June 30, 2013
7 mins read

ትንሽ ስለ ጀዋር መሓመድ – በአብርሃ ደስታ

አንድ ጓደኛየ አንድ የተቀናበረ ቪድዮ በፌስቡክ ገፄን ለጠፈልኝ፤ እንዳነበው እየጋበዘኝ መሆኑ ነው። ቪድዮው ስለ ጀዋር ነው። ግን የሌሎች ሰዎች ስሞችም (የኔን ጨምሮ) ተጠቅሷል። ልጁ ቪድዮውን ሲጋብዘኝ አንዳንድ ዲያስፖራ ተቃዋሚዎች ስለኔ ያላቸው አመለካከት እንዳውቅና ኢህአዴግ መቃወሜን እንዳቆም ‘በአሪፍ’ ተፅዕኖ ማሳደሩ ነው፤ ይህን ድምዳሜ የመጣልኝ ልጁ (ቪድዮው የላከልኝ) ከዚህ በፊት ይልክልኝ በነበሩ ተመሳሳይ መልእክቶች በመነሳት ነው። ይህን የፖለቲካ ስትራተጂ እንደማይሰራ በተደጋጋሚ ለማረጋገጥ ሞክርያለሁ።

ግን …

ሰዎች በኔ ሓሳብ ሊደሰቱ ወይ ሊናደዱ ይችላሉ፤ መደሰትም መናደድም መብታቸው ነው። እኔ ደግሞ የፈለኩትን የመፃፍ መብት አለኝ። ስለዚህ የኔ አቋም ሌሎች ሰዎች በሚሰጡኝ ምላሽ የተንጠለጠለ አይደለም።

ወደ ጀዋርና ቪድዮው ልመለስ። ቪድዮው ጀዋርና ሌሎች ሰዎች ስለተናገሩት ሓሳብ ቀነጫጭቦ ያቀርባል። በመጀመርያ ቪድዮው ትኩረት አልሰጠሁትም ነበር። በኋላ ስለ ቪድዮው የተፃፉ ነገሮች ሳነብ ግን ትኩረት እንደሚያስፈገው ገባኝ።

ባጠቃላይ ሲታይ የተቀናበረውን ቪድዮ አልወደድኩትም። አንደኛ የተቀመጠው የጀዋር ሓሳብ የተቆራረጠ ነው። ለድምዳሜው የሰጣቸው ማስረጃዎች በትክክል በቪድዮው አልተካተቱም። አንድ ጥሩ የነበረ ሓሳብ ቆራርጠን በማቅረብ ጥላሸት መቀባት ይቻላል። ስለዚህ ጠቅላላው የቀረበ አመክንዮ በተፈለገው መጠን ስላልቀረበ በቪድዮን በቀረቡ የተቀነጫጨቡ ሓሳቦች መገምገም አንችልም።

ሁለተኛ በቪድዮው የቀረበው የተቀነባበረ ሓሳብ ጀዋርን ለመገምገም ያስችለናል ብለን ከተነሳን የተናገረው ነገር የልጁን ስም ለማጥፋት በቂ ምክንያት ይሆናል ወይ? የሰጠው ሓሳብ የራሱ (የግሉ) አስተያየት ነው። ‘ኦሮሞዎች በደል ይደርሳቸው ነበር’ ብሎ ማለት ‘ኢትዮዽያን መጥላቱ’ ያሳያል ወይ? የብሄር ጭቆና መኖሩ ሓሳብ መሰንዘር ‘ኢትዮዽያዊ ስሜት’ እንደሌለው ምክንያት ወይ ማረጋገጫ ሊሆን ይችላል ወይ?

ስለ ኢትዮዽያ ስናወራ ስለኢትዮዽያውያን እየተናገርን ነን። ኢትዮዽያውያን ህዝቦች ናቸው። ህዝቦቹም ኦሮሞዎች፣ አማራዎች፣ ትግራዮች፣ ጉራጌዎች፣ ሶማሊዎች፣ ደቡቦች፣ ጋምቤላዎች፣ ቤኑሻንጉሎች … ወዘተ ናቸው። ‘ጉራጌ ተበደለ’ ሲባል ኢትዮዽያዊ እየተበደለ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ጀዋር ‘ኦሮሞች ተበድለዋል’ በማለቱ የተፈጠረ ችግር ምንድነው??? እንኳንም በድሮ ዘመን አሁንም እኮ ‘ጭቆና አለ’ ብለን እየተከራከርን ነን።

ሦስተኛ ጀዋር የሰጠው አስተያየት ጥሩ አይደለም ብለን እንነሳ፤ ታድያ ማድረግ ያለብን ጉዳይ ስም ለማጥፋት መሯሯጥ ሳይሆን አስተያየቱ ስህተት መሆኑ በሓሳብ ማሳመን መቻል ነው። በሰጠው አስተያየት ላይ የሓሳብ ክርክር መክፈት ይቻላል። አስተያየቱ ‘ስህተት’ ስለመሆኑ ማረጋገጥ የምንችል ከሆነ ጀዋርን ለማስተካከል እንዴት ያቅተናል?

አራተኛ አንድ ሰው የተለየ አስተያየት ስለሰጠ ‘የኢትዮዽያ ጠላት’ አድርጎ መፈረጅ መፍትሔ ይሆናል ወይ? ሁሉም ሰው ስለ አንድ ጉዳይ ተመሳሳይ አቋም ይኖረው ዘንድ ግድ አይደለም። የምንታገለው አንድ ዓይነት አስተሳሰብ እንዲኖረን ለማድረግ ሳይሆን እንደየምርጫችን በነፃነት መኖር እንድንችል ነው።

በመጨረሻም

ጀዋር በያዘው አቋም ልዩነት ቢኖረኝም በሰጠው አስተያየት ግን አልተከፋሁም፤ ጥፋቱም አልገባኝም። የብሄር ጭቆና እንደነበር (አሁንም ችግሩ በተገቢ መንገድ እንዳልተፈታ) ከጀዋር ጋር እስማማለሁ። በአሁኑ ሰዓት (ችግሩ ለመፍታት) ምን መደረግ አለበት በሚለው (ብሄርን ከሀገር ማስቀደሙ) ግን ከጀዋር ጋር የሓሳብ ልዩነት አለኝ።

እንደኔ ከሆነ የዘመናት የፖለቲካ ችግሮቻችን መፍታት የምንችለው ታሪክን እያስታወስንና ብሄርን እያስቀደምን የሀገራችን አንድነት በሚያዳክም መልኩ በመወያየት ሳይሆን የነበረው ጭቆና እንዲወገድ አብረን በመታገልና በእኩልነትና በአንድነት የምንኖርባት ኢትዮዽያ እውን በማድረግ ይመስለኛል።

ጀዋር መሓመድ በጣም ከማደንቃቸው ብርቅዬ ወጣት ኢትዮዽያውያን የፖለቲካ ተንታኞች አንዱ ነው። ጀዋር አድናቆቴን ይድረሰህ።

በሓሳብ መለያየት ጥፋት አይደለም። ስለዚህ የሰው ስም ለማጥፋት ዘመቻ መክፈት ተገቢ አይደለም።

ኢትዮዽያችንን ይባርክልን፤ አሜን።

Latest from Blog

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop