June 5, 2013
5 mins read

ምርጫ፦ ህወሃት ወይስ ግብጽ?

በያሬድ አይቼህ – ጁን 5፥2013

አቶ መለስ ዜናዊ የአባይ ግድብን ለመገንባት መስተዳደራቸው መቼ እንደወሰነ ሲጠየቁ ውሳኔው ከ2002 ዓ.ም. በኋላ እንደሆነ ተናግረው ነበር። አቶ መለስ በአንጎላቸው ውስጥ የነቀርሳ ዕጢ እንዳለባቸው ያወቁት ከ2002 ዓ.ም. በፊት ነው።

እንግዲህ የቀድሞው ጠሚራችን (ጠቅላይ ሚኒስትራችን) አባይን ለመገንባት ለምን እንደተመኙ ስጠራጠር ምናልባት የሳቸው መስተዳደር የፈጠረውን አገራዊ መከፋፈል እና የራሳቸውን ታሪካዊ ትሩፋት (legacy) ለማግነንና ለመቤዤት ጭምር ሳይሆን አይቀርም።

የቀድሞው ጠሚራችን ህመማቸው እንደሚገላቸው ያዉቁ ነበር ቢባል ማጋነን አይመስለኝም። አቶ መለስ ታሪክ በበጎ አይን እንዲያያቸው አባይን መገደቡን ጥሩ አማራጭ አርገው አግኝተውታል።

አባይ የሚገደበው በአማራ ክልል ውስጥ አይደለም ፤ በቤንሻንጉል እንጂ። አባይ የኢትዮጵያውያን መንፈስን በቁጪት ጠፍሮ ያሰረ ወንዝ ነው። አባይን መገደብ ለአቶ መለስ ኢትዮጵያውያንን ለማስተሳሰር ትልቅ አጋጣሚ ሆኖላቸዋል። የቀድሞው ጠሚር “አባይን ደፈረ” መባሉን ከዚህ አለም ከመለየታቸው በፊት መስማታቸው የህሊና እረፍት ሰቷቸው ይሆናል።

ሰሞኑን የግብጽ ፓለቲከኞች ሲዶልቱት የነበረውን ቅዠት ሰምተው “ወያኔን ከግብጽ ጋር ተባብረን እንደመስሰዋለን” ሲሉ የተሰሙ ወገኖች አሉ። ግብጽ የአባይን ግድብ በቦንብ ለመደበድብ የሱዳንን አየር መጠቀም የግድ ነው። ሱዳን ከመቼውም የበለጠ የተናጋ ሁኔታ ላይ ያለች አገር ናት። ለሁለት ተከፍላለች ፡ ዳርፉሮች መገንጠል ይፈልጋሉ ፤ ስለዚህ ከኢትዮጵያ ጋር በሰላም መኖር ለሱዳን የግድ ነው።

ሱዳን ከግብጽ ጋር ነው ምሰራው ብላ ሰማይዋን ለግብጽ ጦር አዉሮፕላን ብትከፍት ፡ ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ፡ ከዳርፉር አማጽያን ፡ ከሱዳን ተቃዋሚዎች ጋር ፡ እንዲሁም ከምዕራቡ አለም ጋር በመተባበር የሱዳንን ፓለቲካ መናድ የምትችልበት ሁኔታ ሰፊ ነው።

ግብጽ እንደምንም ብላ ግድባችንን በቦንብ ብትደበድብ ኢትዮጵያ የግብጽን ትልቅ ግድብ (አስዋን ግድብ) እንደምንም ብላ በቦንም የመደብደብ አማራጯን መጠቀሟ አይቀርም።

ግብጾች የአባይን ግድብ እንኳንስ በቦምብ ዝንቡንም እሽ የማለት ድፍረት የላቸውም። እንዲያውም የግብጽ ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ሰፋፊ የስንዴ እርሻ መከራየታቸው አይቀርም። ኢትዮጵያም ለግብጽ ትልቅ የሰብል ንግድ አጋር እንደምትሆን ግብጾች ያቃሉ ፡ ያንንም አማራጭ ለመጠቀምም ተዘጋጅተዋል።

ታዲያ ይሄ ሁሉ ተጨባጭ ሁኔታ እያለ ፡ ምነው አንዳንድ የዲያስፓራ ወገኖች “ከህወሃት ይልቅ ግብጽ ይሻለናል” የሚል ጸያፍ የአገራዊ ጥቅምና ህልውናን አሳልፎ የሚሰጥ አቋም እንወስዳለን?

ግን ይሄ ሁሉ ግር-ግር የሰማያዊ ፓርቲን ትልቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንዴት ከመቅጽፈት አስረሳን? ዲያስፓራ ምራቁን ያልዋጠ ፡ በወሬ በቀላሉ የሚረታ ፡ ስሜቱ የሚቀድመው ፡ ሆድ የባሰው ማህበረሰብ መሆኑ ባለፉት 22 ዓመታት አንድ እርምጃ መራመድ ያልቻለ ማህበረሰብ ለመሆኑ ጠቋሚ ነው።

 

የአባይ ግድብ ይገደባል። ግድቡን የገነባው ይገንባው ፡ ግን ይገደባል።

የዴሞክራሲ ፡ የፍትህና የዜጎች ህገመንግስታዊ መብቶች መከበር ትግልም ይጧጧፋል። ከሰማያዊ ፓርቲ ጅማሬ ጋር ወደፊት!

—————————

አስተያየትና ትቺቶችን በዚህ ይላኩልኝ፦ yared_to_the_point@yahoo.com

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop