ምነዋ ! ማንዴላችን ? !

የግርጌ ማስታዎሻ : ከዘጠኝ አመት በፊት ያጣሁት አንድ ወንደም ነበረኝ ፣ ጋዜጠኛና ደራሲ መጽሐፈ ሲራክ የሚባል። መጽሐፈ የሃገር ፍቅር ልክፍቱን ብቻ አልነበረም ጥሎብኝ እስከ ወዲያኛው ያሸለበው ፣ የዘመናቸን ታላቅ የጥቁር ህዝብ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላን አበክሬ እንዳውቀው የረዳኝ ፣ ለነጻነት ክብር ለዲሞክራ ከቆሙት ጎን እንድቆም ፣ ሰብአዊ መብት ሲዳጥ ዝም እንዳልል፣ የግፉአንን ድምጽ እንዳሰማ የህይወትን ውርስ ያወረሰኝ ወንድሜ ለጥቁር ህዝብ አርበኛው ለኔልሰን ማንዴላ የነበረው ክብር ከፍ ያለ ነበር ! መጽሐፈ “ማንዴላ” እያለ በቀድሞው ለገዳዲ እና የኢትዮጵያ ራዲዮ ተወዳጁ የእሁድ መዝናኛ ተቀኝቶላቸውም ነበር ። ነፍሱን ይማረው እና ዛሬ ያ ወንድሜ በአካል ከእኛ ጋር የለም ! ማንዴላም ሁላችንም እሱ ወደ ሔደበት መጓዛችን ባንቀርም የታለቁ አባትን በጸና መታመም ስሰማ ወንድሜን አስታውሸ ፣ ማንዴላን ለማዘከር በፍጹም ስሜት “ምነዋ ማንዴላ ! ” ብየ ገጠምኩ !
በማለዳው . . .ሰኔ 2005 ዓ.ም June 24,2013 E.c ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ተጻፈ
ከሰላምታ ጋር

ነቢዩ ሲራክ

ምነዋ ! ማንዴላችን ? !
ድምጽህ ቁርጥ ቁርጥ አለ አመመህ
ምነው ደከመህ በማረፊያህ ?
አፍሪካን ከአንባገንን ልጆቿ ጸድታ ሳታይ
ምነዋ መድከም ማሸለብህ ?
የኢትዮጵያን ስርየት ሳይበሰር
ምነዋ የመለየት ጉዞን መጀመርህ
ኢትዮጵያ ከደዌ ተላቃ ሳትጎበኛት
ምነዋ አትቀስቅሱኝ አልክ አንቀላፋህ ?
ምነዋ መልአከ ሞት ከበበህ
የስንብት መርዶ ጽልማሞት ግርማውን አለበሰህ
ምነዋ ጠንካራውን ጉልበትክን ፈተነብህ
የእማማን አፍሪካን ድህነት ማየቱ ታከተህ !
ምነዋ ማንዴላ?. . .

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያዊያን ቆም ብለን የምናስብበት ወቅት ዛሬ ነው - መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
Share