ከጥሩነህ ካሳ (የወርልድ ስፖርት ጋዜጣ አዘጋጅ)
የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግን በኮከብ ግብ አግቢነት እየመራ የሚገኘው ጌታነህ ከበደን ከደቡብ አፍሪካ ክለቦች የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ ተቀብሎ ዛሬ ወደ ደ.አፍሪካ አቅንቷል፡፡ ጌታነህን ለመውሰድ የደቡብ አፍሪካው ሰልቲክ ክለብ ከፍተኛ ፍላጎት አሳይቷል፡፡ በርካታ ደጋፊዎች ያሉት ሰልቲክ ከሌሎች ክለቦች የተሻለ ክፍያ ማቅረቡም ታውቋል፡፡
ጌታነህም በዛሬው ዕለት የጤና ምርመራ ለማድረግ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጉዟል፡፡ የጤና ምርመራውን ማለፍ ከቻለም አዲሱን የኮንትራት ውል ይፈራረማል፡፡ ጌታነህ ከደደቢት ክለብ ጋር ያለው ኮንትራት ውል የፊታችን ሰኔ 30 የሚጠናቀቅ በመሆኑ ዝውውሩን የተሳካ እንደሚሆንም ይጠበቃል፡፡