ይታወቃል፤ ብልጽግና አቅሙ ሲመናመን በመጨረሻ በድርድር እስትንፋሱን ለማስቀጠል እንደሚፈልግ ይታወቃል፡፡

GEMUAWzX0AAgbJl

እንስማው ሃረጉ

ይሁን እንጅ በድርድር የሚፈታ የአማራ ህዝብ ጥያቄ የለም፡፡ ድርድሩ፤ ሰራዊቱ ሙሉ በሙሉ ፈርሶ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር፤ አሁን ያለው የብልጽግና መንግስት ስርዓት ተጨማሪ እልቂት ሳያስከትል በህግ ታግዶ እንዲፈርስና አዲስ ህገ መንግስት፤አዲስ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ለውጥ እንዲመጣ ከሆነ ምናልባት መስማማት ይቻላል፡፡ ምናልባት ወደፊት ያለውን ጦርነት ለማስቀረት የሽግግር መንግስት መፍትሄ ሊሆን ይችላል፡፡ እንድያም ሆኖ ፋኖ አማራ ክልልን ይዞ የሽግግር መንግስት ለመመስረት የሚያስችለውን ቅድመ ሁኔታ ማመቻቸት ይችላል፡፡

የብልጽግናው አገዛዝ እድሜው አልቋል፡፡ ለአምስት አመት እያሰለጠነ ያከማቸው ጦር አልቆበታል፡፡ በአማራ ክልል ከከተሞች ውጭ አንዲት ጋንታ መሬት የመቆጣጠር አቅሙን አጥቷል፡፡ ከተሞችን ይዞ እንዲቆያ ያስቻለው ፋኖ የከተማ ውግያ እንዲደረግ ስላልፈለገ ጭምር ነው፡፡ የብልጽግናው ኃይል አቅሙ ስለተመናመነ ኃይሉን ከቦታ ቦታ እያንቀሳቀሰ መዋጋት ወሰማይችልበት ደረጃ ደርሷል፡፡ የተተኳሽ አቅርቦቱም አልቆበታል፡፡ በዚህ ላይ ዲፕሎማሲ ቅርቃር ውስጥ ስለገባ አልሸባብን መቋቋም አይችልም፡፡ ሶማሊያ ደፍራ ብትተኩስ ለሳምንት የሚዋጋ የብልጽግና ጦር የለም፡፡

በተቃራኒው የፋኖ ተዋጊ አርሶ አደሩን ጨምሮ አዳዲስ ሠልጣኝ ኃይል በየወረዳው አሰልጥኖ ስለሚያስመርቅ ግዙፍ ሆኖ እየወጣ ነው፡፡ ሰፊው የገጠሩ ግዛት የፋኖ መፈንጫ ነው፡፡ በሰፊው የገጠሩ ወረዳ ፋኖ እንደልቡ ይፈነጭበታል፡፡ ፋኖ አደረጃጀቱን አዘምኖ በአንድ ኮማድ እዝ ቢሆን ኖሮ በዚህ ሰዓት የአማራ ክልል ከተሞች ሙሉ በሙሉ በፋኖ እጅ ይገቡ ነበር፡፡ ፋኖ አንድ ሳላልሆነ ዘግይቷል፡፡ ቢዘገይም ፋኖ በአንድ እዝ ሲሆን በመቅጽፈት ከተሞች ይያያዛሉ፡፡ ያኔ ለአንዴና ለመጨረሻ የአማራ ክልል ከብልጽግናው አገዛዝ ሙሉ በሙሉ ነአ ይሆናል፡፡ ይህን ሃቅ የተረዳው ብልጡ ብልጽግና ውስጥ ለውስጥ የድርስር ጥያቄ እያቀረበ ነው፡፡ የፋኖ መሪዎችን ነጣጥሎ ለድርስር በመጠየቅ ከጀመረ ወራት አልፏል፡፡ የአማራ ህዝባዊ ኃይል ለድርድር እየተጠየቀ እንደሆነ ለህዝብ አሳውቋል፡፡ የአማራ ህዝባዊ ኃይል ከድርድር በፊት እስረኞች እንዲፈቱና የብልጽግናው ኃይል ከክልሉ እንዲወጣ ቅድመ ሁኔታ እንዳስቀመጠ አሳውቋል፡፡ የሚሆነውን ወደፊት እናያለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

188194
Previous Story

በጥምቀት ቀን

188211
Next Story

ሜካናይዝድ ጦር በአዲስአበባ | ቀጥታ ከጎጃም ግምባር! /የጎጃም ዕዝ አመራር ከአማራ ድምፅ ጋር! // በበዓሉ ምድር ከጠላት ጋር ትንቅንቅ!

Go toTop