4 መኮንኖች ታሰሩ * የመከላከያ ሰራዊቱ ጥያቄ ወደ አመጽ ሊሸጋገር ተቃርቧል

ፎቶ ፋይል
የደቡብ ምስራቅ እዝ የመከላከያ ሰራዊት ካልደፈረሰ አይጠራም እያለ ነው

ምኒልክ ሳልሳዊ እንደዘገበው:-

ጨፍጫፊው ሌ/ጄነራል አብረሃ ወልደ ማርያም (ኩዋተር) የሚመራው ለሶማሌ ክልል ሰላም በሚል በአከባቢው የሰፈረው የደቡብ ምስራቅ እዝ የሕወሃት የጦር አዛዦች በራሳቸው የሚወሥዱት ውሳኔ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የሚያደርሱት ጫና እና እንዲሁም ሰራዊቱ ያቀረበውን ሕገ መንግስታዊ ጥያቄ ወደ አመጽ ማምራቱ ተሰምቷል::በጎዴ ከሚገኙ የመከላከያ ደህንነት ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ካልደፈረሰ አይጠራም በሚል የተነሳውን አመጽ የተመለከቱ የሕወሓት የጦር አዛዦች የመከላከያ ሰራዊት ጥያቄ እና አመጻ ተከትሎ አነሳስተዋል የተባሉ አራት ወታደራዊ መኮንኖች መታሰራቸው ታውቋል::

በዚህም መሰረት
ሌተናት ኮሎኔል ተክለአረጋይ ዳኘው
ሻለቃ አበባየሁ አቡኑ
ሻለቃ ደምወዜ የኔአለም
የም/መቶ አለቃ ላቀው ልኬየለህ በጎዴ ወታደራዊ እስር ቤት መታሰራቸው ታውቋል::

በጅጅጋ ከተማ በተከታታይ የሚሰበሰበው የሕወሓት ጄኔራሎች ቡድን በደቡብ ምስራቅ እዝ ውስጥ የተነሳውን አለመተማመን እና ግርግር መቅረፍ እንዳልተቻለ እና አመጾች ሳይስፋፉ እና ስር ሳይሰዱ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ሁሉ እንዲወሰዱ ሲል ተስማምቷል::በሶማሊ ክልል የሚገኘው የሕወሓት ጀሌዎች የሆኑ መኮንኖች በኦጋዴን ክልል ማህበረሰብ ላይ ይህ ነው የማይባል ከባድ ግፍ እና ግድያ እስር ሰቆቃ የሚፈጽሙ ሲሆን በሕገወጥ ንግድ ላይ በመሰማራት የሃገሪቷን አንጡረ ሓብት በመዝረፍ እና በማሳጣት ስራ ላይ መሰማራታቸው የአደባባይ ሃቅ ነው::ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው የሕወሓት የጦር መኮንኖች እንዲሁም በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ሴቶችን በመድፈር በዘረፋ ከአከባቢው ሲቭል ባለስልጣናት ጋር የተመሳጠረ ሙስና በመስራት የሚከሰሱ ሲሆን ስርኣቱ በስልጣን እንዲቆይ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በአከባቢው እንደሚፈስ ምንጮቹ የተናገሩ ሲሆን የዚህ ገንዘብ ፍሰት የሙስና ተግባራት በሕወሓት የጦር መኮንኖች ይፈጸማል ሲሉ ይናገራል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ረሃብ በኢትዮጵያ፡ ባለስልጣናቱ በእርዳታ እህል መውደቅ ለሞቱ ሰዎች ተጠያቂ ናቸው

3 Comments

  1. The problem the soldiers who are not from Tigris should stand together and does mighty things, TPLF will not be their future solution but freedom, they need to realise this, if we looked those names none of them aren’t Tigris but “Amharas” they should know by now serving TPLF is criminal and needs to stop. Therefore they rather make a history as their ancestors and free the country from TPLF before it is too late for their own lives!!

  2. አራታችሁ ምንም እንኩአን ያላችሁበት ሁናቴ ባይገባኝም ምንም ቢሆን ጠብመንጃና ጥይት ይኖራችሁል ብየ እገምታለሁ እንዼት ታዲያ አራታችሁ አራት አራት የወያነ ባልሰልጣናትን ድባቅ መምታት ተሳናችሁ? ያው እስር ቤት መግባታችሁ አልቀረ አንጀታችሁን አርሳችሁ ብትሞቱ ምን ነበረበት? ስማችሁ ለዘላለም ህያው ይሆን ነበር.

Comments are closed.

Share