ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY
ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)
ይድረስ ለጎንደር፣ ለጎጃም፣ ለወሎና ሸዋ ፋኖ ታጋዮች የአንድ አማራ ፋኖ እዝ ምሥረታ አሁን!!! ይድረስ ለአርበኛ አሰግድና ለሻለቃ መከታው የአማራ ህዝብ ነፍሶች በእጃችሁ መዳፍ ላይ ናትና ህልውናችንን አስከብሩ!!! አንድ የአማራ ፋኖ እዝ ምሥረታ ለህልውና፣ ‹‹አማራ በሸዋ መከረ፣ አገር አጠነከረ!!!››
‹‹አማራ በሸዋ መከረ፣ አገር አጠነከረ!!!›› ማለት ያኔ ነው፡፡ የኦህዴድ ብልፅግና የስድስትና አራት ወራት የአስቸኮይ ጊዜ አዋጅ የአማራ ህዝብ በኮማንድ ፖስቱ ወታደራዊ ኦፕሬሽን በግፍ ተጨፍጭፎል፣ በድሮውን ተደብድቦል፣ ከአራት ሽህ በላይ ሴቶች ተደፍረዋል፣ እህል ተቃጥሎል፣ ከብቶች ተነድተዋል፣ ህዝቡ የትራንስፖርት አገልገሎት ተነፍጎል፣ አማራ ወደ አዲስአበባ እንዳይገባና እንዳይወጣ አፓርታይዳዊ ፖሊሲ ተነድፎል፣ ከመቶ በላይ ጤና ጣቢያዎች ወድመዋል ህክምናና መድኃኒት የለም፣ ነዳጅ የለም፣ በአማራ ክልል 3.6 (ሦሰት ነጥብ ስድስት)ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተገለዋል 3000 ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፣ የቴሌኮሙኒኬሽን ኢንተርኔት አገልግሎት የለም፣ የመብራትና ውኃ አገልግሎት የለም፣ የባንክ አገልግሎት ተቆርጦል፣ ለገበሬው ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ አልቀረበም፣ የኑሮ ውድነት ሰማይ ደርሶል፣ ኮማንድ ፖስቱ ዙሪያ ገባውን አጥሮ ይዞ፣ ህብረተሰቡን አንቆል፡፡ የጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎና ሸዋ አንድ የአማራ ፋኖ እዝ እስካልተመሠረተ የህዝቡን ስቃይ ይቀጥላል፡፡ የአማራ ፋኖ እዝ መሥርቶ፣ በኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት አዋቅሮ፣ የኮነሬል አብይ ኦህዴድ ብልጽግና መንግሥትን ወንጀለኞች ለፍርድ ማቅረብ ቀጣይ ሥራ ይሆናል፡፡
ህወሓት/ኢህአዴግ (1991 እስከ 2018እኤአ) አንባገነናዊ የሃያ ሰባት አመታት አገዛዝ ዘመን እንዲሁም የኦህዴድ ብልጽግና (2018 እስከ 2024እኤአ) አንባገነናዊ ስድስት አመታት አገዛዝ ዘመን የኢትዮጵያ ስታስቲክስ ኤጀንሲ (Ethiopia Statistics Agency) የህዝብ ቤቶች ቆጠራ ጥናት መሠረት በ1984 እኤአ የኦሮሞና አማራ ህዝብ ቁጥርና ልዩነት 332,414 ወይም (0.8%) የነበረ፣ በ1994 እኤአ የኦሮሞና አማራ ህዝብ ቁጥርና ልዩነት 4,898,228 ወይም (9%) ያደገ ሲሆን፣ በ2007እኤአ የኦሮሞና አማራ ህዝብ ቁጥርና ልዩነት 9,944,415 ወይም (13.4%) እየጨመረ ሲሄድ፣ በ2024 እኤአ የኦሮሞና አማራ ህዝብ ቁጥርና ልዩነት 13,870,384 ወይም (11.7%) እየተመነደገ ለመሄዱ ህወሓት ዘመን የአማራ ክልል ሴቶች እንዳይወልዱ የሚያደርግ መርፊ ይወጎቸው እንደነበርና በተለያየ ጊዜ በበደኖ፣ በወለጋ፣ በወልቃይት፣ በራያ ወዘተ የተፈፀመ የዘር ጭፍጨፋ የአማራ ህዝብ ቁጥር ለመቀነሱና በፓርላማ የሁለት ሚሊዮን አማራዎች መጥፋት አነጋጋሪ የነበረበት ጊዜ ይታወሳል፡፡ በኦህዴድ ብልጽግና የማያባራ የጦርነት ዘመን በኮነሬል አብይ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ በሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንትና አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እየተናበቡ የአማራ ህዝብን በመጨፍጨፍና በሚሊዮኖች በማፈናቀል በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት በመፈጸም፣ የጦር ወንጀል በመፈጸም፣ እንዲሁም የስብዓዊ መብቶች ጥሰት በአማራ ህዝብ ላይ በማድረግ ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል መፈፀማቸው ይታወቃል፡፡ ፋኖ የአማራ ህዝብን የህልውና ትግል በማቀጣጠል እልፍ አእላፍ ታጋዬችን በማፍራትና እነዚህን የህዝብ ጠላቶች ከአማራ ግዛት ነቅሎ በመጣል በህይወት የመኖር ትግሉን በመቀጠል ወንጀለኞቹን ለዓለም አቀፍ ፍርድ ለማቅረብ በመታገል ላይ ይገኛል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ (1991 እስከ 2018እኤአ) እና የኦህዴድ ብልጽግና (2018 እስከ 2024እኤአ) አንባገነናዊ አገዛዝ በአማራው ህዝብ ላይ ለፈፀሙት የዘር ፍጅት፣ የጦር ወንጀል፣ እንዲሁም የስብዓዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂ ወንጀለኞችን የአገሪቱን ሥነ-ህዝብ (ዲሞግራፊ) ለመቀየር፣ በተለይ የአማራን ህዝብ ቁጥር በመቀነስ በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳይ ያለውን ድርሻ ለማውረድ የተጀመረው በአስራዘጠኝ መቶ ስልሳዎቹ በሻብያ፣ ወያኔና ኦነግ አመራሮች የፖለቲካ ሴራ ነበር፡፡ በዚህ የፖለቲካ ሴራ የአማራ ህዝብን ቁጥር በመቀነስ አንደኛ የሥነ-ህዝብ ለውጥ በማድረግ የአማራውን ቁጥር በመቀነስ ከፖለቲካ ተሳትፎ ማሳነስ በፓርላማ እንደራሴነት ቁጥሩን መቀነስ፣ ሥልጣኑን ማውረድ ‹‹ለአንድ ሰው አንድ ድምጽ›› መርህ መሠረት የአማራውን ቀጥር ከቀነስክ፣ የኦሮሞው ቁጥር እንዲጨምር በማድረግ የወያኔና ኦነግ የግማሽምዕተ-አመት የፖለቲካ ሴራ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ሁለተኛ የሃገሪቱ አመታዊ በጀት ቀመር የሚሰላው ከህዝብ ቁጥር አንጻር በመሆኑ የአማራ ህዝብን አመታዊ በጀት ድርሻ ከአመት አመት መቀነስ ዋና ምክንያት የአማራን ህዝብ ቁጥር በአስራ አራት ሚሊዮን እንዲቀንስ በማድረግ የተፈፀመ የዘር ፍጅት ወንጀል የህወሓትና ኦነግ አመራሮች ለፍርድ የማቅረብ የአማራ ፋኖ እዝ የህብረት ሥራና የትግል ጥሪ ነው እንላለን፡፡ አንድ የአማራ ፋኖ እዝ ምሥረታ፣ ለኦህዴድ ብልጽግና ጋቸነ ሲርና፣ ኮሬ ነጌኛ፣ የዘር ጭፍጨፋ መከታ በመሆን ከወዲሁ አስፈላውን ዝግጅት ማድረግ ይገባል እንላለን፡፡ የወለጋ ተፈናቃዬች በደብረብርሃን ከተማ ተጠልለው ከሚገኙበት መኖሪያ በግድ ዳግም ወደ ታረዱበት ሥፍራ በጉልበት ተጭነው ዳግም ለእርድ መቅረባቸው ዋና ተጠያቂ ብአዴን ብልፅግና ሲሆን ፋኖም በገለልተኛነት ሊከላከልላቸው አለመቻሉ ያስጠይቀዋል፡፡ የአማራ ወለጋ ተፈናቃዬች ላይ የሚፈጸመውን ኢስብዓዊ ድርጊት መከታና አሌንታ መሆን ያለበት የሸዋ ፋኖ ነው እንላለን፡፡
1984 እኤአ የህዝብ ቁጥር መሠረት የኦሮሞና አማራ ህዝብ ቁጥርና ልዩነት
- ኦሮሞ 29.1%
- አማራ 28.3%
- ልዩነት 332,414 ወይም (0.8%)
1994 እኤአ የህዝብ ቁጥር መሠረት የኦሮሞና አማራ ህዝብ ቁጥርና ልዩነት
- ኦሮሞ 35%
- አማራ 25.9%
- ልዩነት 4,898,228 ወይም (9%)
2007 እኤአ የህዝብ ቁጥር መሠረት የኦሮሞና አማራ ህዝብ ቁጥርና ልዩነት
- ኦሮሞ 36.7%
- አማራ 23.3%
- ልዩነት 9,944,415 ወይም (13.4%)
2024 እኤአ የህዝብ ቁጥር መሠረት የኦሮሞና አማራ ህዝብ ቁጥርና ልዩነት
- ኦሮሞ 34%
- አማራ 22.3%
ልዩነት 13,870,384 ወይም (11.7%) ……………………….……..(1) [ Episode-1 ] The Mystery of Millions of Missing Amharas: Where Have They Gone? – YouTube ይህን በኢትዮ ክሮኒክልስ የተዘጋጀ ዩቲዩቡ በማየት የሚሊዮኖች አማራ መጥፋት እንቆቅልሽ ምስጢር ይገለጽላችኃል፡፡
‹‹በአለማችን የከተማ ልማት አስተሳሰብና ማእቀፍ/ፓራዳም/ፍሬምወርክ፣ዘላቂነት፣ጽኑነት፣አካታችት ፣ ፍታዊነት/Environmental sustainability/Climate Resilience/Socially inclusive and just በሚሉ ዋና ዋና ማገሮች የሚመራ እየሆነ ነው፣ ይህም በበርካታ ሀገሮች ገዢ አስተሳሰብና አሰራር እየሆነ ይገኛል ። በ2050 የአለማችን ህዝብ 70% የከተማ ነዎሪዎች እንደሚሆኑ የበርካታ ጥናቶች ትንበያ ያሳያል። ስለሆነውም ልማት የከተማውን ኢንፍራስታክቸሮች ማስፋፋት ብቻ ሳይሆን ጽኑ፣ ዘላቂ/እንዲሆኑ ፣ ዜጎች ፣ የከተማ ነዋሪዎች ማህበራዊና አካታችነት፣ ፍትሃዊነት፣ኢኮኖሚ ጽናትና ዘላቂነት/ሶሻል ኢኮኖሚክ ስስተኔብሊቲ/ሬሲሊያንስ እንዲኖራቸው ማድረግን ታሳቢ ያደረገ የልማት አስተሳሰብ ማእቀፍ/ፍሬምወርክ ነው። በመሰረቱ ልማት መዳረሻውም ፣ መነሻውም ሰው ነው። የልማት ግብ የሰዎች፣ የማህበረቦች፣ የዚጎች ልማት ነው፣ የኮንክሪት ጫካ ወይንም ኮንክሪት ጃንግል ግንባታ አይደለም። አብይ አህመድ እንደሚያደርግው የብልጭልጭ ፎቆችና ግንባታዎች መደርደር አይደለም። አማራታ ሰን፣ ማርታ ናስባም ፣ ሌሎችም ታላላቅ የኢኮኖሚ ልማት ፈልሳፎችና ሃሳቢዎች እንዳስቀመጡት፣ ልማት መድረሻውም ፣ መነሻውም የሰው ልጅ ነው። የዜጎችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ስነ ልቦናዊ አቅም ማጠናከር ፣ ማዳበር ነው። በእርግጥም ለህዝብ ለዜጎች የሚጨነቅና ፣ በእኩልነትም የምያይ መንግስት ካለ አንድ ሃገር ውስጥ፣ ዋነኛ የመንግስት ተግባር ይህን መተግበር ነው። ሰው ተኮር፣ ዜጋ ተኮር ልማት/human centered development and enhancement of human capabilities. የእነ እብይ አህመድና የአደነች አቤቤ አገዛዝ ከዚህ በተቃራኒው፣ ማፈናቀል፣ ማውደም፣ ዜጎችን ለማህበራዊ ምስቅልቅ፣ ትርምስ፣ መከራና እንግልት መዳረግ ዋናው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ የአዲስ አባባ ህዝብ የሚገኝባቸው አስከፊ ገጽታዎች ሆነዋል። ለልማት ሳይሆን ለፓለቲካ አላማ የሚፈጸም፣ ግፍና በደል። የጥቅም አጋሮቻቸውን በብዙሃን ኪሳራ ለማደለብ የሚፈጸም በደል፣ ኢፍትሃዊነት፣ ጋጠ ወጥነት፣ እብሪትና ትብኢት!!›› …………………….(2)
‹‹የመጀመሪያው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተደራጀውና በብዛት እየተደራጀ ያለው በኦሮሚኛ መጠሪያ ስሙ ጋቸነ ሲርና(Gaachana Sirnaa) ማለትም አብዮት ጠባቂ(ስርአቱን ጠባቂ) ማለት ሲሆን በክልሉ ባለው ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ችግር ምክንያት መንግስት ስልጣኔን ይቀሙኛል የሚላቸውን ሃይላት ይከላከሉልኛል ብሎ ያደራጀው ነው፡፡ በተለይም በክልሉ የተደራጅቶ የሚንቀሳንቀሰው የኦሮሞ ነጻነት ግንባርና ሠራዊት በመንግስት እምነት ከፍተኛ ህዝባዊ ተቀባይነትና ድጋፍ ስላለው እሱን ለመከላከልና በህዝቡ መካከል መከፋፈል ተፈጥሮ እርስ በእርስ እንዲጠራጠርና እንዲጋጭላቸውን የስልጣን ዘመናቸውን ለማራዘምና ለማደላደል ይረዳናል ብለው በማሰብና ሀገሪቷ ላይ ባለው የብሔር ፖለቲካ ምክንያት ከሌሎች ብሔሮች ሊቃጣ የሚችለው ጥቃት ለማስቀረት (መከልከል ፖሊሲ)የታፍራ ፖሊሲ (deterrence policy) ለመተግበር ያሰበ ነው፡፡››
‹‹ብልፅግና በመላው ኦሮሚያ የጋቸነ ስርና እና የመንግሥት ሠራተኛውን ጨምሮ በሰፊው እያሰለጠነ ይገኛሉ፡ እነዚህ ሀይላት ብልጽግና የራሱን ጊዜያዊ ሥርዓት ለማስጠበቅ የሚጠቀምባቸዉ ከማህበረሰቡ የተወጣጡ ወጣቶችና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ናቸዉ:: የብልፅግና ውድቀት ግልፅ ከመሆኑም በላይ እየሄደበት ያለው ቁልቁለት አወዳደቁን ክፉ ያደርገዋል፡፡ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትን(መንግስት ሸኔ በማለት የሚጠራው) ፍለጋ በሚል ህዝቡን መግደል፣ ማሠር፣ ማሠቃየት ሳያንስ ጫካ ለጫካ ሲያዞርና ሲያንከራትት የሚውለው እነዚህን የስርዓቱ ዘብ ጠባቂዎች ነው፡፡››
‹‹ብዛት ያላቸው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ደጋፊዎችና አባላት እንደሚያስረዱት መንግስት የነጻነት ሠራዊቱን ስም ለማጠልሸትና በህዝብ እንዲጠላ ለማድረግ የነጻነት ሠራዊቱን ስም ለውጥ በማድረግ ሲሆን በዚህም አዲስ ስም በማውጣት፤ ይህውም “ሸኔ” በማለት ከህዝቡ እንዲነጠል በተለያዩ ጊዜቶችና ቦታዎች ላይ በንጹሃን ላይ ጥቃት በመፈጸም የነፃነት ሠራዊቱ እንደፈጸመው በሚዲያዎቹ በማስነገር የነፃነት ሠራዊቱ በህዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነትና እንዲጠላ ለማድረግ ታስቦ ነው ይላሉ፡፡ አንድ የድርጅቱ ደጋፊ እንዳሉትም፡- ››
“እኛ ለኦሮሞና በኦሮምያ ዉስጥ ለሚኖሩት ጭቁን ህዝቦች ነፃነት እንጂ የሚንታገለዉ በኦሮምያ ለዘመናት በሰላም የኖሩትን ንፁሃን ለመግደል አይደለም። እንሱ ቢሆንማ ኦነግ በወለጋ ዉስጥ ላለፉት 40 አመታት ሲንቀሳቀስ ነበር። ለምን ታዲያ ያኔ የዚህ አይነት ተመሳሳይ ድርጊት አልፈፀመም። ይህ መንግስት እኛን ለማጥላላትና አሸባሪ ለማሰኘት ባለፉት አመታት በወሎና በከረዩ አባገዳዎች ላይ የተፈፀሙትን የጅምላ ጭፍጨፋዎች ጨምሮ በእኛ እንዳመኻኘ፤ ሁሉንም አሁንም ለራሱ ርካሽ ፖለትካ ሲባል እራሱ በኦነግ ስም አሰልጥኖ ያሰማራቸዉ “ጋቸነ ስርና” ወይም አ ብዮት ጠባቂ የተባሉ ነፍሰ ጓደዮች የፈፀሙት ወንጀል ነዉ” በማለት ያስረዳሉ፡ በርግጥ እንዳሉት መንግስት ኮሬ ነጌኛ በሚል ያቋቋመው አፋኝና ገዳይ ቡድን የከረኞ አባገዳዎችንና ሌሎች የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የተወቀሰበትን ግድያዎች እንደፈጸመ ሮይተር በምርመራ ሪፖርቱ አስነብቧል፡፡ በአጠቃላይ ጋቸነ ስርና የስርዓቱ ጠባቂ ሆኖ መንግስት ድንገት ወታደሩ ቢከዳው ወይም ቢዳከምበት ከእነዚህ ሃይላት መሳሪያ በማስታጠቅ(አንዳንዶቹ ታጥቀዋል) መንግስት ጠላቴ በሚለው ሃይል ላይ ጥቃት እንዲፈጽሙ በማድረግ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ እንድንገባ የሚያደርግ ነው፡፡ በሌላ በኩል ልክ እንደ ሩዋንዳው ኢንተርሃሙይ የዘር ጭፍጨፋ እንዲያደርግ ቢታዘዝ ሙሉ አቅም ያለው ጥፋት ሃይል ነው፡፡›› …………………(3)
ምንጭ
[ Episode-1 ] The Mystery of Millions of Missing Amharas: Where Have They Gone? – YouTube
በአብይ አህመድ ትእዛዝ የሚፈርሱ የአዲስ አበባ ቅርሶች ወይንስ “ማንም ያቦካው ጭቃ” ? (borkena.com)