April 12, 2014
5 mins read

ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

Blue Advert April 12

አዲስ አበባ፡- ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹የተነጠቁ መብቶችን እናስመልስ!›› በሚል መሪ ቃል ሚያዚያ 19/2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከአሁን ቀደም የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ምላሽ እንዲሰጣቸው ቢጠይቅም ጥያቄዎቹ ምላሽ ያልተሰጣቸው ከመሆኑም ባሻገር ጭራሹን እየተባባሱ በመምጣታቸውና ህዝብም እየተማረረ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፉን መጥራት እንዳስፈለገ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 2005 ዓ.ም ያደረገውን ጨምሮ በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፎችንና ህዝባዊ ስብሰባዎችን ባደረገበት ወቅት የኑሮ ውድነት፣ የእምነት ጣልቃ ገብነት፣ ሉዓላዊነት፣ ዜጎችን ከቀያቸው ማፈናቀልና ሌሎችም መሰረታዊ ጥያቄዎችን አንስቶ የነበረ ቢሆንም ጥያቄዎቹ ምላሽ ሊያገኙ እንዳልቻሉ የህዝብ ግንኙነቱ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ በእስልምና እና ኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ የሚደረገው ጣልቃ ገብነት፣ ዜጎችን ከቀያቸው ማፈናቀሉ፣ የኑሮ ውድነት፣ ሙስና አሁንም ድረስ ተባብሰው መቀጠላቸው ሰላማዊ ሰልፉን በመጥራት ህዝቡ እነዚህን የተነጠቁ መብቶች እንዲያስመለስ ማስተባበርና ማታገል የግድ በማለቱ ነው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ለገዥው ፓርቲ ስልጣን እንጅ ለህዝብ አገልግሎት የማይጨነቁት ተቋማት ስራቸውን በሚገባ ባለመስራትቸው ህዝብ ለከፈለው ክፍያ የሚገባውን አገልግሎት እያገኘ አለመሆኑም ሌላኛው ሰላማዊ የሰልፉ ምክንያት መሆኑን ተገልጹዋል፡፡ በተለይ የውሃ፣ የመብራት፣ የቴሌኮሚኒኬሽንና የትራንስፖርት አገልግሎቶች ህዝብን እያማረሩ መቀጠላቸው መፍትሄ ስለሚያስፈልገው የሰላማዊ ሰልፉን አስፈላጊነት እንዲሚያጎላው ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

ምንም እንኳ ‹‹የህዝብ መብት መነጠቅና የአግልግሎቶች እጦት ሰላማዊ ሰልፉን ወቅታዊ ቢያደርገውም የሰማያዊ ፓርቲ በአመት ውስጥ ከያዛቸው ፕሮግራሞች መካከል አንዱ ህዝብ የተቀማቸውን መብቶች ማስመለስ መሆኑንና ይህም በተደጋጋሚ በተለያዩ ሚዲያዎች መገለጹን›› አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ገልጸዋል፡፡

ሰላማዊ ሰልፉ እሁድ ሚያዚያ 19 ከቀኑ 4 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት ካሳንቺስ ከሚገኘው የፓርቲው ጽህፈት ቤት እስከ ጃን ሜዳ እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን ጃን ሜዳ የተመረጠበት ምክንያትም መብቱን የተነጠቀውና ማህበራዊ አገልግሎቶችን በሚገባ ማግኘት ያልቻለው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ጥያቄዎቹን እንዲያነሳ ሰፊ ቦታ በማስፈለጉ ነው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በየ ክፍለ ከተማው የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሰላማዊ ሰልፉን ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ የገለጹት ኃላፊው ‹‹በሀይል የተቀሙትን መብቶችን ለማስመለስ በሚደረገው ጥረት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ ሚዲያውና እያንዳንዱ ዜጋ ተሳትፎ በማድረግ አገራዊ ግዴታውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Source: – ነገረ ኢትዮጵያ

3 Comments

  1. Why is blue party not organizing it with the udj ? Are they competing with udj or struggling for the cause of freedom ? The udj has already called for a demonstration. It will be held either miazia 19 or 26. To jump in the middle of this is not giving political courtesy and respect to other oppositions. I think such immature, emotional, divisive and confrontational group like the blue party are dangerous. The udj ought to give distance from these people and focus on the big picture.

  2. Why are this people calld for demonstrations? Is it worthy to demonstrate on everything? if soup expensive protest,if you sneezing they will protest again.I am sure This people trying to use protest to overthrow the government by creating chaos just like 2005, they are hoping out of 50 protests maybe one will be successful…

  3. ምን ነካቸው ሰማያዊዎች ? የሚታገሉት ወያኔን ነው አንድነትን ? አንድነት ሰልፍ ለማድረግ ግብርብር ፈጥሮ እነርሱ አብረዉ መስራት ሲገባቸው ለብቻቸው ሰልፍ መጥራት፣ በርግጥ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አስበው ነው ወይንስ አንድነትን ለማሳጣት ? እኔ አሁን እየጠረጠርኩኝ ነው የአመራር አባላቱ ከወያኔ ጋር ይሰሩ ይሆን እንዴ ?
    ሁልጊዜ አንድነት አንድ ዝግጅት ሲያደርግ ይሽቀዳደሙና እነርሱም አንድ ነገር ለማድረግ ይሞክራሉ። አንድነት በመስከረም 5 በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ሲጥየራ፣ እነርሱን ነሐሴ 28 ጠሩ። አንድነት በድንበር ጉዳይ ላይ አንድ እሁድ ቀን ፓናል ዲስከችን ሲያደርግ እነርሱ በጎንደር ሰልፍ ጠሩ ፣ ቅዳሜ ደግሞ እነርሱን በድንበር ጉዳይ ላይ ፕላን ዲስከችን አደረጉ። የአንድነት ፓርቲ እና ሚአድ በባህር ዳር ሰልፍ ሲጠሩ፣ ቅስቀሳዉ ተጧጡፎ ባለበት ወቅት፣ እነርሱን አብረው መቀላቀል ሲገባቸው፣ ድረዳዋ የራሳቸዉን ዝግጅ አደረጉ። (ብዙ ሰው አልመጣላቸውም እንጂ) ። አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ የ እሪታ ቀን አዉጆ ሰልፍ ሲጠራ፣ እነርሱም «እኛ ተረሳን» በሚል ነው መሰለኝ እነርሱን ሰልፍ ጠሩ። የርሳቸውን ሥራ እየሰሩ ሳይሆን እነዚህ ሰዎች ያሉት አንድነትን እየተከታተሉ በአንድነት ላይ ትግል እያደረጉ ናቸው።
    ሰማያዊዎች፣ እንደዉ እነ አልማሪያም እና ጥቂት ዳያስፖራዎች አናታቸው ላይ ሲያወጧቸው፣ በጥጋብ ተሞልተዋል። «ያለ እኛ ተቃዋሚ » የለም የሚል ባዶ እብሪት እየተሞሉ ነው። የሚያደርጉትንሥራ ትግሉን የሚረዳና የሚያስተባበር ሳይሆን ከፋፋይ ሥራ ነው። ሰማይዊ እያላችሁ ሆይ ሆይ የምትሉ ሁሉ ልብ በሉ።
    አንድነቶችን በተመለከተ ሰማይዊዎች ባበዱ ቁጥር ብዙ ቦታ ሰጥተው የሚጨነቁ አይደሉም። የሚሰሩት ያወቃልኩ: በርካታ፣ በጥንቃቄ፥ በማስተዋል፣ ከገለባ የስሜት ፖለቲክ ጸድተው ሕዝቡን እያደራጁት ነው። ከመኢአድ ፣ ከአረአን አብሮ መስራት ከሚፈልግ ድርጅት ጋር ሁሉ ለመተባበር ፣ ለመዋሃድ ጥረት እያደረጉ ነው። አንድነት ኃይል አለው። አንድነቶች ሕዝቡ ወደ አንድነት ለማምጣት የሞአይደርጉት ጥረት ይግፉበት። ሰማይዊዎች ከእብደታቸው ከተመለሱ ይመለሱ። አሊያም ቤብደታቸ መቀጠል ከፈልጉ ፣ መንገዱን ጨርቅ ያርግላቸው።

Comments are closed.

Previous Story

የኢቲቪ “የቀለም አብዮት” ስጋት!

Next Story

የቀደመ ውን ፍቅርህን ትተሃልና የምነቅፍብህ ነገር አለኝ።

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop