የአያት አክሲዮን ማህበርና የስራ አመራሮቹ ላይ በእስርና ከፍተኛ በገንዘብ ተቀጡ

May 22, 2013

(ፍኖተ ነፃነት) የአያት አክሲዮን ማህበር፣ በስራአስኪያጁ አቶ አያሌው ተሰማና በሌሎች ማህበሩ አመራሮች ላይ ላይ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በተመሠረቱባቸው  ክሶች ጥፋተኛ በመባላቸው ዛሬ በልደታ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ወንጀል ችሎት በእስርና ከፍተኛ በገንዘብ እንደተቀጡ የፍኖተ ነፃነት የፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

የፍኖተ ነፃነትየፍርድ ቤት ዘጋቢ እንዳስታወቀው የልደታ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ወንጀል ችሎት ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት አያት አክሲዮን ማኅበር 90 ሚሊዮን ብር፣ የአያት አክሲዮን የማኅበሩ መስራችና ከፍተኛ ባለድርሻ እንዲሁም ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ተሰማ 12 ዓመት እስራት እና 3.2 ሚሊዮን ብር ቅጣት፣ ዶ/ር መሐሪ መኮንን 12 ዓመት ፅኑ እስራት እና 436,646 ብር ቅጣት፣ አቶ ጌታቸው አጎናፍር 10 ዓመት ፅኑ እስራት እና 411,969.60 ብር ቅጣት ተወስኖባቸዋል፡፡  የአያት አክሲዮን የማኅበሩ መስራችና ከፍተኛ ባለድርሻ እንዲሁም ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ተሰማ እና ሌሎች ታዋቂ ነጋዴዎች ላይ ክስ በማቀናበርና በየሚዲያው ማብራሪያ ሲሰጡ የነበሩት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶገብረዋህድ ገ/ጊዮርጊስ በሙስና ተጠርጥረው በቅርቡ መታሰራቸው ያስታውቃል፡፡

1 Comment

  1. ‘ሙስናዊት ሀረካት!”(ማጥፋት) ድራማ …ትልቁ ዓሳ ትንንሾቹን ዓሳ ሲውጣቸው… አዞ ትልቁን ዓሳ ዋጠው …የገቢዎችና ግምሩክ ባለሥልጣን ም/ዳ አቶ ገብረዋህድ ገ/ጊዮርጊስ… በአያት የመኖሪያ ቤቶች ሥራ አስኪያጅና ሌሎች ገናና ነጋዴዎች ላይ ክስ በማቅረብና በእየሚዲያው ማብራሪያ ሲሰጡ ነበር። ይህ የወያኔ ገድሎ የማርዳት ቆሞ የመቅበር ዘመንና ትውልድ ተሻጋሪ ራዕይ ወደፊት በፋውንዴሽኑ ጥላ ቁጭ ብለህ የምትማረው አደለምን!? “think tank” ‘ታንክን አስብ ‘ ትደፈጠጣለህ!! አሁን ወያኔ ካለበት የኢኮኖሚና የቱልቱላ ትራንስፎርሜሽን ለማደናገር ይችን ዓይንት ድራማ በሰፊው ይቀጥላል። አቶ መልስ ትተውት ያለፉት የማይበረዝ፣ የማይከለስ ፣የማይሸራረፍ፣ ለጋሲ …አሁን በታሳሪዎች ላይ ከፍተኛ የገንዘብ ጫና ይጣላል ምክንያቱም ገና ብዙ የእስር ቤት መጣበብና ወጪ አለ። ድሮስ ከቂጥ ቆርጦ ለአንገት የሚሸልም ‘አብዮታዊ ደሞክራሲ’ ይህ አደለምን!? ‘ዓለም በቃኝ’ ሲዘጋ ‘ኢትዮጵያ በቃኝ’ ተከፈተ ይሉሃል ይህ ነው በለው! በሌባ ሁለት እጃችን ተይዟል ያሉት እኛ የሞቱ ጠ/ሚ አንደበታቸው እስኪዘጋ ለምን ዝም አሉ? እሳቸውስ ቡናው ተቆልቶ ሳይሸተን ሲወቀጥ ሳንሰማ ተባነነ ሲባል “ሁላችንም ተነካክተናል እንዳልተያየን እንተላለፍ” አላሉንም እሳቸውም አለፉ !? ያሳለፋቸውም ቆመው ሸኟቸው !? እኛም ተገረምን በለው!!

Comments are closed.

Abrham Desta
Previous Story

! …. ባህር ዳር አነባች…….!

Addis Ababa
Next Story

የኢሕአዴግ የአ.አ ወጣቶች ማህበር 15 አመራሩን አገደ

Latest from Blog

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ንብረቱ እንዲወረስ የሚደነግግ አዋጅ ቀረበ

ዮሐንስ አንበርብር በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሠረተ ንብረት የመውረስ ድንጋጌም በአዋጁ ተካቷል አዋጁ የሚፀድቅ ከሆነ 10 ዓመት ወደኃላ ተመልሶ ተፈጻሚ ይሆናል ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ሰው ወይም ሊታወቅ ከሚችል ገቢው በላይ ሀብት አፍርቶ ምንጩ ሕጋዊ መሆኑን ማረጋገጥ ያልቻለ ሰው፣ ንብረት በመንግሥት እንዲወረስ የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ
Go toTop