ይድረስ በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድሐኒአለም ቤተ ክርስቲያን ለምትገኙ ክርስቲያን ወንድሞቼ እና እህቶቼ፤
እንኳን ለሆሳእና በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
ነበር ለካ እንዲህ ቅርብ ነበር እንዲሉ፤ ባለፉት ዓመታት ደብረ ሰላም መድሐኒአለም በሰሜን አሜሪካ ካሉ አድባራት በታላቅነቱ ከሚጠቀሱት ውስጥ ነበር ብል ማጋነን አይሆንብኝም። እኛን ምእመናኑን ሆነ እንግዶችን እጅጉን ባስደነቀ ግሩም አገልግሎት ኢትዮጵያ ያለን እስኪመስለን ድረስ በታላቅ ደስታ አምላካችንን በቅዳሴው፣ በማህሌቱ፣ በመዝሙር ስናመሰግን ኖረናል። በእንግድነታችን ሀገር እግዚሃብሄር ፈቃዱ ሆኖ በቤተ መቅደሱ በስርዓተ ተክሊል ጋብቻ ፈጽመን፤ ልጆቻችንን በ40 ቀን በ80 ቀን አስጠምቀን፣ በስጋ ለተለዩን ጸሎተ ፍትሃት አድርሰን ለዓመታት በሰላም በፍቅር እዚህ ደርሰናል። አንዳችን ለሌላው የክፉ ቀን ደራሽ ሆነን፣ ሀዘናችንን ተጋርተን …..ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ…