February 19, 2016
1 min read

የወያኔን ባለስልጣናት ለምን የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት መቅረብ እንዳልቻሉና ለምን ማቅረብ እንዳልተቻለ ያሬድ ኃ/ማርያም አስረዱ| ሊያደምጡት የሚገባ

  • “ኢሰመጉ እስካሁን ያወጣቸውን ሪፖርቶች እንኳ ብንመለከት ከ7000 ሰዎች በላይ በወያኔ ተገድለዋል”
  • “ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለመዳኘት ካልፈረሙ ጥቂት የዓለም ሃገራት መካከል አንዷ ናት”
  • “ሰዎች ሲገደሉ ለአንድ ለሁለት ሳምንት ሰልፍ በኢምባሲዎች ደጃፍ ወጥተህ ለአንድ አመት የምትተኛ ከሆነ ለውጥ አይመጣም.. እነርሱም ከቁምነገር አይቆጥሩትም”
  • ኢትዮጵውያን ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፍትህ የሚፈልጉ ከሆነ ማድረግ ስለሚገባቸው ነገሮች ይናገራሉ

የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ያሬድ ሃይለማርያም ከሕብር ራድዮ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ ጋር ቆይታ አድርጓል:: በተለይ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ከማንም በላይ ፈረንጆቹ ጋር ቅርበት ያለው ያሬድ በርከት ያሉ ጉዳዮችን አንስቷል:: “በኦሮሚያ እስከ 200 ሰዎች ተገድለዋል.. በጋምቤላም እንዲሁ.. እነዚህ የገደሉ የኢህአዴግ ባለስልጣናት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲጠየቁ የመዘዋወር ገደብ ሲደረግባቸው አይስተዋልም:: እነዚህን ባለስልጣናት በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት መጠየቅ አይቻልም ወይ?” ለሚለው ጥያቄ ከሰጠው ምላሽ ይጀምራል.. ያድምጡት::
https://www.youtube.com/watch?v=jkZVjT0_gcs

Go toTop