የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ሰኔ 30 ቀን 2005 ፕሮግራም
የ30ኛው ዓመት የዘንድሮው በዓል ደምቆ አልፏል የፌዴሬሽኑን ጆሮ የሚፈልጉ የሕዝብ አቤቱታዎች ግን አሉ ለ31ኛው በዓል ሊደገሙ አይገባቸውም ( ልዩ ዘገባ ከተሳታፊዎች፣ከፌዴሬሽኑ ተወካዮች፣ ከነጋዴዎች፣ከኢትዮጵአውያን ጋር በበዓሉ ከተሳተፉ የውጭ ሰዎች መካከል ከአንዷ ጋር ቆይታ እና ሌሎችም)
<<…ልጆቹ እኛ በፈለግንበት ቦታ ነው የሚሄዱት እነሱ እርስ በእርስ የሚያሳልፉበት ሁኔታ የለም።…ልጆቻችን ከሌሎች ልጆች ጋር በፌዴሬሽኑ በዓል ላይ የሚውሉበት ሁኔታ ሊፈጠር ይገባል…>> ጋዜጠኛ በፍቃዱ ሞረዳ የቀድሞ የጦማር ጋዜጣ አዘጋጅና አሳታሚ ስለ ዘንድሮው በዓል ከተናገረው
<< ..መጉላላት ነበር ሶስት ዓመት አይቻለሁ ለውጥ ይመጣል ብዬ አልጠብቅም በፌዼሬሽኑ በኩል መሻሻል የለም.. ሕዝቡ ለውጥ ይፈልጋል…>> ጋዜጠኛ ዳንኤል ገዛሃኝ (የሲዋን ደራሲና የቀድሞው የሞገድ ጋዜጣ አዘጋጅ)
ማንዴላ (ልዩ ዘገባ)
ማንዴላ ስለ ኢትዮጵያ ማንዴላ ስለ አጼ ሀይለስላሴ
ኦባማ የማንዴላን መጽሐፍ መግቢያ ሲጽፉ ምን አሉ? ማንዴላን ታላቅ ስላሰኛቸው ይቅር ባይነት ምን ይላሉ? የኢትዮጵያ ጉዞዋቸውስ? ኢትዮጵያ ለአረ አባርታይድ ትግሉ ያደረገችው ድጋፍ እና ማንዴላ ከንጉሱ ጋር የነበራቸው ቆይታስ? ወቅታዊ የጤና ሁኔታቸውን ጨምሮ ዳሰነዋል
(ዝርዝሩን ከወቅታዊው ዘገባ ያዳምጡ)
ግብጽና አዲሱ በሕዝብ ይሁንታ የተደገፈ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት መጨረሻው ወዴት ያመራል? ትላንት አብዮቱ ከቱኒዚያ ወደ ግብጽ በመጣበት ዛሬ ተመልሶ ወደ ቱኒዚያ ሊሄድ ነው? (ወቅታዊ ዘገባ በግብጽ አብዮት ዙሪያ)
ሌሎችም ቃለ መጠይቆች አሉን
ዜናዎቻችን
– በቬጋስ ኢትዮጵያዊው በቁማር ከ3.1 ሚሊዮኝን ዶላር በላይ አሸነፈ
* ቁማርተኛ እንዳልነበረና ቁማርንም እንደማያበረታታ ገልጿል
– ኢትዮጵያ ከሩሲያ ተዋጊ ጄቶች ልትገዛ ነው
– የመከላከያው በጀት በ15 በመቶ ጨምሯል
– በሳኡዲ አረቢያ 40 ሺህ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ዕጣ ፈንታ አጣብቂኝ ውስጥ ወድቋል ተባለ
– አይ .ኤም.ኤፍ ኢትዮጵያ በሯን እንድትከፍት ጠየቀ
– የደሴውን የአህባሽ ደጋፊ ሼህ ስርዓቱ ለፖለቲካ ትርፍ ሲል እንደገደላቸው የዕምነቱ ተከታዮች እየገለጹ ነው
* በ97 ከወ/ሮ ገነት ዘውዴ ግቢ በተወረወረ ቦንብ 7 ፖሊሶች ሆን ተብሎ በአገዛዙ መገደላቸውና የኦሜሪካ ግዳይ ፈጻሚ ለመንግስታቸው እንዳጋለጡት ደግንነቶች ቦንብ ሊያፈነዱ በሚል የኦነግ አባላት በሚል የገደሏቸው ራሳቸው ደህንቶች መሆናቸው የሰጡት ምስክርነት ለሰሞኑ ግድያ ማጣቀሻነት እየቀረበ ነው
– በስራ ማቆም አድኢማ ላይ ያሉት የቬጋስ አሽከርካሪዎች ኩባንአውን ከሰሱ
* ዩኒየኑን ለመክሰስ ዝግጅታቸውኝ አጠናቀዋል
ሌሎችም ዜናዎች አሉን