*** የአማራ ሕዝብ የምንግዜም የጥቃት ምንጭ የሆነው ብአዴን የአማራ ሕዝብ ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለባቸውን፣ በደምና በአጥንቱ ነጻ ያወጣቸውን ታሪካዊ ርስቶቹን ዳግም አሳልፎ ለጠላት ወያኔ ማስረከቡን ቀጥሏል።
የዐቢይ አሕመድ የትሮይ ፈረስ የሆነው ተመስገን ጥሩነህ፤ ምስለኔው አረጋ ከበደ፤ አድርባዩ አብዱ ሁሴን፤ ካድሪው ይርጋ ሲሳይ የአማራ ታሪካዊ ርስቶችን ዳግም በመሸጥ ዋናዎቹ ባንዳዎች ናቸው። አብዱ ሁሴን የተባለው ሰው የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆኖ፣ ዋና ስራው የአማራ ሕዝብ ማንነትና ወሰን ጥያቄ ይዞ ታግሎ ነፃ ያወጣቸውን ራያ፣ ኮረም፣ አበርገሌ፣ ጠለምት፣ ወልቃይት ጠገዴን ለጠላት አንድ በአንድ አሳልፎ የሚሰጠውን ዐቢይ ኮሚቴ መምራት ነው፤ ሪፖርት የሚያቀርበውም ለተመስገን ጥሩነህ ነው።
ተመስገን ለዐቢይ እንዲህ ባለ የባንዳነት ቅብብል የአማራ ታሪካዊ ርስቶች አንድ ባንድ ለጠላት ተላልፈው እየተሰጡ ነው። የዐማራ ሕዝብ ታሪካዊ ርስቶችን በድጋሚ ከሸጡት ዋናዎቹ ባንዳዎች እነዚህ ሰዎች ከፊት መስመር ይጠቀሳሉ። ሚያዚያ 5/2016 ራያ እና ኮረምን ሰኔ 22/2016 ዓ.ም ጠለምትን ዳግም ለጠላት አሳልፈው ሰጥተዋል። ከትላንት ምሽት ጀምሮ ከሦስቱ የጠለምት ከተሞች በአስር ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ ተፈናቅሎ አዳርቃይ ከተማ ገብቷል። ዛሬም በርካታ ተፈናቃይ እየገባ ነው። ምክንያቱም ሜካናይዝድ የሆነው አርሚ 42 እና አርሚ 11 በርካታ ኃይላቸውን ይዘው ወደአማራ ታሪካዊ ግዛት ጠለምት እንዲገቡ በአረጋ ከበደ የልዑካን ቡድን መሪነት፤ በብልጽግና ሰራዊት (መከላከያ እና ፌደራል ፖሊስ) አጃቢነት ወደ ጠለምት ገብተው ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ እንዲያቋቁሙ ስለተስማሙ በዚህ ስጋት የገባው ሕዝብ ከሦስቱም የጠለምት ወረዳዎች ተፈናቅሎ ወደ አድርቃይ፣ ዛሪማና ደባርቅ መሰደድ ጀምሯል። ወያኔ ከሚያዚያ 5/2016 ጀምሮ፣ በራያ ዓለማጣ ከተማና ዋጃ ጥሙጋ ራያ ቆቦ ቀበሌዎች (እንደ ዋልካ መንደር ባሉት ትምህርት ቤቶችና ቀበሌዎች 14 የታጣቂ ማዘዣ ጣቢያዎች አቋቁሟል። በእነዚህ አካባቢዎች 52,000 የአማራ ሕዝብ ከመኖሪያ ቀዬው ተፈናቅሏል።( ይህ መረጃ የተባበሩት መንግሥታት ያወጣው ነው።)
ምስለኔውዎቹ እነ አረጋ ከበደ ደግሞ የአማራ ሕዝብን አገር አልባ ለማድረግ ለኦሕዴድ እና ወያኔ ስትራቴጂያዊ ጥቅም እየሰሩ ነው። የኦህዴድ ብልጽግና የኦሮሞ ኢምፓየር ግንባታ፤ የወያኔ ጉዞ ደግሞ “የታላቋ ትግራይ ምስረታ ጊዜው አሁን ነው” በሚል ተከዜን ተሻግሮ ወሳኙን ኮሪደር ዳግም ለመውረር በእነ በነ ተመስገን ጥሩነህ ታሪካዊ ስህተት መንገዱ እየተጠረገለት ነው።
ጠላት ብአዴን የኦሕዴድ የጫማ ሶል ሆኖ ከማገልገሉ በላይ ምንም ስለማያውቀው፤ ዓላማና ግቡን ስላልተረዳው “የፕሪቶሪያ ስምምነት ትግበራ” እያለ ይደሰኩራል። የፕሪቶሪያ ስምምነት ወያኔን የማዳን፤ አማራን አገር አልባ የማድረግ የዐቢይ አሕመድ የጥፋት ፕሮጀክት ነው። ይህን የጥፋት ፕሮጀክት ሁለቱም ታሪካዊ ጠላቶች በብአዴን መንገድ ጠራጊነት ወደግባቸው እየሄዱበት ነው።
የፕሪቶሪያ ስምምነት የተባለው ቁማር፦ በናይሮቢ፣ ቀጥሎ በሃላላ ኬላ፣ ከዛም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል፣ በመጨረሻም መቀሌ ላይ የቁማሩ ካርዶች እየተመዘዙ መጫዎቻ ሆነዋል። በአማራ ሕዝብ ላይ ሸፍጥ ተሰርቷል።
አማራን አገር አልባ የማድረግ የጥፋት ፕሮጀክቱ በዚህ መልኩ ቀጥሎ ጠላት ወያኔ በዛሬው ዕለት ሦስቱን የጠለምት ወረዳዎች ተረክቧል። የአማራ ሕዝብ እነዚህን የባንዳ ቁንጮዎች በልቡ ይመዝግብ፤ ብአዴን በአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ ፋኖ መደምሰሱ አይቀሬ ነው። ያኔ እነዚህ ባንዳዎች ዋጋቸውን ያገኛሉ!! በአይበገሬው ፋኖ፦ የአማራ መሬት ጠላቶቻችንን አቅልጦ የሚያሰምጥ እሳተ-ጎመራ ሆኖ ይቀጥላል… አማራ በጠላቶቹ መቃብር ላይ ታሪካዊ ርስቶቹን መልሶ ይቆጣጠራል፤ በዘላቂነትም ያፀናል!! የነገዋ ጀምበር መውጣት ርግጥ የሆነውን ያህል አማራ አሸናፊ መሆኑ አይቀሬ ነው!!
=====
===