“መሬትህን ሊቀሙ ነው የመጡት” በሚል የቤንሻንጉል ነዋሪ ተመላሽ አማራዎችን እንዲያገል በመንግስት ተላላኪዎች እየተሰበከ ነው

ወደ ቤንሻንጉል የተመለሱት የአማራ ተወላጅ ተፈናቃዮች እጅግ በከፋ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን የመንግስት ሃይሎች የአካባቢው ነዋሪዎች አማሮቹን እንዲያገሉ በተዘዋዋሪ መንገድ እየተወተ እንደሚገኝ ፍኖተነፃነት ጋዜጣ ከአዲስ አበባ ዘገበ።
እንደ ጋዜጣው ዘገባ ከሆነ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቅለው በፍኖተሰላምና በተለያዩ አካባቢዎች ተበትነው ከቆዩ በኋላ ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው እንዲመለሱ የተደረጉት የአማራ ተወላጅ ተፈናቃዮች እስካሁን እርሻ አለመጀመራቸውን አስታውቀዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ እንዳስታወቁት ወደ ቀድሞው ቦታቸው እንደሚመለሱ ተነግሯቸው ቢመጡም፣ ስፍራው ሲደርሱ የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ለህብረተሰቡ አስቀድመው የተከራየነውን መሬት እንዳያስረክቡን በመቀስቀሳቸው ሊቀበሏቸው እንዳልፈለጉ አስረድተዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት አካላት “ተመልሰው የመጡት መሬታችሁን ሊቀሟችሁ ነው እንዳታቀርቧቸው” ተብለዋል የሚሉት ተፈናቃዮቹ “እርሻችንን እንዳትነኩ ወደ መሬታችንም እንዳትደርሱ” መባላቸውን ለጋዜጣው ተናግረዋል።
“በዚሁ ምክንያት እጅግ ለከፋ ችግር እንደተጋለጡ የሚናገሩት ተፈናቃዮቹ መንግስት በአካባቢው በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈፃመውን ግፍ እንዲያስቆም ተማፅነዋል፡፡” ያለው ዘገባው አክለውም “እኛ ያለ ባለመሬቱና ያለ መንግስት ፈቃድ የሰው መሬት አንነካም፤ ይህንን የአካባቢው የመንግስት አካላት ለህብረተሰቡ ሊያስረዱልን ይገባል፡፡ ሰርተን ለመኖ ተቸግረናል” ብለዋል ሲል ዘገባውን አጠናቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአዲስ አበባ ከተማ - የከተማዋን ነዋሪ ስነ-ልቦና ፣ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ማዕከልነትን ታሳቢ ያደረገ የፖሊስ ኃይል ያስፈልጋታል

1 Comment

Comments are closed.

Share