እንዳሉ ህዝቡ ያወቃቸው መሆኑ  ያወቃሉን ; ወይ ያነባሉን ?ህዝቡ ከሚኖሩበት ቤት  ወለል ጀምሮ ባገር ወሥጥ ; በወጭ የሚሠሯት; የመዘበሩዋት  የትእንደአሥቀመጧት  በቀጥታ ይሁን  በተዘዋዋሪ ከሸሪኮቻቸው ጋር ሆነው  ያካበቷት ሀብት መላው የኢትዮጱያ ህዝብ አበጥሮ የሚያወቃት መሆኑሥ ያነባሉን ?  ለመሆኑ ይቅርና  ራሣቸው ልጆቻቸው  ዘርመንዝራቸው  ሸሪኮቻየው በ90  ሚሊዮን  የኢትዮጱያ ህዝ የአይን ብሌን ተሠክተው እንዳሉ  ያውቃሉን ? ሥልጣን ከጨበጡባት ዘመን ጀምሮ እሥከ አሁን ድረሥ ለህዝብ የገቡለት ቃል ; አዋጆች መመሪያዎች  ለህዝብ እናደርግልሀለን ብለችሁ  ቃለማሀላ ፈጽማችሁ መካዳችሁ በጥልቀት የሚያውቃችሁና ተቀዩሞዋችሁ እንዳለ  ታነባላችሁ ? ለመሆነ በአሁኑ ጊዜ የኢሀአደግ አባል ፓርቲዎችና አጋሮቻችሁ  ፓርት   ከፓርተ በግለ ፓርትም እርሥ በእርሣችሁ ሥምምነት እንደሌላችሁና እነደተፈረክረካችሁ አንደማትናበቡ;ወደ መጥፎ አሥተዳደግ ያባላሸው ሀጻን ባህሪ እንደተቀየራችሁ;   ህዝብ በጥልቀት ያነበባችሁና አምርሮ የጠላችሁ መሆኑ እያነበባችሁ ነውን;

  ከዚሁ ታሪካችሁ በመንደርደር ከጠ/ም/ሀይለማርያም ደሣለኝ ጀምሮ እስከቀበሌ ድረሥ ; መልካም አሥተዳደረ; ፍትህ የሀግየበላይነት አናረጋግጣለን; ሙሦኛች እንጠራርጋለን  እሥከአሁን  የተፈጸሙት ሥህተቶች ወደ ማንም ጣታችን አንቀሥርም ጥፋተኞችና ተተያቂዎች  እኛው ነን እያለችሁ በነዛ ለውሼት የተቋቋሙ ሚዲያዎቻችሁ  እያሣራጫችሁ ናችሁ;; ለመሆኑ አንደኛ ሙሦኞች ከግንዳቸው ከመታችሁ ማን መቺ ማን ተመቺ ሊሆን ነው?
ሁለተኛ ህዝብሥ ያምነናል በዚሁ እናረጋጋው አለን ብላችሁ የምትጠብቁ ከሆናችሁ አበደን የማይታሠብ ነው;; ምክንያቱም 25  አመት የዋሻቹትን ሁሉ ባዶ እንደሆነ  በጥልቀት በሥፋት ሥለሚያውቅ የምትነግሩን ሁሉ አይቀበላችሁም;;

ተጨማሪ ያንብቡ:  በካልጋሪ ከተማ የኮፈሌ ሰመአትን ለማሰብ በተደረገው ዝግጅት ላይ የቀረበ ማራኪ ግጥም - - በእዝራ ዘለቀ

ሠወሥተኛ ጠ/ ም/ሀይለማርያም  ደሣለኝ በሁሉ መድረክ እየወጡ የሚናገሩት ያሉ ዲሥኩር  ከአንጋፋዎቹ አባታውያንና ከመላው መዋቅራቸው  እየተናበቡ ነውን? በተጨማሪ የተናገሩት ሁሉ ተቀብለውታልን ? አይታሠብም;; ታድያ እኝህ ሠውዬ ማንተማምነው ነው ማንንሥ አይዞህ ቡሎዋቸው ነው?
ጠ/ም  ሀይለማርያም ደሣለነኝ ጠቅለል ያለ ቃል የኢሀአደግና አጋር ፓርቲዎቹ ፍጹም የማይቀበሉት አንኳር  ግለሂሥ አድርገዋል ያአንኳር ሂሥ ደግሞ  በ25 አመት የክፉ ሠርአታችሁ አገዛዝ የፈጸማቸው  የፓርቲዎች መግደል ጭራሹን መደምሠሥ የሚያሠጉዋችሁ ፓርቲዎች በግ ሽፋን ማፍረሥ ; ሥብሠባ ሠላማዊ ሠልፍ  መከልከል;  ገንዘብ ከህዝብ ለመሠብሠብ ከህዝብጋር መገናኜት መዝጋት; የፓርት መሪዎችና አባሎቻቸው ማሠር መገደል ; ካገር መባርር;  ሀቀኛ ነጻፕሬሦች መዝጋት ጋዜጤኞች ማሠር መግረፍ መገደል ተፈጽሞዋል;;

  የአሁኑ ይባሥ ደግሞ ካለፈውን  የቀጠለው የኦሮሞ የፓለቲካ መብቶች;የዲሞክራሢ ጥጥያቄ ; የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ   ወዘተ  መልሥ የተሠጠው  በጅምላ ተገድለዋል በሽዎች ታሥረዋል ;; እንዲሁም በደቡብ ህዝቦች ብሄር ቢሄረሠብ  የመብት የዲሞክራሢ የፍት ጥያቄ  አንሥተው በግድያና በእሡር በመሠቃዮት እየተፈጸመ መጣ አሁንም ግድያ ማሠር ዘር ከዘር እየተላለቀ ይገኛል;; በጋንበላ በአኝዋክና ኒዌር ሀዝብ ; በቤለሻነጎልና አመራ  ከጋንቤለ ወዘተ የዘር ጅምላ እልቂት  ተፈጸሟል ;; በአማራ ቅማንት በሚልም ገድያ ማሠር ተፈጽሟል;;  ትልቅ የዘር ግጭትም  እዬተፈጸመ ይገኛል;; አሁን  ደግሞ የወለቃይት ጸገዴ የይገባናል ጠያቄ በቀላሉ ሊፈታ የሚችል  ከይገባናል በዘለለ  አማራና ትግሬ   ወደሚል የዘር ግጭት  እያመሩት ይገኛሉ::እንዳው በባአዴንና ህወሓት አማራርም  መካከል  ጎራ ለይተው በመፋጠጥ ደረጃ ይገኛሉ ;; በተጨማሪም የሁለቱ መሪዎች የዘር ቅሥቀሣው ወደአደገኛ አቅጣጫ እየገፉት ይገኛሉ :: ሁለቱም በገልጸና በህቡእ በተደራጀ  መንገድ በድህረገጽ  የዘር ህቡእ  ዘመቻ ተያይዘውታል ;; በቅርብ ጊዜ  ከቤተመንግሥት ያፈተለኩ  መረጃዎ እንደሚያሥረዱት ሀይለማርያም ደሣለኝ  ለሀወሓተና ለበአዴን መሪዎች ለመሥታረቅ ተጠምደው ሠንበተው እንዳልተሣካላቸው እና መናናቁ እጅጉን ጣርያ እንደደረሠ  ይገለጻለ::

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጎሕ መንፈስ (በየነ ሞገስ)

ይህ የሚያመለክተው  ሁለቱ ቡዱኖች አቅማቸው ጭራሹ መውረዱ ደግሞ 25 አመት ሙሉ በዝህች አገርና  ህዘቦቻ ያደረሡት በደል የሙሡና ምዝበራ  ህዝብ ሥለአወቃቸው ያንን ለመሸፈንና  የሀዝብን የአሥተሣሠብ  አቅጣጫ  ለመቀዮር ነው:: ለዚሁ ርካሽ ፈላጎታቸው  ህዝብ  ወደግጭት መምራት  ማለት አሥተሣሠባቸው 200 አመት ወደ ኋላ መመለሣቸው  ያሠያል:: ይህ ተግባር የኢትዮጱያ ህዝብ ነቅቶ ይጠበቃቸው:: በተጨማሪም በዬፊናቸው  የድህረገጽ   ጸሀፊዎች አደራጅተው ዘረኛ  የሆኑ  ጸህፎች ያሣራጫሉ  ለነዚህ ቅጥረኞችም  ሁሉ ሀዝብ መቃወም አለበት::በተለይ  አንድ አነድ ሽማግሌ  ሆው አገር እንደመጠበቅ እንደማሥታረቅ : ግጭቶች እንደመፍታት :: እድሜ ልካቸው  ጠባብነት የተጠናወታቸው   ቤት  ለቤት እያድሞነሞኑ  የጠብብ  ዘረኝነት መርዝ የሚረጩ ሤሮኛች  በትግራይም  በአማራም ይገኛሉ  :: አነዚህ ሠዎች ለራሣቸውና ዘርመንዝራቸው  ሸሪኮቻቸው በሙሡና የተጨማለቁና ወራሪዎች  ናቸው;;ለትግራይ ህዝብ  የሚያሥቡ መሥለው የትግራይ ማንነትና ክብር  ሊቀማ ነው መተኛት የለብንም እያሉ ይቀሠቅሣሉ:እነዚህ ሤሮኞች ትግራይ ለመገንጠልና ትግራይ ትግራይ  ትግርኝ  ብለው ኤርትራ ጨምረው የሠሜን ኢትየጱያ  መንግሥት ሊመሠርቱም ያሥቡ  ይሆናል   በመሆኑም እንጠብቃቸው በተለይ ይሀ  ትትውልድ  በሚነዱት  በገንዘብ  መነዳት የለበትም  ::
የህወሑት ኢህአደግ  ሥርአት  25 አመት ሙሉ ለህዝብ በተለያዬ መንገድ  እያታለለ  በሀይልም እጨፈጨፈ   መሣሪያ  የሚሆኑት ደካማ ሙሁራን ተብዮዎችና ድርየዎች  በመሠብሠብ ሥቢል ሠርቢሥ ኮለጅ  በካድረ  ሥልጠና ለብለብ  አድርጎ ዲግሪ ማሥተርሥ ደጉትሬት ወረቀት  ሠጥተው  በየሚበሉበት ቁልፊ ቦታ በማሥያዝ በመላው ሀገራችን በክልሉ ቋንቋ ተናጋሪዎች በመመደብ ቡሉ ወረሩ ቡሎ በመፍቀድ እች ሀገር እንድትወረር አድርጎ ሢያበቃ አሁን መሡና  ከግንዱ እንቆርጣለን ቢለን  እንዴት ብለን እናምናለን??  እነዚህ ሠወች  እኮ ሙሡና ሥርአት አድርገውታል  : የታጠቁ ሀይሎች ሆነዋል :: ታድያ ሀይለማርያም ደሣለኝ  ሙሡና እንመታን ሢሉን ከማን ጋር ሆነው  ለማንሥ ነው የሚሞቱት ?ሚኒሥቲሩ ፓርላማው  ወታደራዊ መኮነኑ  አንባሣደሩ  የክልል የዞን የወረዳ የቀበሌ ንገሦች   መነጋ ተላላኪ  ካድሬ  የአገር ድሀንነት ሊጠብ የተመደበ  መንጋ ድህንነት ወዘተ በሙሉ በሙሡና የተበላሸ ነው :: እነዛ ሸሪኮቻቸውም  ቢሌነሮችና  የታጠቁና  መንጋ  ታጠቂዎችአሉዋቸው :: በዘህች አገር  ያሉ ሙሁራኖች  ተማራማሪዎች  በናንተ አይን የተናቁና የተገለሉ ናቸው :: በጠላትነት አይንም ይታያሉ ::  እነሡም  ግን ፈርተወና  ሠግተው  እችሀገር  ወደምጥ እያሥገባት እየተመለከቱ  ዝመታ መምረጣቸው ነጻ አይሆኑም  :: ሥለሆነ አቶ ሀይለማርያም እንዴት ብለው ነው የሚታገሉት? የዋህነት ያጠቃዎታል:: የምሬን ሀቁን ልንገርዎ በእኔ እምነት  እና መላው  የኢትዮጱያ ህዝብ በሙሉ በሙሡና እጅ አለዎት የሚል እምነት የለውም  ::   ግን ደግሞ መልከም አሥተዳደር እናነግሣለን ሙሡና እናጠፋለን ቆርጠናል  ብ ላችሁ ሥታወጁ በመሬት ያለው አላነበባችሁ ?  እርሥ ለእርሣችሁም  አልተናበባችሁም::  ነው እያልኩ ያለሁ::
መለሥም  እያለ እኮ መጀመሪያ ሙሡና ከግንዱ  እንቆርጣለን ብሎ ሢያበቃ ቆየት ብሎም  ሽለኮበት ሙሡና ከግንዱ  ካጠፋን ኢህአደግም ሙሉ በሙሉ  አብሮ ይጠፋል:: ብሎነበር  እርሥዎም የመለሥ ሌጋሢ እንዳለ በሙሉ አምላኪ በመሆንዎ  ህዝብ ከማመን ወአለማመን ነው ያዘነበለው::
ሌላ ያለፈው ጊዜ የመልካም አሥተዳደር የፍትህ መከልከል  በዜጎች ነጻነት መከልከለ የኛ ጥፋት ነው ከላችሁ  ከትግራይ አሥከደቡብ በመላው ሀገር ያለወ ግጭት የተፈጠረው የኛ  ጥፋት ነው ካላችሁ በወህኒ ቤት በምርመራ ክፍል  እየተሣቃዩ ያሉ ::በመላው ሀገራችነ ድበቅ እሡርቤቶች በፓሊሥ ጣብያዎች የሚገኙ  ክሥ እንካን ያልተመሠረተባቸው ዘመድ ቤተሠብ የማያውቃቸው እሥሮኞች የሚሠቃዩ ያሉ  ለምን አይፈቱም?? ጋዜጦኞች የተቃወሚ መሪዎችና አበላት  ለምን አይፈቱም ብሎ ቅር ብሎታል ::
ይሀ ጽሁፍ ገና እቀጥልበት አለሁ
ከአሥገደ ገብረሥላሤ ኢትዮጱያ ትግራይ መቀለ

ተጨማሪ ያንብቡ:  አቡነ ማትያስ መህበረ ቅዱሳንን አፈርሰዋለው ሲሉ የማፍረሻውን ትዕዛዝ ማን ሰጣቸው? ቅዱስ ሲኖዶስ? ወይንስ....? | ከተማ ዋቅጅራ
Share