«ዉጡ ፤ በሰላማዊ ሰልፎች ላይ ተሳተፉ!» እስክንድር ነጋ

ሐምሌ 3 ቀን 2005 ዓ.ም

አቶ በትረ ያእቆብ በቃሊት አቶ አንዱዋለም አራጌን እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በጎበኙበት ወቅት የሚከተለዉን መልእክት ከእስክንድር ነጋ ይዘው መጥተዋል። ተላናት ቅኝ የነበሩ የአፍሪካ አገሮች በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባት የትናየት እንደደረሱ የጠቆሙት አቶ እስክንድር «ትናንት የአፍሪካ መሪ እንዳልነበርን፣ ዛሬ ጭራ ሆነናል» ሲሉ በኢትዮጵያ ያለዉ የሕዝብን መብት የሚረግተ፣ አምባገናዊ ስር;አት መኖር ብሄራዊ ዉርደት እንደሆነም ገልሰዋል።

አቶ እስክንድር የአንድነት ፓርቲና ሌሎች እየመሩት ያለዉን ሰላማዊ እንቅስቃሴ በአገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ አገር የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲቀላቀለዉ ጥሪ አቅርበዋል። «ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጊዜና ቦታ ሳይገድበዉ በአንድነት ሊንቀሳቀስ ይገባዋል» የሚል አገር ወድድነት የተሞላበት መል እክስት አስተላልፈዋል።

«የጠባቂዎችን ግልምጫና ሀይለ ቃል ተቋቁሞ በዚያ ዉጥረት በበዛበት ሁኔታ እንዲህ ሲል ነበር እስክንድር ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሁም ለዲያስፖራዉ መልዕክቴን አስተላልፉልኝ ያለዉ» ሲኡ አቶ በትረ የእስክንድርን መልእክት እንደሚከተለው አቅርበዉታል።

“አገራችን ኢትዮጵያ ትልቅ አጣብቂኝ ዉስጥ ትገኛለች ፤ እንደ አገር በመቀጠልና ባለመቀጠል አጣብቂኝ ዉስጥ፡፡ ይህ ደግሞ የህልዉና ጉዳይ ነዉ፡፡ በተጨማሪም እኛ ዜጎቿም በጭቆና ፍዳችንን እያየን እንገኛለን፡፡ ትናንት በአዉሮፓዉያን ተጠፍጥፈዉ የተፈጠሩ እንዲሁም እኛ ያዋለድናቸዉ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ዲሞክራሲን ሲጎናፀፉ እኛ እያደር ወደ ኋላ እያዘገምን እንገኛልን፡፡ ትናንት የአፍሪካ መሪ እንዳልነበርን ዛሬ ጭራ ሆነናል ፤ ይህ ብሔራዊ ዉርደት ነዉ፡፡”

“ስለሆነም ይህንን ችግር ከስሩ ለመቅረፍ የግድ ሰላማዊ ትግል ማካሄድ ይኖርብናል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አሁን በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ እንዲሁም በሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪነት የተጀመረዉ የትግል እንቅስቃሴ ይበል የሚያስብልና የሚያበረታታ ነዉ፡፡ ትግሉ በዚሁ ተጠናክሮ ከቀጠለ እንዲሁም የሁላችን ተሳትፎ ከታከለበት ያለምንም ጥርጥር ወደ ነፃነት ጎዳና ያደርሰናል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጊዜና ቦታ ሳገድበዉ በአንድነት ሊንቀሳቀስ ይገባዋል፡፡”

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከዓለም-አቀፍ የጉራጌ ማህበር (ዓጉማ) የተሰጠ መግለጫ

“አትፍሩ! የአንባገነኖችን ዛቻ አትቀበሉ! ፍርሐት የአንባገነኖች ዋንኛ የአፈና መሳሪያ መሆኑን በመገንዘብ ከልባችሁ አዉጡት፡፡ መቁሰል ፣ መታሰር እና መንገላታት ቢኖርም ይህ የምንከፍለዉ መስዋትነት አገር አልባ ከመሆን ያድነናል ፤ የተሻለች አገር ለመገንባት ይረዳናል፡፡ ስለዚህ ዉጡ! ፤ በሰላማዊ ሰልፎች ላይ ተሳተፉ፡፡”

እስክንድር አያይዞም ለዲያስፖራዉ እንዲህ አለ፡- “ዲያስፖራዉ ለሀገሩ ያለዉን ቀናኢነት የሚያሳይበት አጋጣሚ ይህ ነዉ፡፡ ለህዝቡ ያለዉን ፍቅርና ወገንተኝነት የሚገልፅበት መንገድ ነዉ፡፡ ይህንን በመረዳት አገር ወዳድ ከአገር ዉጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዉያን በጠቅላላ በሚካሄዱ የተቃዉሞ ሰልፎች ላይ በተለይም አዲስ አበባ ላይ በሚካሄደዉ በአካል በመገኘት ተሳታፊ ሁኑ፡፡”

1 Comment

Comments are closed.

Share