የክርስቲያኖ ሮናልዶ 28 ልዩ ቀናት (Updated)

April 26, 2013

ከ ይርጋ አበበ
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር የካቲት 5/ 1985 ዓ.ም በፖርቹጋሏ ገጠራማ ከተማ ሳንቶ አንቶኒዮ የተወለደው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ዶሳንቶስ አቬሮ የዛሬ የእዚህ ገጽ እንግዳችን ነው።
የእግር ኳስ ሕይወቱን ገና በ8 ዓመቱ ነው የጀመረው። አንዶሪና ለሚባለው የአካባቢው አማተር ክለብ በእዚህ ዕድሜው መጫወት ጀምሮ በሲ.ዲ ናሽናል ጎለበተ። በሲ. ዲ ናሽናል ክለብ ለሁለት ዓመታት ቆይታ ካደረገ በኋላ የፖርቹጋሉን ኃያል ስፖርቲንግ ሊዝበን የግሉ አደረገው። 28 ቁጥር ማሊያ ለብሶ በፖርቹጋል ሊግ መታየት የጀመረው የዛሬው የ28 ዓመት ኮከብ በስፖርቲንግ ሊዝበን የአንድ ዓመት ቆይታው አርሰን ቬንገርንና አሌክስ ፈርጉሰንን ጨምሮ የታላላቅ ክለብ አሠልጣኞች ዓይን ያርፍበት ጀመር። በውድድሩ በለስ የቀናው ግን የላንክቫየሩ ክለብ ማንዩናይትድ ነበር በ12 ነጥብ 24 ሚሊዮን ፓውንድ የግሉ አደረገው።
ምንም እንኳ በእንግሊዙ ታላቅ ክለብ በርካታ ሥራዎችን የሠራ ቢሆንም በእዚህ ጽሑፍ ለአንባቢያን ለማቅረብ የሞከርነው ግን በሪያል ማድሪድ ክለብ ውስጥ ያከናወናቸውን አብይ ክንዋኔዎች ለይተን 28ቱን ብቻ ነው። በእዚህ ጽሑፍ ውስጥ የምንጠቀመው የአውሮፓውያን አቆጣጠር መሆኑንም እንገልጻለን።

ክፍል 1
ሐምሌ 1/ 2009
በወላጅ እናቱ ጎትጓችነት የሚወደውን የሰር አሌክስ ፈርጉሰንን ቡድን ለቅቆ ወደሚወዱት ሪያል ማድሪድ ክለብ የተዘዋወረበት ቀን ነው። 80 ሚሊዮን ፓውንድ ወይም 131 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር ማሬንጌዎቹን ያስወጣው ፖርቹጋላዊ በእዚህች ቀን የ6 ዓመት ኮንትራቱን ሲፈራረም ከ80 ሺ በላይ ደጋፊዎች በደማቅ ሥነ ሥርዓት ነበር የተቀበሉት። ይህ የደጋፊዎች ቁጥር ደግሞ ዲያጎ ማራዶና ከባርሴሎና ወደ ናፖሊ ሲዘዋወር ከተቀበሉት 75,000 ደጋፊዎች የላቀ ሆኖ ተመዝግቧል።
ነሐሴ 29 ቀን 2009 የስፔኗ ዋና ከተማ ክለብ በሜዳው ዲፖርቲቮ ላኮሮኛን 3ለ2 ሲያሸንፍ ግብ የማግባት ሥራውን አንድ ብሎ የጀመረበት እለት ነው። በሪያል ማድሪድ እግር ኳስ ክለብ ታሪክ ከፍተኛ ክብር የሚሰጠውን የአልፍሬድ ዲስቲፋኖን 9 ቁጥር ማሊያ ለብሶ መጫወት የጀመረው CRገ አሁን ለክለቡ ካስቆጠራቸው 193 ግቦች ሁሉ ቀዳሚዋን ግብ ያስቆጠረው በእዚህ እለት ነበር።
ግንቦት 5/ 2010
በእዚህ ዕለት ደግሞ የቀድሞው የሳሙኤል ኤቶ ክለብ የነበረው ሪያል ማዮርካ የክርስቲያኖ ሮናልዶን ሦስት ግቦች (ሀትሪክ) የተስተናገደበት ክለብ ነው። በማሬንጌዎቹ ቆይታው በድምሩ 15 ሀትሪኮችን ቢሠራም የመጀመሪያውን ሀትሪክ ለማስቆጠር ሪያል ማዮርካዎችን መጠበቅ ግድ ሆኖበት ነበር።
ሐምሌ 3/ 2010
ለነጭ ለባሾቹ የፈረመበትን የመጀመሪያ ዓመት እያከበረ ነው። ይህች እለት ግን ሌላ ዜና ይዛለት መጥታለች። ዜናው ከመስከረም 2005 በ52 ዓመታቸው ሕይወታቸው ያለፈውን ወላጅ አባቱን ማስረሻ የሚሆን ነው። እ.አ.አ ሐምሌ 3/ 2010 ክርስትያኖ ሮናልዶ የልጅ አባት ሆነ። የልጁ እናት ማንነት አወዛጋቢ ቢሆንም ክርስቲያኖ ሮናልዶ ግን ሮናልዶ ጁኒየር የሚል ስም የተሰጠውን ልጅ ያገኘው ከላይ በተጠቀሱት እለት ነበር።
መጋቢት/3/ 2011
ለሀገሩ ሲጫወት ከደረሰበት ጉዳት አገግሞ ወደ ሜዳ የገባበት እና በማላጋ መረብ ላይ ሦስት ግቦችን ያሳረፈበት እለት። ለ10 ቀናት ቁምጣና ታኬታ መልበስ ያልቻለው ፈጣኑ ልጅ በእዚህ ዕለት ኳስ ናፍቆት እንደነበር ያሳየበትን ጨዋታ ነበር ያደረገው።
ሚያዝያ 20/2011
ከመጋቢት ሦስት እስከ ሚያዝያ 20 ድረስ ባሉት 6ሳምንታት ውስጥ 6 ግቦችን በማስቆጠር እ.አ.አ በ2007/08 ማንቸስተር ዩናይትድ በነበረበት ጊዜ በዓመቱ ያስቆጠረውን 42 ግብ የማግባት ክብረ ወሰን የተጋራበትን ጀብዱ ፈጽሞ ነበር ለሚያዝያ 20 የኤል ክላስኮ ጨዋታ የደረሰው። 103 ደቂቃዎችን በፈጀው በእዚሁ የኤል ክላሲክ ፍልሚያ ማሬንጌዎቹ ብዎሉ ግራናዎቹን አሸንፈው የኮፓ ዴልሬይ ዋንጫን ሲያነሱ መልከ መለካሙ ሮናልዶ ከኢማኑኤል አዲባየር የተሻገረችለትን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ከቪክቶር ቫልዴዝ መረብ ውስጥ ጨመራት።
ግንቦት 7/ 2011
የኢንዶኔዢያ ክለብ ሲቪያ በሜዳቸውና በደጋፊያቸው ፊት አንገት የሚያስደፋ ውጤት ሲያስመዘግቡ ግብ አነፍንፊው ፖርቹጋላዊ 4 ግቦችን ለግሉ ሲያስመዝግብ ለቀሪዎቹ ሁለት ግቦች የነበረው ሚናም ከፍተኛ ነበር። እነዚህ ግቦች በዓመቱ ያስቆጠራቸውን ግቦች ድምር ወደ 46 ያሳደጉለት ነበሩ።
ሜይ 15/2011
ከአራት ቀን በፊት በጌታፌዎች መረብ ላይ የዶላቸው ሦስት ግቦች 49ኛ የውድድር ግቦች ሲደርስ ግንቦት 15/2011 ምሽት ደግሞ ሌላ ታሪክ ሠራ። ቀደም በሁጎ ሳንቼዝ እና በቴልሞ ዛኑ ተይዞ የነበረውን 38 የሊግ ግብ የተጋራበትን ግብ ቪላሪያል መረብ ላይ አሳረፈ።
ግንቦት 21/2011
የዓመቱ የመጨረሻ ጨዋታ አልሜሪያ ከሪያል ማድሪድ በሳንቲያጎ ባበርናባው ክለቡ ሪያል ማድረድ በ37 ጨዋታዎች 97 ነጥቦችን ሰብስቦ ከባርሴሎና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት 8 አድርሷል። በአንፃሩ የቀድሞው የማን/ ዩናይትድ ወጣት 38 ግቦችን አስቆጥሮ የፒቺቺ ኮከብ ግብ ማስቆጠሩን አረጋግጧል። የአልሜሪያ ጨዋታው ግን ለልጁም ሆነ ለክለቡ ታሪክ የሚሠራበት ቀን ነበር። ሪያል ማድሪድ ካሸነፈ 100 ነጥቦችን በአንድ የውድድር ዓመት የሰበሰበ ብቸኛው የላሊ ክለብ ይሆናል። በአንፃሩ ሮናልዶ ግብ ማስቆጠር ከቻለ ደግሞ ከፍተኛ ኮከብ ግብ አስቆጣሪነቱን በሪከርድ መዝገብ ላይ ማስቀመጥ ይችላል። ጨዋታው ከተጀመረ ደቂቃዎች ሄዱ። ሪያል ማድሪድ አልሜሪያን ሲያሸንፍ ኮከባቸው ሮናልዶም ሁለት ግቦችን አስቆጥሮ በ40 ግቦች የውድድር ዘመኑ ከፍተኛ ግብ አግቢ ሆኖ አጠናቀቀ።
ነሐሴ 17 /2011
የስፓኒሽ ሱፐር ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ የመጀመሪያ ዙር በካምፕኑ ምሽት የምንጊዜም ተቀናቀኞቹ ባርሴሎና ከሪያል ማድሪድ ከዕረፍት በፊት ዴቪድ ቪያ ባስቆጠረው ግብ ባርሴሎና መምሪት ጀመረ። ከደቂቃዎች በኋላ ግን ከራኡል ጎንዛሌዝ ክለቡን መልቀቅ በኋላ «7 ቁጥር» ማሊያ የለበሰው የፖርቺጋል ብሔራዊ ቡድን አምበል ማሪጌዎቹን አቻ አደረገ። ይህች ግብ በሪያል ማድሪድ ማሊያ ያስቆጠራቸውን ጠቅላላ ግቦች ድምር 100 ማድረስ የቻለች ነበረች። መቶኛ ግቡን በካምፕኑ።
የማንቸስተር ዩናይትድን 1000ኛ የፕሪሚየር ሊግ ግብ በሚድልስ ቦሮ መረብ ላይ ማሳረፍ የቻለው የነጭ ለባሾች አዲሱ 7 ቁጥር የራሱን መቶኛ ግብ ኑ ካምፕ ላይ ማስቆጠሩን አንስተን ነበር ያለፈውን ጽሑፋችንን የዘጋነው። ቀጣዩም እንዲህ ይነበባል። የዘመን አቆጣጠሩ ዛሬም በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር መሆኑን ልብ በሉ።
ነሐሴ 27/2001
የስፓኒሽ ሱፐር ካፕ ዋንጫን በአወዛጋቢ ሁኔታ በጆሴፕ ጋርዲዮላ ልጆች የተቀማው ማድሪድ የላሊጋ ውድድሩን የጀመረው በቁጭት ነበር። የቀድሞውን የጋርዲዮላ ምክትል ያሁኑን የባርሴሎና ዋና አሰልጣኝ ቪቶ ቪላኖቫ ጆሮ የቆነጠጡት ፖርቹጋላዊ ምርጥ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኖ ሪያል ዛራጐዛን 6 ለባዶ በሆነ ውጤት በማሸነፍ ከብስጭታቸው ሲገላገሉ በአንፃሩ መልከ መልካሙ የ2008 ኮከብ ተጫዋች 3 ኳሶችን መረብ ውስጥ ማሳረፍ ችሎ ነበር የውድድር ዓመቱን የጀመሩት።
መስከረም 24/2011
ራዮ ቫዮካኖን በሜዳው ያስተናገደው ኃያሉ ሪያል ማድሪድ 6ለ2 የሆነ ጣፋጭ ድል አስመዝግቦ ነበር ተጋባዡን ቡድን የሸኘው። በራዮ ቫዮካኖ መረብ ውስጥ ከተጠቀጠቁት 6 ኳሶች መካከል ሮናልዶ የሦስቱ ድርሻ ነበረው። እነዚህ ሦስት ግቦቹ በክለቡ ያስቆጠራቸው 10ኛ ሀትሪኩ ሆነው ተመዝግበውለታል።
መስከረም 27/2011
እስካሁኗ ሰዓት ድረስ 50 የሻምፒዮንስ ሊግ ግቦችን ለሁለቱ ኃያላን ክለቦች (ማድሪድና ዩናይትድ) ማስቆጠር የቻለው ሮናልዶ በዚሁ ዕለት የሆላንዱ ዋና ከተማ ክለብ አያክስ አምስተርዳም ሪያል ማድሪድን ሲገጥም አስገራሚ ግብ አስቆጥሯል።
ጥቅምት 22/2011
ለተከታታይ ሦስት ጨዋታዎች የግብ መንገድ ጠፍቶበት የሰነበተው ሮናልዶ የሦስቱን ግብ አልባ ጨዋታዎች ካሳ አሥራ አንደኛ የማድሪድ ሀትሪኩን በማላጋ መረብ ላይ አሳረፈ። የማኑኤል ፔሌግሬኒወን ቡድን መረብ ሦስት ጊዜ ሲጐበኘው ማድሪድም በተጨማሪ የከሪም ቤንዜማ ግብ ታግዞ 4 ለዜሮ አሸንፎ ሸኘው።
ህዳር 6/2011
አሳሱና እና የስፔኑ ሻምፒዮን የነበራቸውን የስፔን ላሊጋ ጨዋታ ግብ አዳኙ ሮናልዶ በኤል ጐዳር ስታዲየም (የኦሳሱና ስታዲየም) የታደሙትን የኦሳሱና ደጋፊዎች አንገት ያስደፉ 3 ኳሶችን መረብ ውስጥ ጨምሮ ሃትሪክ ሰርቶ ወጣ። ይህ ውጤት በኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ምክንያት ለሁለት ሳምንት ለሚቋረጠው የስፔን ላሊጋ ሪያል ማድሪድ መሪነቱን አስጠብቆ እንዲቆይ የሮናልዶ 12ኛ ሃትሪክ ወሳኝ ነበር።
ህዳር 26/2011
በማድሪድ ደርቢ (ኤል ደርቢ ማድሪዲኞ) የዲያጐ ሲሞኒውን አትሌቲክ ማድሪድ ሲገጥሙ እና 4 ለ 1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ክርስቲያኖ ሁለት ኳሶችን በፍፁም ቅጣት ምት ከታይባውት ኮርቶስ ጀርባ ከተወጠረው መረብ ውስጥ አሳርፎ ምርጥ የፍፁም ቅጣት ምት ባለሙያ መሆኑን አሳየ።
የካቲት 12/2012
ማሬንጌዎቹ በሜዳቸው እንቁራሪቶቹን (ሌቫንቴን) አስተናግደው 4 ለ 1 በሆነ ልዩነት ሲረቱ የሮናልዶ ሦስት ኳሶች በረኛውን አልፈው መረብ ውስጥ አርፈዋል። በዚህም ተጫዋቹ 14ኛ የክለቡን ሃትሪኩን ሰርቶ ሲወጣ ክለቡ ደግሞ የምንጊዜም ተቀናቃኙን በ10 ነጥቦች ርቆ የደረጃ መሪነቱን እንዲቆናጠጥበት ረድተዋል።
መጋቢት 24/2012
ሪያል ማድሪድ በሳንቲያጎ በርናባው የቫስክ ግዛቱን ክለብ (ሪያል ሶሴዳድ አስተናግዶ የግብ ናዳ ሲያወርድበት የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አንበልም እንደለመደው ኳስና መረብን ሁለት ጊዜ አገናኝቷል። እነዚህ ሁለት ግቦች ደግሞ ለስፔኑ ኃያል ክለብ ያስቆጠራቸውን የላሊጋ ግቦች ድምር 100 አድርሰውለታል። የስፔን ላሊጋን በተቀላቀለ አጭር ጊዜ ውስጥ 100 ጊዜ ካሶችን ለግብ አብቅቶ የምንግዜውም ሁለተኛው ፈጣኑ ተጫዋች ሆኗል።
ነሐሴ 23/2ዐ12
የአውሮፓ ክለቦች ውድድር ቢቋረጥም ጐረቤታሞቹ ዩክሬንና ፖላንድ በጣምራ ያዘጋጁት የአውሮፓ ሀገሮች ውድድር እየተካሄደ ነበር። በአውሮፓ ዋንጫው ከአንድሬስ ኢንየሽታ ቀጥሎ ሁለተኛው ኮከብ ተጫዋች የነበረው ክርስቲያኖ ከማን ሲቲ ባለቤት እና ሊቀመንበር ሽክ መንሱር የቀረበለትን የ200 ሚሊዮን ፓውንድ ዝውውር ችላ ብሎ ወደ ሳንቲያጐ በርናባው ክለብ ተጓዘ። ከላይ በጠቀስኩት ዕለት ታላቁ የኤል ክላሲኮ ደርቢ ተካሂዷል። ውጤቱ ደግሞ ሁለቱም ግዙፍ ክለቦች 4 እኩል ናቸው። በዚህ ጨዋታ ሮናልዶ አንድ ግብ ያስቆጠረ ሲሆን ፣ይህ ግብም በአራት የኑ ካምፕ ጨዋታዎቹ ያስቆጠረው አራተኛ ግብ ሆኖ ተመዝግቦለታል።
መስከረም 2/2012
በፖርቹጋል፣ እንግሊዝና ስፔን ቆይታው በድምሩ ያስቆጠራቸውን ግቦች ብዛት ወደ 200 ከፍ ያደረገለትን ግብ በግራናዳ መረብ ላይ አሳረፈ። በዚህ ጨዋታ ተጐድቶ እስከ ወጣበት ድረስ ተጨማሪ አንድ ግብ ያስቆጠረ ሲሆን ፥ ግቧን ካስቆጠረ በኋላ ያሳየው የመከፋት ስሜት በርካታ የስፖርቱ አፍቃሪያንን አነጋግሯል። በሪያል ማድሪድ ተገቢውን ጥበቃ እና እንክብካቤ እየተደረገልኝ አይደለም ያለው የ2008ቱ ኮከብ ተጫዋች በእዚህ ዕለት ነበር የውድድር ዓመቱን ሁለት ግቦች ያስቆጠረና ያስከፈተው።
ጥቅምት 4/2012
በቀዝቃዛማው የጥቅምት ወር መግቢያ ደግሞ ጠንካራው ፖርቹጋላዊ በሻምፒየንስ ሊጉ የመጀመሪያ ሃትሪኩን ሥራ። ሪያል ማድሪድ በተደለደለበት የሞት ምድብ ውስጥ ከሚገኙት ቡድኖች አንዱ የሆነው የሆላንዱ አያክስ አምስተርዳም ነበር ለሮናልዶ 3 ግቦች እጁን የሰጠው። በእስካሁኑ የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎው 50 ጊዜ የተቃራኒ ቡድኖችን መረብ የጎበኘው 7 ቁጥር የመጀመሪያውን ሃትሪክ መስራት የቻለው በሆላንዶቹ ሻምፒዮን ላይ ነበር።
ጥቅምት 7/2012
በ2012/13 የስፔን ፕሪሜራ ሊጋ ውድድር ሁለቱን ዝሆኖች በመጀመሪያዎቹ ሳምንት ያገናኘበት ምሽት ነበር። 4 ግቦች በሁለት ተጫዋቾች በተቆጠሩ በት ፍልሚያ ባለሜዳዎቹ ብሎግራናዎቹን አርጀንቲናዊ ጥበበኛ ሲያስቆ ጥርላቸው ማሬንጌዎቹ ደግሞ በፖርቹጋላዊ ሁለት ግቦች ከባርሴሎና ሜዳ አንድ ነጥብ ሸምተው ሊመለሱ ችለዋል። እነዚህ ሁለት ጎሎች የቀድሞውን የስፓርቲንግ ሊዝበን ተጫዋች ብቸኛው የሪያል ማድሪድን ማሊያ ለብሶ ባርሴሎና መረብ ላይ ብዙ ግብ ያገባ ተጫዋች አድርጎታል።
(ይቀጥላል)

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

አበበ ፈለቀ በዲሲና በአካባቢዋና በሌሎችም የአሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸውና ህጋዊ ሂደት ውስጥ ያሉት ጭምር በሰፊው እየተወሰደ ባለው የስደተኞች አፈሳና መመለስ (Deportation) ጋ ተያይዞ በቂ መረጃ አለማግኘት፣ ጭንቀትና ስጋት

አሜሪካ ለሚኖሩ፡ የስደተኞች አፈሳና መመለስን በተመለከተ ማወቅ ያለብን ነጥቦች

January 29, 2025
ይነጋል በላቸው “አማራ በድርድር የሚፈታ ችግር አልገጠመውም” በሚል ርዕስ በፈረንጆቹ አቆጣጠር Sept. 16, 2023 የሚከተለውን መጣጥፍ ጽፌ እንቅልፍ ሳይበግራቸው፣ ድካም ወፃማ ሳይፈታቸው ለሀገራቸው ትንሣኤ ሌት ከቀን ለሚታገሉ ድረ ገፆች በመላክ ለንባብ በቅቷል፡፡

የአማራና የኦሮሙማ ድርድር – በሣቅ አትግደሉን!

Go toTop