March 30, 2015
5 mins read

Hiber Radio: ግብጽ የአባይን ግድብ እንቅስቃሴ የሚቃኝ የስለላ ሳተላይት መግጠሟ ታወቀ.. ከ10 ሺ በላይ የቅማንት ማህበረሰብ ከቀያቸው እንዲለቁ ትዕዛዝ ተላለፈ… በካናዳ ለ5 ዓመት የጠፋው ኢትዮጵያዊ አስከሬኑ ከጣራው ስር ተገኘ.. የደብረታቦር ሕዝብ አገዛዙ ስልጣኑን እንዲለቅ በተቃውሞ ሰልፍ ጠየቀ… ኢትዮጵያ ጦሯን ከሶማሊያ ባይዳዎ ግዛት አወጣች…ኢትዮጵያውያን የእግረኛ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በየመን ላሉ ወገኖቻቸው ጠንክረው ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ተጠየቁ… እና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
Hiber Radio: ግብጽ የአባይን ግድብ እንቅስቃሴ የሚቃኝ የስለላ ሳተላይት መግጠሟ ታወቀ.. ከ10 ሺ በላይ የቅማንት ማህበረሰብ ከቀያቸው እንዲለቁ ትዕዛዝ ተላለፈ... በካናዳ ለ5 ዓመት የጠፋው ኢትዮጵያዊ አስከሬኑ ከጣራው ስር ተገኘ.. የደብረታቦር ሕዝብ አገዛዙ ስልጣኑን እንዲለቅ በተቃውሞ ሰልፍ ጠየቀ... ኢትዮጵያ ጦሯን ከሶማሊያ ባይዳዎ ግዛት አወጣች...ኢትዮጵያውያን የእግረኛ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በየመን ላሉ ወገኖቻቸው ጠንክረው ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ተጠየቁ... እና ሌሎችም 1

የህብር ሬዲዮ መጋቢት 20 ቀን 2007 ፕሮግራም

< …ዛሬ በደብረ ታቦር ሕዝቡ በተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ወጥቶ ስርኣቱ በቃን ፣ልቀቁን ውረዱ ብሏል…ሕዝቡ ሰልፉን እንዳይቀላቀል መንገድ ዘግተውበታል ። ከፍተና የፖሊስና የደህንነት ሀይል ነበር።..ምርጫው ነጻ ቢኖር ኖሮ ለብአዴን ድምጽ የሚሰጠው አይኖርም …> አቶ ሳሙኤል አበበ በደብረ ታቦር ሰማያዊ ፕርቲን ጨምሮ የዘጠኙ ፓርቲች ትብብር የጠራው ሰልፍ አስተባባሪና የሰማአዊ ዕጩ ተወዳዳሪ ስለሰልፉ ተጠይቆ ከተናገረው የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ )

<…በየመን ያዩ ኢትዮጵያውያን ከወዲሁ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ከዚህ ሳውዲ የተባረሩትም በዚያው ነው የሚመጡት ከአገር ቤትም ወደ የመን የሚሄዱ ይኖራሉ በዚህ የጦርነት ወቅት ግን…>

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከጂዳ በሳውዲ የሚመራው ጦር በየመን አማጽያን ላይ የከፈተውን የአየር ጥቃት ተከትሎ በኢትዮጵያውያን ላይ ስለጋረጠው ስጋት ካደረግነው ቃለ መጠይቅ(ሙሉውን ያዳምጡት)

<…እዚህ በየመን ያለንበት ሁኔታ እጅግ አስጊ ነው። ስደተኛው በጥሩ መንገድ አይታይም ። የአየር ድብደባውን ተከትሎ የእግረኛ ጦርነት ከተጀመረ ሁኔታዎች አስቸጋሪ ይሆናሉ … አስከፊ ችግር ውስጥ ስንገባ ከመሰለፍ አሁኑኑ አስቀድሞ ሊጮህልን ይገባል…>

ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሀይማኖት በየመን ኢትዮጵያውያን ስላሉበት ሁኔታ ከህብር ተጠይቆ ከሰጠው ምላሽ(ሙሉውን አዳምጡት)

ኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ላይ ያደረጉትን ስምምነት መሰረት ያደረገ የግብፅ መገናኛ ብዙሃን እይታ (ልዩ ዘገባ )

ባሻ ይገዙ < ሰይጣን በአገሩ! > (ልዩ ግጥም)

በቬጋስ የፍሪያስ የቀድሞ ታክሲ አሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ ያደረጉበትን ሁለተኛ ዓመት አስመልክቶ ውይይት

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

– ግብፅ የአወዛጋቢውን ህዳሴ ግድብ እንቅስቃሴ የሚቃኝ ዘመናዊ የስለላ ሳተላይት መግጠሟ ታወቀ

– የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎችና የአገዛዙ ወታደሮች ፍጥጫ ውስጥ ገቡ

* ከ10 ሺህ በላይ የቅማንት ነዋሪዎች ከመኖሪያቸው በሁለት ሳምንታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ መመሪያ ተላለፈባቸው

– ኢትዮጵያ ጦሯን ከሶማሊያ ባይዳዎ ግዛት አወጣች

– የዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር በ15ከተሞች ካቀዱት ሰላማዊ ሰልፍ በጥቂት ከተሞች በከፍተኛ ጫና አካሄዱ

– በደብረ ታቦር በሰልፉ ላይ ህዝቡ አገዛዙ እንዲወርድ ጠየቀ

– ኬኒያ ህገወጥ ያለቻቸውን 65ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በገንዘብ ቀጣች

– በካናዳ ለ5 ዓመት የጠፋው ኢትዮጵያዊ አስከሬኑ ከጣራው ስር ተገኘ

– የየመን የእርስ በእርስ ጦርነት ወደ አካባቢ ጦርነት ማደጉ ስጋት ፈጠረ

– ሱዳን በየመን የተሰማሩ ጄቶቿ ጥቃት እንዳልደረሰባቸው ገለፀች

* ኤርትራ የየመን አማፅያን አላስተናገድኩም አለች

– በየመን የሚገኘው የአገዛዙ ኤምባሲ ዲፕሎማቶቹን ለማስወጣት እየተሯሯጠ ነው

* ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በምዝገባ ስም እየሸነገለ ነው

– ኢትዮጵያውያን የእግረኛ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በየመን ላሉ ወገኖቻቸው ጠንክረው ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ተጠየቁ

– በቬጋስ በፍ/ቤት ታግዶ የነበረው ሁበር በቅርቡ ወደ ገበያው እመለሳለሁ አለ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Previous Story

  **ድንቄም ምርጫ** – ነብሮ

Next Story

የምርጫ ክርክር ሶስት- ግብርና እና ገጠር ልማት (ከግርማ ሰይፉ ማሩ)

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop