June 23, 2014
4 mins read

ማስታወቂያ – ሰላማዊ ትግል 101 መጽሐፍ በግርማ ሞገስ

ሰላማዊ ትግል 101 የተባለው በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው አዲስ መጽሐፍ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ገበያ ላይ ውሏል። ሰላማዊትግል 101 የተዘጋጀውበሰላማዊትግልየኢትዮጵያን ህዝብ የመንግስት እና የአገሩ ባለቤት በማድረግ ኢትዮጵያን ወደ ዴሞክራሲለማሸጋገር የሚሹአገርወዳድኢትዮጵያውያንበተለይም ወጣቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ ትምህርታዊየመወያያመጽሐፍእንዲኖረውታቅዶ ነው።ስለዚህ ሰላማዊ ትግል 101 በአቀራረቡም ሆነ በይዘቱ የውጭ አገር ቅጅ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ነው።

ለዘመናት በእርስ በርስ ጦርነት (Civil War) ሲፈጸም የነበረው የመንግስትሽግግርባህላችንንየግድ ማቆም እንዳለብን ግንዛቤ ለመስጠት ሰላማዊትግል 101 ከአክሱም ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ የተደረጉት የመንግስት ሽግግሮች በህዝባችን እና በአገራችን ላይ ያደረሱትን አሳዛኝ ሃቅ በጭሩ ይተርካል።

ከአልበርትአነስታይንሰላማዊትግልምርምር ተቋምዘመናዊስራዎችውስጥ ጠቃሚዎቹን አቅልሎ ከማቅረቡ በተጨማሪ መጽሐፉ በ232 ገጾቹ ኢትዮጵያ ለምን ኋላ እንደቀረች፣ ሰላማዊ ትግል ከክርስቶስ ልደት ቀደም ብሎ ጀምሮ በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጭ ያደረገውን እድገት፣ የመንግስት ስልጣን ባለቤት ህዝብ ነው የሚለው ጽንሰ አሳብ ከፖለቲካ ኃይል ምንጮች ባለቤትነቱ ጋር ያለውን ዝምድና፣ ፣ የፖለቲካ ኃይል ምንጮች እና የፖለቲካ ድጋፍ ምሶሶዎች ምን እንደሆኑ፣ ከ200 የሰላማዊ ትግል መፈጸሚያ መሳሪያዎች ውስጥ ዋናዎቹን፣ ሰላማዊ ትግል ህዝብን እንዴት የራሱ ነፃ አውጭ እንደሚያደርገው፣ በሰላማዊ ትግል የሲቪክ ድርጅቶች ሚና ምን እንደሆነ፣ ሴቶች ከሰላማዊ ትግል ጋር ያላቸው ተፈጥሮዋዊ ትስስር፣ በአሜሪካ አፍሪካ-አሜሪካውያን ለነፃነት ያደረጉት ሰላማዊ ትግል በሙሉ በቀላሉ ይተነትናል።

ሰላማዊ ትግል 101 በምርጫ እና በሰላማዊ ትግል መካከል ያለውን ትግግዝ ያብራራል። በተጨማሪ ዴሞክራሲ በዳበረበት በምዕራቡ አለም እና አምባገነኖች በሚገዟቸው አገሮች የሚደረጉ ምርጫዎች የተለያዩ መሆናቸውን፣ በአምባገነን አገሮች በሚደረጉ ምርጫዎች በሰላማዊ ትግል የህዝብ ድምጽ እንዳይሰረቅ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በሰርቢያና በዝምባቡዌ የተደረጉትን ምርጫዎች እና የተፈጸሙትን ሰላማዊ ትግሎች በንጽጽር ይተነትናል። የግብጽ ወጣቶች ስላደረጉት ሰላማዊ ትግል እና የምርጫ ፓርቲዎች ስለሰሩት ስህተት ቀርቧል።

የምርጫ ታሪካችንን በሚመለከት ደግሞ መጽሐፉ ከኃይለስላሴዘመነመንግስትጀምሮለ80 አመታትያህልበኢትዮጵያየተደረጉትንምርጫዎች ይገመግማል።  ግምገማው ለምርጫ 97 ትኩረት ይሰጣል። ምርጫ 2007ን አስመልክቶም መጽሐፉ በክልሎች እና በፌዴራል ደረጃ በሚደረጉ ምርጫዎች የምርጫ ፓርቲዎች ማድረግ ስለሚገባቸው ዝግጅቶችም ውይይት ይከፍታል። መልካም ንባብ። መልካም ውይይት።

 

 

 

ethiopia parliament
Previous Story

የ2007 የመንግሰት በጀት ሚስጥር

10478183 742597102465708 4057302345624676295 n
Next Story

በሐዋሳ በ3 ጣቢያዎች የታሰሩት የአንድነት ፓርቲ አባላት ዛሬም ፍርድ ቤት አልቀረቡም

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop