Sport: ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ የፊታችን እሁድ በአ.አ. ወሳኝ ጨዋታ ይጠብቃታል

June 11, 2013

ከአሰግድ ተስፋዬ

ለ2014 የአለም ዋንጫ ተሳትፎ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ይጫወታል። ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ይህን የእሁዱን ጨዋታ አሸንፎ ምድቡን በበላይነት ካጠናቀቀም አህጉሪቱን በብራዚሉ የአለም ዋንጫ የሚወክሉ 5 ቡድኖችን ለመለየት በ10 ብሄራዊ ቡድኖች መካከል በሚደረገው የደርሶ መልስ ጨዋታ ከሚደርሰው ቡድን ጋር እንደሚጫወት ተገልጿል።
የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ አቶ ሰውነት አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከክለብ ጨዋታዎች ያለ እረፍት ወደ ቡድኑ በመቀላቀላቸው ከቦትስዋና አቻቸው ጋር በነበራቸው ጨዋታ ላይ በተለይም በጨዋታው መጠናቀቂያ አካባቢ የተፈጠረባቸው የድካም ስሜት ውጤቱ ከዚህ በተሻለ ሁኔታ እንዳይጠናቀቅ የራሱ ድርሻ እንደነበረውም አስታውሰዋል።

ኢትዮጵያ ደቡብ አፍሪካን በእሁዱ ጨዋታ ካላሸነፈች ወደ ቀጣዩ ውድድር ስለማትገባ ቡድኑ አጥቅቶ መጫወት እንደሚገባው ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው እሁድ አዲስ አበባ ላይ ብሄራዊ ቡድኑች ሲጫወት ሕዝቡም በድጋፉ እንዲበረታ ጥያቄ አቅርበዋል።
ምድብ አንድን ኢትዮጵያ በ10 ነጥብ እየመራች መገኘቷ እና ደቡብ አፍሪካም በ8 ነጥብ በቅርብ ርቀት መከተሏ የእሁዱን ጨዋታ ተጠባቂ አድርጎታል።
በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አገሪቱ ከመሠረተችው የአፍሪካ ዋንጫ ተፎካካሪነት ከራቀችና የሩቅ ተመልካች ከሆነች ከ31 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ መሳተፉን እንዲሁም የአገሪቱ አንጋፋ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ላይ ያሳየውን ተፎካካሪነትን ተከትሎ በርካታ የስፖርቱ ጸሐፍት «ኢትዮጵያ የእግር ኳስ የበላይነቷን እያስመለሰች ነው» ማለት ጀምረዋል ።
ጸሐፍቱ እንዲህ ማለት ከጀመሩ የሰነባበቱ ቢሆንም፣ ዋሊያዎቹ ባለፈው ቅዳሜ ቦትስዋናን በሜዳዋ ላይ ሁለት ለአንድ ከረቱና በዓለም ዋንጫ ማጣሪያው የምድብ መሪነታቸውን ያስጠበቀ ውጤት ካስመዘገቡ በኋላ አጠናክረው ቀጥለዋል።
ይህንን ሐሳብ ከሚጋሩት መካከል ኢኬና አጉ የተሰኘው ጸሐፊ ይገኝበታል። ጸሐፊው ዋሊያዎቹ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያው ምድባቸውን መምራት መቻላቸው የአገሪቱ እግር ኳስ መነቃቃት እያሳየ እንደሚገኝና ኢትዮጵያም ወደፊት በስፖርቱ ብርቱ ተፎካካሪ አገር እንደምትሆን አመላካች መሆኑን ጽፏል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሶማሊያውን የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ሳይጨምር አራት ጨዋታዎች አድርጎ አንድም አለመሸነፉ ቡድኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዋሃደና ጥንካሬ እያገኘ በመሄድ ላይ እንደሚገኝም ጸሐፊው ጠቁሟል።
ዋሊያዎቹ ምድብ አንድን በአስር ነጥብ ከደቡብ አፍሪካ በሁለት ነጥቦች በልጠው ከአናት መቀመጥ መቻላቸውና ደቡብ አፍሪካን በአዲስ አበባ የሚያስተናግዱ መሆናቸው ከምድቡ የማለፍ ከፍተኛ እድል በመያዝ ቀዳሚ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል ሲልም በጽሑፉ አስነብቧል።
«ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኗ ለዓለም ዋንጫ አልፎ ባያውቅም በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2014 ላይ በብራዚል የሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ይህን የቆየ ታሪክ የሚቀየርበት እንዲሆን ለማድረግ ቆርጠው የተነሱ ይመስላልም » ብሏል ኢኬና አጉ።
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን መስራቿና የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳታፊ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ እንዲሁም ዋንጫውን ያዘጋጀችና ያሸነፈችዋ ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ በስፖርቱ ከነበራት ስፍራ ቀስ በቀስ እየተንሸራተተች ሄዳ ደካማ ከሚባሉ አገሮች ተርታ መመደቧን ጸሐፊው አስታውሶ፣ «የ2013ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የአገሪቱ እግር ኳስ እያንሰራራ ለመምጣቱ ግልጽ ማሳያና አገሪቱ በአህጉሪቱ የነበራትን ስፍራ ለመመለስ በሂደት ላይ መሆኗን አመላካች ሆኗል» ብሏል።
ብሔራዊ ቡድኑ በአፍሪካ ዋንጫ ከምድብ ማጣሪያው ማለፍ ባይችልም እንኳን ነገሮች በትክክለኛው አቅጣጫ ላይ እንደሚገኙ አመላካች እንደነበሩ ያመለከተው ጸሐፊው፣ ከዚያ በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የምድብ ድልድል ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መግባቱና ዋሊያዎቹ በአራት ጨዋታዎች ባገኟቸው አስር ነጥቦች ምድብ አንድን መምራት መቻላቸውን በማሳያነት በጽሑፉ ጠቅሷል።
የኢኤስፒኤን ጸሐፊው ፍርዶስ ሙንዳም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ስፖርት በማንሰራራት ላይ እንደሚገኝ ከጻፉት መካከል አንዱ ነው። ጸሐፊው ኢትዮጵያ በአውሮፓውያኑ 1962 የአፍሪካ ዋንጫ ብታነሳም እስካሁን በአህጉራዊ ውድድሮች ምድብ ድልድል ውስጥ የገባ አንድም ክለብ እንዳልነበራት ያስታውስና ኤሲ ሌኦፓርድ የተባለው ክለብ የኮንጎን እግር ኳስ እንዳነቃቃ ሁሉ ቅዱስ ጊዮርጊስ በቅርቡ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስመዘገበው ውጤት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት ከፍተኛ አዎንታዊ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው ግምቱን አስፍሯል።
ከዚሁ ጋር አያይዞ ብሔራዊ ቡድኗ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በማሳየት ላይ የሚገኘው አስደናቂ ብቃትና ውጤታማነት የአገሪቷን የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪ እጅጉን ማርካቱን ጠቁሟል።
ዋሊያዎቹ በሚቀጥለው እሁድ ከባፋናባፋናዎች ጋር አዲስ አበባ ላይ የሚያደርጉትን ጨዋታ በበላይነት የሚያጠናቅቁ ከሆነ ሕዝቡ የሚኖረው ደስታ ባለፈው ጥቅምት 4 ቀን 2005 ዓ.ም ሱዳንን በማሸነፍ ከ31 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን ያረጋገጠበት እለት ካሳየው በእጅጉ የተለየ ሊሆን እንደሚችል ገምቷል።
«ዴይታይምስዶትኮምዶትኤንጂ » የተሰኘው ድረ ገጽም በተመሳሳይ « የአፍሪካ የእግር ኳስ ኃያልነት ቀስ በቀስ ወደ ኢትዮጵያ እየተመለሰ ነው » ሲል ጽፏል።
ድረ ገጹ ለማሳያነትም የቅዱስ ጊዮርጊስንና ዋሊያዎቹ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያው በማስመዝገብ ላይ የሚገኙትን ውጤት ጠቅሶ፤ የአገሪቱ ውጤት በአጭር ጊዜ ከአህጉሪቱ ኃያል ከሚባሉት ተርታ ሊሰለፍ እንደሚችል ገልጿል።
ዋሊያዎቹ በማስመዝገብ ላይ የሚገኙት ውጤት የአገሪቱ እግር ኳስ ስፖርት መነቃቃትና በአፍሪካም ደረጃ ወደፊት ከፍተኛ ተወዳዳሪ እንደሚሆን ማሳያ ሆኖ በብዙዎች ዘንድ ተወስዷል።
ይህንን ተከትሎም በቀጣይነት ከዋሊያዎቹ ጋር በአዲስ አበባ ላይ ጨዋታ የሚያደርጉትን የደቡብ አፍሪካን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ጎርደን ኢግሰንድንና የቀድሞ የቡድኑን አባላት አስግቷል።
ባፋናባፋናዎች በዓለም ዋንጫው ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከዋሊያዎቹ ጋር አድርገው ሳላዲን ሰኢድ ባስቆጠራት ግብ ሲመሩ ከቆዩ በኋላ አቻ ለ አቻ መለያየታቸው ይታወሳል። የባፋናባፋናዎች አሠልጣኝ ጎርደን ኢግሰንድ ባለፈው ቅዳሜ ከመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ጋር ካሜሩን ላይ ከመጫወታቸው በፊት ብዙ የሚያሳስባቸው አዲስ አበባ ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ መሆኑን ገልጸዋል።
ከእርሳቸው በተጨማሪ የቀድሞው የቡድኑ አምበል ሉካስ ራዴቤ የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫው ለመሳተፍ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ከፍተኛ ተፎካካሪ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንደሆነ አስተያየቱን ሰጥቷል። ባፋናባፋናዎች አዲስ አበባ ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ እጅግ ፈታኝ እንደሚሆንባቸውም ግምቱን ከሰጠ በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማድረግ ላይ የሚገኘው መሻሻል እንዳስደነቀው ተናግሯል።
በበርካታ የእግር ኳስ ስፖርት ተንታኞችና ጸሐፍት ዘንድ አድናቆትንና ሙገሳን በማግኘት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው መመራት ከጀመረ በኋላ በሥነልቡና፣ በቴክኒክና በታክቲክ ረገድ ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቱ እውነት ነው።
ይህንንም አገሪቱን በስፖርቱ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደመነሻ መውሰድና መሥራት ይጠበቃል።

2 Comments

  1. Bravooooo coach Sewenet Bishawe ! Sewenet sisera Genene Gk yaweralle ! ahun selchet yalen neger binor Ye-Genene Gk and Ye-Bulla Gellebba were newe !

  2. hello, all

    can any one tell me what time will be the game start. I am so expecting to see the game. Good luck my Ethiopia brothers and sisters from anther mother. would be great if some one can tell me in eastern time. if not just post it as in Ethiopia, Addis-Abeba.

    Again good luck !!!

Comments are closed.

asreat abrham
Previous Story

ሁለት የአረና ለትግራይ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ከፓርቲው ለቀቁ

4235
Next Story

“ወንድሞቻችንን እና ልጆቻችንን የገደሉትን መንግስት ቢወድቅ እንኳ አንረሳም” ኦባንግ ሜቶ

Latest from Blog

አገራችን አሁን ያለችበት እጅግ አጣብቂኝ ሁኔታ (እውነቱ ቢሆን)

በዚህች አጭር ጽሁፌ ሁለት ነገሮች ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፤ በወልቃይትና ራያ መሬቶች ጉዳይና ስለአብይ አህመድ የማይሳካ ቅዠትና ህልም ዙሪያ፡፡ ስለወልቃይትና ራያ፦ እነዚህ ቦታወች ዱሮ የማን ነበሩ? በማን ስርስ ይተዳደሩ ነበር?  አሁንስ የማን ናቸው?? ለምንስ ይህንን ያህል ደም ያፋስሣሉ… ወዘተ ወደሚለው ጥያቄ ከማምራታችን በፊት መሬቶቹ በውስጣቸው ምን ቢይዙ ነው? አቀማመጣቸውና ጠቀሜታቸውስ ምንና

ሳሙኤልም እንደ እስጢፋኖስ!

 በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ሳሙኤል አወቀ እንደ ቅድመ አያቶቹ ዝቅዝቅ መታየትን ያልተቀበለና በጥናት የታገለ ከመጀመሪያዎቹ ፋኖ ሰማእታት አንዱ ነው፡፡  ሰማእታትን መዘንጋት አድራን መብላት ነው፡፡ አደራን መብላትም እርምን መብላት ነው፡፡ እርምን መብላትም መረገም ነው፡፡እርማችንን

በትሮይ ፈረስነት የመከራና የውርደት አገዛዝን ማራዘም ይብቃን!!!   

June 16, 2024 ጠገናው ጎሹ በሥልጣነ መንበር ላይ የሚፈራረቁ ባለጌ፣ ሴረኛ፣ ሸፍጠኛና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች መከረኛውን ህዝብ ከአስከፊ ድንቁርና እና ከሁለንተናዊ የመከራና የውርደት ዶፍ ጋር እንዲለማመድ  ከሚያደርጉባቸው እጅግ በጭካኔ  የተሞሉ ዘዴዎቻቸው መካከል ኮሚቲ፣

ኑሮ የከበዳቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓትን በቤተ እምነቶች እያሳለፉ መሆኑ ተነገረ

ሲሳይ ሳህሉ / ቀን: June 16, 2024 የቤት ኪራይ መክፈል ያልቻሉ ተደብቀው ቢሮ ውስጥ ያድራሉ ተብሏል መንግሥት የሚከፍላቸው ወርኃዊ ደመወዝ አልበቃ ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓታቸውን ወደ ቤት እምነቶች በመሄድ፣ እንዲሁም ቤት

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት
Go toTop