ወያኔ ባለስልጣናቱን አቶ መላኩ ፈንታን እና ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን አሠረ

May 10, 2013

አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ ብአዴኑ መላኩ ፈንታ እኚህ ናቸው።
(ዘ-ሐበሻ) የወያኔ ሥርዓት በኢትዮጵያ ብቻውን ያሸነፈበትን ምርጫውን ሙሉ በሙሉ አሸንፌያለሁ በሚል ከማወጁ አስቀድሞ የሕዝቡን ስሜት ለመቀየር አቶ መላኩ ፈንታ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተርን እና ምክትላቸውን አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ 12 ሰዎችን በሙስና ጠርጥሮ ማሰሩን በሰበር ዜና አብስሯል።
መላው የወያኔ/ኢሕአዴግ ባለስልጣናት በሙስና የተጨማለቁ መሆናቸው በይፋ የታወቀ ሲሆን ስርዓቱ የጸረሙስና ሕጉን የፖለቲካ ልዩነት በሚያሳዩ ባለስልጣናት ላይ ብቻ ተግባራዊ በማድረግ ሲተች ቆይቷል የሚሉ ታዛቢዎች ከዚህ ቀደም አቶ ታምራት ላይኔ በሙስና ሲታሰሩ፣ አቶ ስዬ አብርሃ ከነቤተሰባቸው ዘብጥያ ሲወርዱ፣ አቶ ቢተው በላይ እና አባተ ኪሾም እንዲሁ ከርቸሌ ሲወረወሩ የጸረሙስና አዋጁ ተግባራዊ የሆነባቸው ከድርጅታቸው ጋር የፖለቲካ ልዩነት በማምጣታቸው እንጂ እውን አዋጁን ተግባራዊ ከማድረግ ጋር በተያያዘ አለመሆኑን በአስተያየታቸው ላይ ተናግረዋል።
አቶ ይሁን ተድላ የተባሉ ታዛቢ የዛሬውን የገቢዎችና የጉምሩክ ባለስልጣናት መታሰርን ተከትሎ የሰጡት አስተያየትም ከዚሁ የሚለይ አይደለም። እኚህ አስተያየት ሰጪ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ “አቶ መላኩ ፈንታ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ለእስር የተዳረጉበት ወቅታዊ ምክንያቱ በ አማራው ብሔር ከደቡብና ከቤንሻንጉል ክልል መፈናቀል ጉዳይ ላይ በብአዴን ውስጥ በተፈጠረ የተለያየ አቋም ድርጊቱን በተመለከተ ግለሰቡ ህወሃት ላይ ጣታቸውን በመቀሰራቸው ነው የሚል ጥርጣሬ አለ። ወያኔ ታማኝ አገልጋዮቹን ለክፉ ጊዜ ብሎ ባሰናዳላቸው ወጥመድ በቀላሉ ወንጅሎ ወደ ወህኒ ሊያወርዳቸው እንደሚችል የተረጋገጠ ነው። በመሆኑም የአቶ መላኩ ፈንታ አሁን ተይዘው ወደ እስር ቤት የተወሰዱበት ምክንያት ሁሉም የኢህአዴግ አባላት ንጹህ በማይሆኑበት ሙስና ተጠርጥረው ነው የሚለው ፕሮፓጋንዳ ሚዛን የሚደፋ አይደለም። ከደብረፅዮን ቢሮ ሾልኮ የወጣው ወሬ እንደሚያመለክተው ከሆነ አቶ መላኩ ፈንታ ለጊዜው ወደ አልታወቀ ሀገር ለመኮብለል ሲዘጋጁ ኤሌክትሮኒክ መልዕክታቸው በመጠለፉ ነው።በዚህ ላይ አቶ መላኩ ፈንታ በሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በሃላፊነት ሲሰሩ የሚያውቁት የደህንነትና የድርጅት ሚስጥሮች ስላሉ የግለሰቡ ከሀገር መኮብለል ተመጣጣኝ ስልጣን እንደነበራቸው አቶ ጁነዲን ሳዶ ኩብለላ በቀላሉ የሚታይ አይደለም በሚል የውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ።አብረዋቸው የተያዙት የህወሃቱ እና ሌሎች ባለስልጣናት ግልፅና ተጨባጭ ከሆነው የባለሥልጣኑ መስሪያ ቤት የሙስናና የአሰራር ንቅዘት አኳያ አቶ መላኩ ፈንታ ለታሰሩበት እውነተኛ ምክንያት ጥሩ የወያኔ ሽፋን እና ማጭበርበሪያ እንደሚሆኑ ታዛቢዎች ይገልፃሉ።” ይላሉ።
የኢቲቪን ዜና ይመልከቱ፦

11 Comments

 1. ኢህአዴግ ለጥፋት የቆመ ድርጅት እንደመሆኑ አባላትን በሙስና እያማለለ መሳብ አለበት። ሙስና ውስጥ የገባ ባለስልጣን ደግሞ ሰጥለጥ ብሎ ከመገዛት በቀር የተቃውሞ ድምፅ ማሰማት አይችልም። ይህን የለተፃፈ ህግ ሲተላለፍ ደግሞ የሙስና ካርድ እየተመዘዘበት ዘብጥያ ይወርዳታል። ከታምራት ላይኔ እስከያረጋል አይሸሹም ድረስ ሲፈፀም ያየነው ይሄንኑ ነው። አሁንም ስለመላኩ ፈንታ ያቀረባችሁት ትንታኔ ነገሮች በተለመደው መንገድ መቀጠላቸውን የሚያሳይ ነው።

 2. Ethiopian reviewoch ebakachu wegentetegna atihunu lela gize weyane be musina hager gedele tilalachu gin Melaku Fanta amara silehone bicha lemin tasere alachu. Ene betam azinalew woyanem enantem metfo yezeregnnet abaze alebachu. Please to be rational unless ur news never different from addis zemen or ETV news. God bless Ethiopia.

 3. ምን አለ አንዳንዴ አንኩዋን እውነት ብትጽፉ፡ ስው በሙስና ሲታስር አማራ ስለሆነ ነው ማለትን ምን አመጣው…ግዜ አችሁን በውሽት ጨረሳችሁት…የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ የሚባለው ይህን ዜና ለጻፈ ስው ነው።

 4. All these greedy hyenas will descend to the pit one by one. They are there to fill their stomach and when the game of looting is up the next step is down to prison. We are witnessing these hyenas eating each other up.

 5. I will trust when TPLF corrupt military generals thrown to jail, unless forget it!!!!!!!!!!

  Usual TPLF bullshit!!!!!!!!!!!!

 6. ye musna emebet woinm woizero Zerfeshual be mebal yemtitawekew Azeb Gola bale ra eyu bepayroll bemikefelew neber sintedader yeneberw yalchiw neger teqebaynet agigntual mallet naw!!!! …bayhonma musna neger ke tenesa megemeria zebtia mewred yalebachew esuana ye woyane generaloch nachew!!!!…

 7. Gobez kehonu kehager wuchi tezerfo yetekemachewen genzeb yasmelisu. melaku leba lihon yichilal. Yebelete degmo yewoyane lebenet abatoch ena enatoch Alu re: Azeb mefin, Abo sebhat, Generals, Bereket Simon, Abadulla, Junedin Sado, lelochim be 1000 yemikoteu!!!

 8. mekawem begna hager endezihe kehone tasazenalachu shola bedefen malete enante nachu ande wente yalachu eprdf musena ale tekekle nachu gen letewelede yemiterfe setefelegu amara degmo koyetachu lela debube benishangul atkalaye huluneme mekawme ahun bezihe laye yememekrachu betelu yemishalach bertu lelochem alu neber gen tasazenalachu lemane enaneten yekebedale oh egzibhair eth. Barkat ateleyayen

 9. እንደልቡና ኦልጂራ፣ ፅሁፉን በፅሞና ያነበባችሁት አልመሰለኝም። አቶ መላኩ ፈንታ አማራ ስለሆነ ታሰሩ አልተባለም እኮ! የተባለው በፖለቲካ ልዩነት (ማለትም የአማሮችን መፈናቀል ስለተቃወሙ) ታሰሩ ነው። በፖለቲካ ልዩነት ሳቢያ ሰዎችን በሙስና ሰበብ ማሰሩ ደግሞ የቆየ የኢህአዴግ አሰራር መሆኑ የአቶ ስዬ አብርሀ ከነእህትና ወንድማቸው ጋር እና የአቶ ቢተው በላይ መታሰር በምሳሌነት ቀርቦአል። ስለዚህም በሌላ አትተርጉሙት።

Comments are closed.

fergusen davids moyes
Previous Story

ዴቪድ ሞይስ ሰር አሌክስ ፈርጉሰንን ተኩ

melaku fenta
Next Story

የታሰሩት ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች ስም ዝርዝር (ይዘናል)

Latest from Blog

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት

የኢካን ዓላማ በኔዘርላንድ የሚኖረውን ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያውያንን ኮምዩኒቲይ የማሰባሰብ ሳይሆን የመከፋፋልና የማዳከም ተልኮን ያነገበ ነው።

አገር ! ለየአንድ ሠው ቋንቋው፣ ልማዱ፣ ባሕሉ፣ እምነቱ፣ አስተሳሰቡ፣ ወጉና በአጠቃላይ እሱነቱና ማንነቱ የሚከበርበት ብቸኛ ሥፍራ ነው። ኢትዮጵያውያንም በስደት በሚኖሩባቸው አገራት ሁሉ እነኝህን በስደት ያጧቸውን የግልና የጋራ ማንነቶቻቸውን በአንድ ላይ ሆነው ለመዘከር

ፋኖ ምሽጉን ደረመሰው ድል ተሰማ | ” ስልጣን እለቃለሁ ” ፕረዚዳንቷ | ህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ | “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ

-966+9-የኦህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ – ስልኩ ተጠለፈ “እኛ የምን’ዘጋጀው ለፋኖ ሳይሆን ለኤር-ትራ ነው” አበባው|”በጊዜ ቦታ አዘጋጁልኝ” አረጋ

አንድ በኢኮኖሚና በሌሎች ነገሮች ወደ ኋላ የቀረች አገር አንድን ኃያል መንግስት በመተማመንና ጥገኛ በመሆን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማምጣትና የተሟላ ነፃነትን መቀዳጀት ትችላለች ወይ?

ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ሰኔ 4፣ 2016 (ሰኔ 11፣ 2024)   በዚህ አርዕስት ላይ እንድጽፍ የገፋፋኝ ዋናው ምክንያት ሰሞኑኑ ዶ/ር ዮናስ ብሩ የቻይንንም ሆነ የቬትናምን በኢኮኖሚ ማደግ አስመልክቶ ሁለቱ አገሮች እዚህ ዐይነቱ የዕድገት ደረጃ ላይ ሊደርሱ የቻሉት ከአሜሪካ ጋር

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት አብይና ዳንኤል ክብረት ጉድ አሰሙ-|ጀነራሉ በቁ*ጣ ተናገሩ-‘ህዝቡ ጉድ ሰራን’-|“ብልፅግናን ራ*ቁቱን አስቀርተነዋል”-|ታዳሚው ባለስልጣናቱን አፋጠጠ
Go toTop