ወይ መላ ነሽ አሉ ወይ መላ አባ መላ!

ከሎሚ ተራተራ

እነደምን ከርማችሁ ወዳጆች ? እኔ አምላክ ይክበር ይመሰገን ደህና ነኝ። ሰሞኑን ከወደ ትውልድ አገር የመጡን አዛውንት እንኳን ደህና መጡ፤ የሰሜን አሚሪካ አየርሰ እንዴት ተቀበሎት ለማለት ወደ ጎረቤት ቤት፤ ጎራ ብዪ ነበርና፤ አረፍ እንዳልኩ አንድ ቀደም ብሎ ባለሁበት ከተማ ለጥቂት ወራት በርቀት ዝቅ ብለው እጅ በመንሳት የሃገሬን ተናፋቂ ባህል የሚያሰታውሱኝና እጀግም የማከብራቸውን አባት ድምጥ ሰማሁ።

እንድምነ ዋላችሁ አሉ አቶ በልሁ፤ ድምጣቸውን ያለወትሮዎቸው ለዘብ አድረገው፤ ;;’’’’’ እግዚአብሒር ይመሰገን”’ እንደምን ዋልክ በልሁ ግባ፣ ምነው ? ምን አዲሰ ነገር ሰማህ ደግሞ ድምጥህ ያለወትሮው ለዘብ ብሏል አሉ አቶ ታከለ፤ የዛሪን አያረገወና ልጆቻቸውን ለማየት ወደ ሰሜን አሜሪካ ከመጡ ወዲህ ቀረ እንጂ ድሮማ ሰው ሁሉ የሚጠራቸው “ አልሞ ተኳሸ” እያለ ነበር አሉ።

አቶ በልሁና አቶ ታከለ ለረጅም ግዜ ወዳጆች ከመሆናቸውም ሌላ በወቅቱ የሀገራችን ጉዳይ ዙሪያ ዘወትር በቁጭት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ካላቸው ሃገራዊ ፍቀር በመነሳት መደረግ ሰለሚገባው የሃገር ጉዳይ ፤ በተለይም እንዴት አንድነታቸንን መገንባት እንደሚገባን አበክረው ከሚናገሩት የአካባቢያቸን የሰሜን አሜሪካ አዛውንቷች ዋናዎቹ ናቸው።

ወዲያዉ እግራቸው እንደገባ ወንበርም ላይ ሳይቀመጡ አዬ…; ተወኝ እባክህ…..ሲሉ የሰሙትን ለማጫወት ጀመሩ።, እኔም ኖር;……. በዪ እጅ ከነሳሁ በሗላ ጆሮዪን ሰጥቼ ማዳመጥ ቀጠልኩ፣…… ይገርምሃል ሰሞኑን በዚህ በ “ቡል” ቶክ…ነው.. ”ፓል”ቶክ,,….የሚባል…. የመወያያ መደረክ….. አዪ……ለነገሩ እኔ ይሔንን የመወያያ መድረክ ሳይሆን….”የወሬ ቋት” ነው የምለው። አሉና… ቀጠሉ.. አንድ “አባ…መላ….የሚባል….የ..ወያኔዎቹ አፈቀላጤ.. ሚሰጥር አጋለጠ።……የወያኔን..የግፍ ሰራ መደበቅ (መሸፈን) ደከመኝ..ብሎ ተቃውሞ ሲያሰማ ዋለ። ብዙም ሚሰጥር የማወቀው አለ ብሏል..’…. እያለልሕ …..አዳሜ ተሰበሰቦ ….”ውይ መላ ነሸ አሉ ወይ መላ አባ መላ እያለልህ” ከበሮ፤ ይደልቃል።

ሲሉ ከልቤ ሳቅኩና፤ ፈጠን በዪ ማጋለጡ፣ መልካም አይደለምወይ ብዪ ? ጠየቀኳቸው? ሲመልሱ….እሱማ..መልካም..ነው። አሰገራሚዉ ነገር እኮ አራት ቀን ሙሉ..እንደውም አምሰተኛው ቀን ይኸው መጣ ተሰበሰቦ ማዳነቅ ምን ይሰራል? የተገኝወን መረጃ ሰበሰቦ ተግባራዊ ሰራ ላይ ማተኮር ነው የሚበጀው።

ብለው ሲሉ. በዚሁ ቃላቸው ተሰማምቼ እቸኩል ሰለነበር የሚጣፍጠውን ጫዋታ ገና በእፍታው፤ ትቼ በሉ ደህና ይዋሉ ብዪ ተሰናብቼ ወጣሁና፤ እቤቴ እሰክደርሰ” ወይ መላ ነሸ አሉ ወይ መላ አባ መላ” አሉ አቶ በልሁ፤ እያልኩ እያሰላሰልኩ እቤቴ ደርሰኩና ይቺን ለመጫጫር በቃሁ እላችኸላሁ።

ከላይ ለመመልከት እንደሞከርነው “ወይ መላ ነሸ አሉ፣ ወይ መላ አባ መላ” እያሉ ከበሮ መደልቅ; አባታችን አቶ በልሁ እንዳሉት አይጠቅመንምና መላው ዳይሰፖራውን ይታሰብበት እያለኩ፤ ከዚህ የሚከተለውን ይበጀናል ያልኩትን ብትጠቀምም ባትጠቅምም መፍትሄ ነው። ብዪ ሰለማምን ጀባ እላለሁ።

ዳይሰፖራው ማተኮር የሚገባው፦

1ኛ) በተገኝው ማንኛውም ይጠቅማል የተባሉትን ኢንፎረሜሸኖች በማሰባሰብና በማጠናከር ላልሰማውና ላልተረዳው፣ የህበረተሰብ ክፈል እነዲደርሰ ማደረግና ለውጤቱም ተግቶ መሰራት።

2ኛ) ከማንኛወም አይነት የጥላቻና የ መጎነታተል ወይም የመናናቅ የ ትግል ሰልት መራቅና ወቅታዊና አንገብጋቢው በሆነው የሃገራችን ቸግርላይ በማተኮር ሳንሰልችና ሳንታክት እያንዳንዳችን የድርሻችንን በቅንነትና በኢትዮጲያዊ ጨዋነት ማበርከት።

3ኛ) በወቅታዊው የሃገራቸን የፖሎቲካ፣ የ ኢኮኖሚም ሆነ የመሃበራዊ ችግሮቻችንን እና መፍትሄዎቻቸውንም ጭምር ባለሞያ ወንድሞቻችንንም ሆነ እህቷቻችንን በመጋበዝ ህብረተሰባችን ሰለወቀታዊው የሃገር ችግርና መፍትሄው ማወያየት።

4ኛ) የፖሎቲካ ድረጀቶችም የኔ የፖሎቲካ ፐሮገራም ነው ለወቀታዊው የሃገራችን ችግር ብቸኛ መፍትሄ የሚሆንው። ከሚል አሰተሳሰብ ወጥተን የጋራ የሆነወን የገጠመንን የሃገር ችግር በጋራ አፋጣኝ መፍትሄ ለማምጣት በመቻቻል፤ ተግቶ በጋራ በመሰራት አገር ወሰጥ ላሉት ለፖሎቲካ ድረጅቶች መልካም ኢትዮጲያዊ ሰሜትን በሁሉም መሰክ በመተግበር አጋርንትን በተገበር ማሳየት።

5ኛ) ከሁሉም በላይ ለምናልመውና ለማይቀረው የህዝብ የሃግር ባለቤትነት እያነዳንዱ ዜጋ ድርሻዪ ምንድነው ? በማለትና ለተግባራዊነቱም እውቀቱንም፤ ጉልበቱንም፤ ገንዘቡንም ህይወቱንም ሳይቅር ለመሰዋት የተዘጋጀ መሆን እንዳለበት ማረጋገጥ ነው።

ይህንን ካልተረዳና ለተግባራዊነቱም ካልተዘጋጀን በሰተቀር ቀደም ብዪ በመግቢያዪ ላይ እንደገለጥኩተ ትርፉ አቶ በልሁ እናዳሉት”…

ሆይ… መላ… ነሸ… አሉ… ሆይ,,.. መላ… አባ… መላ…

ነውና… እነዲህ አይነቱን… ባዶ… ከበሮ… ከመደለቅ… ያውጣን! አሜን!!!

በተመሳሳይ መጣጥፍ እሰክንገናኛ ደህና ሁኑ በቸር ይግጠመን! ችርም ያሰማን!

ከሎሚ ተራ ተራ

Wednesday, May-22-13

አሰተያየትዎን/ነቀፊታዎንም ቢሆን: mwl200825@yahoo.com

1 Comment

 1. *******************************
  “ወይ መላ ነሽ አሉ ወይ መላ
  ምን ነገር አወራ ከቶ አባ መላ
  እንዲህ የተቆጨው በልቶ ነው ሳይበላ?
  እኛ ስንናገር እሱ ግን ሲያጥላላ
  ምነው አሁን ጮኸ ሀገር ከተበላ ?
  የትምህርት፣የጤና፣ውድቀት፣መች ታያቸውና
  ድንጋይ ሲቆለል በመስተዋት ተጥበረበሩና
  ሲንጫጩ ሲጮሁ በዕድገት ብልፅግና
  ትውልድ አመከኑ ሀገር ረከሰ ከበረ ሙስና
  እነ አባመላስ ተጠያቂ ናቸው ለኢህአዴግ ብልግና !!።
  ******************************
  ሎሚ ተራ.. ተራ.. የ፭ቱን ነጥብ አደራ ! ይህንን እኛም እንዲሠራበት ተናግረናል መክረናል አባመላ እኛ ስንፅፈው ከነበረው ውጭ የአመጣው ምንም አዲስ ነገር የለም!። ተቃዋሚው ክፍል አመራርና አሠላለፉ ተዘበራረቀበት። የኢህዴግ ደጋፊ የሚያሳዝነው ግን “ተደጋፊ” ሆነው መዝለቃቸው ነው። መሠረቱ ያልፀና ሁሉ ዘላቂነቱ አሳሳቢ ነውና የተደገፉበት ልምጭ እጅግ አሳሳቢና አደገኛ ደረጃ ደርሷል’ ኢትዮጵያ መጀመሪያ ”ሀገር ፍቅር’ የምትል ቱልቱላ ቧልት ሁሉ አሁን ይጋለጣል ባይበላ አይጮህም! ሀገሩም አዘውትሮ አይመላለስም! ከተጠያቂነትም አያመልጥም በለው!!
  ከሀገረ ካናዳ በቸር ይግጠመን

Comments are closed.

Tewahdo
Previous Story

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራው ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የአዲስ አበባው ሕገ ወጥ ሲኖዶስ ለበተነው የሐሰት ጽሑፍ የተሰጠ መልስ

3501
Next Story

በጎንደር ህዝቡ ደፍሮ በአደባባይ ተቃውሞውን አሰማ (VIDEO)

Latest from Blog

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ | አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ | አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል | ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ\  አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

ከመጠምጠም መማርን እናስቀድም!

;በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) አብዛኛው አንባቢ ተገንዝቧል ብዬ እንደምገምተው ሕዝብ ለቡና ቲራቲም፣ ለግብዣ፣ ለበዓል፣ ለሰረግ፣ ለሐዘን፣ ለእድር፣ ለእቁብ ለውይይትና ለሌሎችም ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ሲገናኝ የሚበዛው አድማጭ ሳይሆን ተናጋሪ  ወይም ደግሞ ለመናገር  መቀመጫውን ከወንበር ወይም
Go toTop