ብአዴን ‹‹ሰለሞናዊ›› ስርወ መንግስት!? – (ሊያነቡት የሚገባ የአደባባይ ምስጢር)

የብርሐኔ አበራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ቤተሰብ አባላት አቶ በረከት እና አዲሱበአንድ ወቅት ዜጋ መጽሔት ላይ ታትሞ የነበረና ለግንዛቤዎ ይጠቅምዎታል ብለን እንደገና ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች አቅርበናል።
በአንዳንድ የአገዛዝ ሥርዓቶች በሀብት፣ በመደብ፣ ወይም ዴሞክራሲያዊ ምርጫ፣ አልያም በዘር የተዋቀረ ሥርዓት ይኖራል፡፡ ለምሳሌ በአፄ ኃይለ ስላሴ ጊዜ የነበረው የስልጣን ፍልስፍና ከሰለሞን ስርዎ መንግስት የሚመዘዝ የዘር ሀረግ ባለቤት መሆንን ይጠይቅ እንደነበረ ሁላችንም የምናስታውሰው ነው፡፡ ከሰለሞን ስርዎ (Solomon Daynasty) መንግስት ውጭ ላሉና በዚያ የስልጣን ዘር ሀረግ ውስጥ ያሉ ሆነው በጉልበትም ይሁን በብልሃት ስልጣን ላጡት ስልጣን የሚሰጣቸው በጋብቻ ትስስር እንደነበረ ለማስታወስ የአፄ ኃይለስላሴ ልጆች ከማንና የት ተጋብተው እንደነበረ ማስታወሱ በቂ ምሳሌ ነው፡፡
ከፍ ብዬ የጠቀስኩትን የታሪክና የንድፈ ሀሳብ ማነፃፀሪያ ይዘን የኢህአዴግ አባል ድርጅት ስለሆነው ብአዴን የስልጣን ድልድልና ከሕወሓት በሚሰጣቸው መመሪያ ድርጅቱን በሞኖፖል አንቀው የያዙትን ግለሰቦች የጋብቻ ትስስር፣ በትጥቅ ትግል ዘመን ጊዜ የነበራቸው ተሳትፎን እንዲሁም ዛሬ ያሉበትን ሁኔታ እንደሚከተለው ላቀርብ ተከታተሉ፡–
በክልል ሶስት በዋግ ህምራ ዞን ብርሃኔ አበራ ስለሚባሉ ባልቴት ታጋይ ነው የማወጋችሁ፡፡ ለስሙ የዋግህምራ ዞን ኃላፊ (ሊቀመንበር) ልጃለም ወልዴ ሆኑ እንጅ የዞኑ ህቡዕ መሪ ብርሃኔ አበራ ናቸው፡፡ ይታሰር ያሉት ይታሰራል፤ ይፈታ ያሉት ይፈታል፤ ይባረር ያሉት ሁሉ ከስልጣን ላይ ይባረራል፡፡
ወይዘሮ ብርሃኔ አበራ ለመሆኑ ይኀን ሁሉ ገበሬ ኩሉ ስልጣን ከየት አገኙት? የስልጣን ምንጫቸውን የጨበጡት ከዚህ ቀጥሎ ዝርዝራቸውን በማቀርባቸው ‹‹ታጋይ›› ልጆቻቸው፣ እህቶቻቸውና አማቾቻቸው ወዘተ ነው፡፡
የብርሃኔ አበራ ልጆች
1. መዝሙር ፈንቴ የብአዴን ማ/ኮ አባል የነበረ አሁን የተባረረ፤
2. አሰፋ ፈንቴ፡- የበረከት ስምኦን ሚስት/ሲቭል ሰርቪስ ኮሌጅ የምትማር፤
3. ገነት ፈንቴ፡- አንድ የሕወሓት የደህንነት ባለስልጣን ያገባች፤
4. የሺሀረግ ፈንቴ
5. አሸናፊ ፈንቴ
6. መላኩ ፈንቴ
7. አበባ ፈንቴ፡- የሟቹ ሙሉአለም አበበ ሚስት የነበረች፤ በአገር ውስጥ ጉዳይ የኢሚግሬሽን ቪዛ ኃላፊ የነበረች፤ (የብርሃኔ አበራ እንጀራ ልጅ)
8. አለሚቱ ፈንቴ፡- በክልል ሶስት የምክር ቤት አባል የነበረች፤ አሁን እንግሊዝ አገር ያለች (የብርሃኔ አበራ የእንጀራ ልጅ)
9. ኃይሉ ፈንቴ፡- የጢጣ ት/ቤት አስተዳደር
10. አድና ፈንቴ (የተሰዋች)
የወይዘሮ ብርሃኔ አበራ ታጋይ እህቶች
1. የሺ አበራ የጄኔራል ኃይሌ ጥላሁን ሚስት፣ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል በኃላፊነት ቦታ የምትሰራ፤
2. ነጻነት አበራ፡- የታደሰ ጥንቅሹ (ካሳ) ሚስት ክልል ሶስት በፕሮፖጋንዳ ክፍል ውስጥ የምትሰራ፤
የብራሃኔ አበራ ታጋይ የልጅ ልጆች
1. ውዲቱ አጋዡ፤- መከላከያ ውስጥ የነበረች፤
2. ፍሬህይወት አጋዡ፡- የኢህአዴግ ቢሮ ውስጥ ያለች፣ የውዲቱ አጋዡና የፍሬህይወት አጋዡ እናት የብርሃኔ አበራ ታላቋ ልጃቸው ዋርቃ ናት፡፡
የብርሃኔ አበራ የእህት ልጆች
1. እንወይ ገብረመድህን የጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር (የአዲሱ ለገሰ ሚስት የነበረች)
2. ቢያድጎ፤
3. የዋግህምራ አቃቢ ህግ ሹም-ወይዘሮ እንወይ ገ/መድህን የአንድ ወንድ ልጅና የሁለት ሴት ልጆች እናት ናቸው፡፡ የወ/ሮ እንወይ ልጆች አባት አቶ ብርሃኑ ነጋሽ ዛሬ ነዋሪነታቸውን አሜሪካ አገር ያደረጉ ሲሆን፣ ከባለቤታቸው ጋር የተለያዩት ወ/ሮ እንወይ ገና ወደትግል ሜዳ ከመግባታቸው በፊት ነበር፡፡ ወ/ሮ እንወይ የብርሃኔ አበራ ቤተሰብን በጋብቻ የተዛመደው ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ)ወደ ትግል ከገቡ በኋላ ከአቶ አዲሱ ለገሰ ጋር አንድ ወር ላልበለጠ ጊዜ ጋብቻ መስርተው ነበር፡፡ የአሁኗ የአዲሱ ለገሰ ሚስት የሰቆጣዋ ታምር ተሻለ ነች፡፡ ወ/ሮ እንወይ በአሁን ሰዓት ትዳር የላቸውም፡፡ ወ/ሮ እንወይ ትግሉን ሙሉ በሙሉ የተቀላቀሉት ከ1978 ዓ.ም ወዲህ ነው፡፡ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ኢህዴን ወደ ብአዴን ከተለወጠ በኋላ ነው፡፡ ምንም እንኳ በበረሃው ዘመን የነበራቸው የፖለቲካ ንቃት የኢህዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ሊያደርጋቸው የሚችል የነበረ ቢሆንም፣ ኢህዴን ከሕወሓት የፖለቲካ ፕሮግራም የገለበጠውን ‹‹ፊውዳሊዝም አስፈጊ ጠላታችን በመሆኑ (Threa-tening enemy) በፕሮግራማችን ውስጥ መስፈር አለበት›› የሚለውን አመለካከት ወ/ሮ እንወይ ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያ አብዮትና ደርግ ጠራርገው የጣሉት ስርዓት የሌለ ስለሆነ፣ ስለሌለ ፊውዳሊዝም መሰረታዊ የኢትዮጵያ ህዝቦች ጠላት ነው ብሎ ፕሮግራማችን ውስጥ ማስፈር የለብንም›› የሚል አቋም ነበራቸው፡፡ ይህ አቋማቸው እንዲያውም የኢህአፓን ፕሮግራም ተከታይ አስብሏቸው ስለነበረ ነው በጣባው ኮንፍረንስ የኢህዴን ማ/ኮ አባል ሆነው ሳይመረጡ የቀሩት፡፡
4. ሌላኛዋ የብርሃኔ አበራ የአክስት ልጅ፡- የአቶ ታምራት ባለቤት ሁለት ልጆቿን አሜሪካ ይዛ የገባችው ወ/ሮ ሙሉ ግርማይ ናት፡፡
የዚህ ቤተሰብ የእርስ በእርስ ግንኙነት ሁኔታ
በትጥቅ ትግሉ ዘመን ይህ ቤተሰብ እርስ በራሱ በጣም ይደጋገፍ ነበር፡፡ ከእንወይ ገ/መድህን በስተቀር እስከ 1983 እንወይ ገ/መድህን ከዚህ ቤተሰብ እንዲገለሉ ያደረጋት ታደሰ ጥንቅሹ ነበር፡፡ በ1975 ዓ.ም የኢህዴን የህቡዕ አባላት ተጋልጠው የህይወትና የአካል አደጋ ደርሶባቸው ነበር፡፡ ይህን የህቡዕ አባላት እንቅስቃሴ በጊዜው ይከታተለው የነበረው ታደሰ ጥንቅሹ ነበር፡፡ የእቡዕ አባሎቻችንን ያጋለጠችው እንወይ ነች ብሎ ስላስወራባት ነው እስከ 1983 በመጠኑም ቢሆን ከዚህ ቤተሰብ የተገለሉት፡፡
ሌላኛዋ የዚህ ቤተሰብ አባል ሆና ይኸን ያህል የጎላና እፍ እፍ የቤተሰብ ፍቅር ያልነበራት ወ/ሮ ሙሉ ግርማይ ነች፡፡ እንዲያውም ወደመጨረሻው አካባቢ የአንድ ቤተሰብ አባል ሆነው በባሎቻቸው የስልጣን ከፍና ዝቅ ማለት፣ በአኗኗርና በአለባበስ በወ/ሮ ሙሉ ግርማይና በሌላው ቤተሰብ አባላት ከፍተኛ አለመግባባት ተከስቷል፡፡ አቶ ታምራት ላይኔም ከብርሃኔ አበራ ቤተሰብ ጋር ይዛመዳሉከዚህም በላይ አቶ ታምራት የግንቦት 20 ትምህርት ቤት ይማሩ በነበሩ የዚህ ቤተሰብ አባላት ዘንድ ከፍተኛ ፈንጠዝያ ተፈጥሮ ነበር፡፡
ዘ-ሐበሻ ድረገጽን ሁልጊዜ ያንብቡ። በየሰዓቱ አዲስ ነገር አያጡም።
በትጥቅ ትግሉ ወቅት የዚህ ቤተሰብ ተሳትፎና መስእዋትነት
በመግቢያዬ የዘረዘርኳቸው የዚህን ቤተሰብ አባላት ዋና ዋናዎቹን ነው፤ እንጂ ጠቅላላ በብአዴን ውስጥ ያሉትን ኢህዴን ውስጥ የታገሉት በቁጥር 60 ናቸው፡፡ በትጥቅ ትግሉ ውስጥ የነበራቸውን ተሳትፎ በትክክል ማየት እንድንችል ከዚህ ቀጥዬ ስም ዝርዝራቸውን የማቀርብላችሁ በኢህአዴን ውስጥ እንደታጋይ ታቅፈው ጊዜው ይጠይቅ የነበረውን የትጥቅ ትግል ምላሽ ለመስጠት እንዲችሉ የወታደራዊ ስልጠና (ተአለም) ያልወሰዱትን ነው፡፡
1. እንወይ ገ/መድህን
2. ኃይሉ ፈንቴ
3. የሺሀረግ ፈንቴ
4. ገነት ፈንቴ
5. አሸናፊ ፈንቴ
6. አለሚቱ ፈንቴ
7. ብርሃኔ አበራ ከማስታውሳቸው የዚህ ቤተሰብ አባላት ከፊሎቹ ናቸው፡፡
ሁሉም ሰው መገንዘብ እንደሚችለው በአንድ የሽምቅ ውጊያ ስልታዊ ንቅናቄ ውስጥ የሚገኙ የድርጅት አባላት በሙሉ ትግሉ የሚጠይቀውን የወታደራዊ ስልጠና ወስደው ቢያንስ ራሳቸውን መከላከል በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መገኘት አለባቸው፡፡ ሙያና ምንም አይነት የመጀመሪያ ደረጃ የውጊያ እውቀት የሌለው ታጋይ ጠላት ኃይሉን አጠናክሮ ወደ ድርጅቱ ቤዝ አምባ ሊገባ በሚዘጋጅበት ጊዜ ከእቃ ጋር አብሮ መሸሽ ነበር የመጨረሻ እጣ ፈንታው፡፡ ይህ በደፈናው የሚቀርብ የንድፈ ሀሳብ ትንተና ሳይሆን ኢህዴን ውስጥ በተግባር የታየ ሀቅ ነው፡፡ ይህ ቤተሰብ በትጥቅ ትግሉ ዘመን መሽጎ የኖረው ጠላት ይደርስበታል ተብሎ በማይገመተው የኢህዴን ቤዝ አምባ ውስጥ ነው፡፡ የትጥቅ ትግሉ የሚጠይቀውን የውዴታ ግዴታ ይህ ቤተሰብ ሊፈፅም ባለመቻሉ በተለይ በ1978 አካባቢ በሌላው የድርጅቱ አባላትና ይኸን ቤተሰብ ጉያው ውስጥ በሸጎጠው የኢህዴን ማ/ኮ አባል መካከል ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር፡፡
በወቅቱ ይነሱ የነበሩ ጥያቄዎች ይህ ቤተሰብ ለመስእዋትነት ዝግጁ አይደለም፤ የሌላውን የድሀ ገበሬ ልጅ ላብና ደም እየጋጠ መኖር የሚፈልግ ነው፤ የኢህዴን ማ/ኮ ለዚህ ቤተሰብ (የነማዘር ቤተሰብ) አባላት ልዩ እንክብካቤ ያደርጋል የሚሉ የሰላ ሂሶች ነበሩ፡፡
ከላይ ስለዚህ ቤተሰብ የገለፅኳቸውና ያነታርኩ የነበሩ ጥያቄዎች ምን ያክል ትክክል መሆናቸውን ለማየት ከ60 የቤተሰብ አባላት ውስጥ ስንቶቹ የህይወት፣ ስንቶቹ የአካል መስእዋትነት ከፈሉ የሚለው ጥያቄው በትክክል ይመልሰዋል፡፡ ከዚህ ቤተሰብ ውስጥ የህይወት መስእዋትነት የከፈለችው አድና (ታሪክ) ፈንቴ ብቻ ነች፡፡
በጥይት የቆሰሉ
1.ነፃነት (አምራየ) አበራ በ1977 ዓ.ም ቀስታ ውስጥ ልዩ ስሙ አቡነይ ጋራ በተባለ ቦታ በተካሄደ ውጊያ ዳሌዋ ላይ መጠነኛ የመቁሰል አደጋ የገጠማት ሲሆን በሌላ ውጊያ በጌምድር ክፍለ ሀገር ደጎማ ከተማ በተካሄደ ውጊያ ቀኝ እጇን በብርቱ ቆስላለች፡፡
2.መዝሙር ፈንቴ በ1977 ዓ.ም ዋግ አውራጃ ልዩ ስሙ ተላቁዝቁዛ ይገኝ ከነበረው የኢህዴን ቤዝ አምባ ከራሱ ከመዝሙር ፈንቴ ቤተሰብ ጥይት እግሩ ላይ የመቁሰል አደጋ ገጥሞታል፡፡ ሲጠቃለል ከስድስት ግለሰቦች ውጪ በዚህ ቤተሰብ ላይ የደረሰበት የአካልም ይሁን የህይወት መስእዋትነት የለም፡፡ ስለዚህ የኢህዴን አባላት ለዚህ ቤተሰብ መስእዋትነት ከፈሉ እንጂ ይህ ቤተሰብ ለኢህዴን የከፈለው መስእዋትነት ኢምነት ነው፡፡ እንዲያውም በደም ጎጆ በተገነባ ቤት ውስጥ ተንደላቀው ኖሩ እንጂ ስለነ ‹‹ማዘር›› (ብርሃኔ አበራ) ቤተሰብ ሲነሳ እኔም ጆሮ ዳባ ልበስ ብዬ የማሳልፈው ሀቅ አለ፡፡ የዚህ ቤተሰብ አንድ የእህል ወፍጮ ከቤተሰቡ በላይ እንዳገለገለ መርሳት እኔም የበላሁትን ቂጣ መካድ ይሆንብኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ያሁኑ የኢትዮጵያ ሁነታ፤ ይመስላል የተምታታ - ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

(ዘ-ሐበሻን ያንብቡ0

8 Comments

  1. all this it doesn’t help ETHIOPIAN people one bit,where were you all this time?

  2. First of all I thank the writer for his piece. But as a person who knows some of the family members, I wanted to write what I know too. The above piece has some grain of truth. But much of the story is a bit exaggerated. There is no doubt the family as a whole sacrificed much of their time and property including their life to the struggle, they thought was right at that time. That interest to join the Weyanes emanated from the sufferings their parents underwent under the hands of Derg, The writer didn’t mention that their father and mother were divorced, and the family members who joined Weyane first, convinced their mother to join them in the struggle against Derg in Sekota. The father stayed behind in Korem and he was a devoted Christian with no interest in politics. He had one hotel which was serving the Derg soldiers stationed in the area efficiently. Their hate of Derg was so strong that the mother donated her flour mill to Weyane including all property under her possession. At a time of war, there is no need for everybody to sacrifice her or his life. There is also a need to contribute money and property, as this is also one of the basic needs for a positive outcome. In fact for Weyane, the contribution of the family was too much. The writer said many of the family saved their life. According to him (her), they were not interested to die. First of all, there is no need for all fighters to die in war. Some will always be there. Secondly, war needs not fighters only. These days much of the win comes through propaganda, and many of the family members was doing exactly that kind of thing for Weyane. Alemitu was especially very good at boosting the moral of the rest of the fighters through her spirited talk. She was very bright and highly dedicated. In fact, many thought that she could be one of the ladies who can be part of the current leadership.

    Generally, they showed the gut to fight when we all were enjoying city life or visit schools. So, I give them credit. It would be good if their sacrifices were used for the good of the Ethiopian people. Unfortunately, the result of the struggle was hijacked by Meles and used for his own purposes. That annoys us and all of the family members. That was the reason why Mezimur was unhappy and left them. Many were unhappy when Mulualme was assassinated. Alemitu was shocked with that action because she was the town chief in Debre Markos during the killing. That created a rift among them. Alemitu was quick to understand that things are going not according to her wish and left them and reside in London. Enwey assumed leadership in some of the government offices but was powerless because of the interference of Meles and Bereket.

    To summarize, this is a family who gave a lot to the struggle, but benefited not much from it. Many are still poor with no single house in Addis or Bahir Dar. Alemitu is working in London as hard as many of us to earn something for her own life. I think this is a corruption free family. Except Assefu (Bereket’s wife), many are still lower class. So, give them the credit they deserve. Challenge me with evidences if this is not correct.

    Probably, their major sin would be that they all see Bereket as a nice man, where the rumor is that he and Meles were the man who masterminded the killing of Mulualem. They still think he is a man who can stand for Ethiopia.

    The family was also against Tamirat because they were unhappy that he cheated on his wife (their sister). They are saying that he could file for divorce and do what he liked like what Addisu did against Enwey.

    I hope all of the above clarifies the ambiguity.

    Thanks

  3. after i read this all, i am confused, is it real ? if it is true, i feel so sorry….

  4. Hello Zehabesha,

    This story remind me of the deceased dictator communist Chao Cheshko family who ruled long time the Romanian people. In order to serve the Chaeo government you need to a close family member or otherwise what we call it extended family member. But, at the end of the day, I had observed that this is not a warranty to stay in power for ever. For the second time in my life ( the first one is a red teror campaign commited by derg followers on EPRP members), I saw the body of Chaeo and Ellena ( his wife) bodies lie on the ground covered by snow. The reason was death penality decision of at that time provisional government.

  5. I think formerly epdm and now, biaden should be renamed as :The Agew Dynasty and the servant of the tplf.

  6. ግንግን ኢህደን/ብአደን/አንድ የማመሰግናቸ ነገር ቢኖር ባለራዕዪ መሪ ትግራይንም ጭምር ገንጥሎ ታላቃዋን ትግራይ የመመስረት የነበረውን ህልም አክሽፈዋል::ኢትዮዽያ የሚለውን ስም የሰሙት ኢህደን ከተመሰረተ በሓላ መሆኑን ከራሳቸው አንደበት በአንድ ደክመንተሪ ላይ በኩራት ሲናገሩ ሰምተናል::ብአደን ግን ስሙ ይቀየር::የብርሀኔ አበራ ምንትስየ ንቅናቄ ይባል::ይሄ ይመጥነዋል::

  7. yejegnoch tagayochin sim be-alubwalta mankuwases ayichalim! viva Mother Birhanie; viva ANDM(EPDM) and TPLF

Comments are closed.

Share