ያማራ ሕዝብ የሕልውናውን ጦርነት የሚያካሂደው ባማራ ክልል ውስጥ ብቻ እስከሆነ ድረስ፣ በዚህም በዚያም ወገን የሚጨፈጨፈው አማራና አማራ ብቻ ነው። ይህ ደግሞ የኦነጎችና የወያኔወች ዋና ፍላጎት ነው። ከኦነጎችና ከወያኔወች በተጨማሪ ደግሞ በነጭ ላዕልተኞች (white supremacists) የሚዘወሩት ምዕራባውያን መንግሥታት (በተለይም ደግሞ የአንግሊዝና ያሜሪቃ መንግሥታት) ያማራን ሕዝብ እርስ በርስ መተላለቅ በሚከተለው ምክኒያት አጥብቀው መመኘት ብቻ ሳይሆን፣ አጥብቀው ይሠሩበታል።
ያማራ ሕዝብ ጦቢያዊነቱን ካማራነቱ የሚያስቀድም፣ ብሔርተኝነቱ ኢትዮጵያዊነት የሆነ፣ ድርና ማግ ሆኖ ጦቢያን ያስተሳሰረ የጦቢያ ትልቁ ሕዝብ ነው፡፡ የጦቢያ ብሔርተኝነት (Ethiopian nationalism) ያማራ ብሔርተኝነት (Amhara nationalism) ነው የሚባለውም በዚሁ ምክኒያት ነው፣ የጦቢያ ብሔርተኝነትን በብዛትና በጥልቀት በማቀነቀን ያማራን ሕዝብ የሚስተካክል ማንም የለምና፡፡ ሁሉንም የጦቢያን ብሔረሰቦች ባንድነት በማነሳሳት ታላቁን ያድዋን ድል እንዲጎናጸፉ ያስቻላቸው ይህ ያማራ ብሔርተኝነት ነው የሚባለው የጦቢያ ብሔርተኝነት ነው፡፡ መላዋ አፍሪቃ ነጻ እንድትወጣና የመላው ዓለም ጥቁሮች በማንነታቸው እንዲኮሩ (black pride) መሠረት የጣለውም ይኸው ያማራ ብሔርተኝነት ነው የሚባለው የጦቢያ ብሔርተኝነት ነው፡፡
ስለዚህም በነጭ ላዕልተኞች (white supremacists) የሚዘወሩት ያንግሎ ሳክሶን (Anglo-Saxon) መንግስታት (ማለትም አሜሪቃና እንግሊዝ) ጦቢያን በተመለከተ ማናቸውንም ፖሊሲ (policy) የሚቀርጹት ያማራን ሕዝብ አለቅጥ በማዳከም (ከተቻለ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በማጥፋት) በጦቢያ ፖለቲካ ላይ የሚጫወተው ሚና ኢምንት ወይም አልቦ እንዲሆን ለማደርግ በማቀድ መሆኑ ምንም አያስገርምም።
በመሆኑም ያማራ ሕዝብ የሕልውና ጦርነቱን የሚያካሂደው ባማራ ክልል ላይ ብቻ እስከሆነና እርስ በርስ የሚተላለቁት አማሮች ብቻ እስከሆኑ ድረስ፣ ያሜሪቃና የንግሊዝ መንግሥታት ልባቸው ቅቤ ይጠጣል እንጅ ከልብ የሆነ እውነትኛ የጦርነት ተቃውሞ ድምጽ አያሰሙም። እንዲያውም በተቃራኒው ጦርነቱ በተቻለ መጥን እንዲራዘምና በተቻለው መጠን አማሮች እንዲያለቁ፣ ለጭራቅ አሕመድ በተለያዩ መንገዶች የቀጥታና የተዛዋሪ ድጋፍ ያደርጉለታል። ቱርክና ኢሚሬት ያሜሪቃን እሽታ ሳያገኙ፣ አማራን መጨፍጨፊያ ንቦቴ (drone) ለጭራቅ አሕመድ ማቅርብ አይችሉም።
አንድ የትግሬ ሴት ተደፈረች፣ አስር ትግሬወች አዲሳባ ላይ በማንነታቸው ታሰሩ ብለው በ BBC፣ CNN እና በመሰሎቻችው አማካኝነት ኡኡታውን በማቅለጥ የተባበሩት መንግሥታትን የፀጥታ ምክርቤት አስር ጊዜ ያስጠሩት እንግሊዝና አሜሪቃ፣ የመከሰሰ መብታቸው ያልተነሳ የሸንጎ አባሎችን ጨምሮ እልፍ አእላፍ አማሮች በማንነታቸው ሲታሰሩ፣ ሴት ወንድ ሳይባሉ በማንነታቸው ሲደፈሩና፣ ሕፃን አዛውንት ሳይባሉ በማንነታችው ሲጨፍጨፉ ዓይተው እንዳላዩ በመሆን ዝም፣ ጭጭ ያሉት ከእስሩ፣ ከመደፈሩና ከመጨፍጨፉ ዋናውን ትርፍ የሚያገኙት እነሱ ስለሆኑ ነው።
አነጋውያን የወለጋዋ ቶሌ የኛ ብቻ ስለሆነች ውጡልን ብለው ባንድ ጀምበር በሺ የሚቆጥሩ አማሮችን ማረዳቸውን በደንብ የሚያውቀው ባሜሪቃ የጦቢያ አምባሳደር አቶ ኧርዊን ማሲንጋ (Ervin Massinga)፣ የዲፕሎማሲን ሕግና ደንብ ጥሶ፣ በማያገባው ገብቶ በመፈትፈት ነዋሪውቿ ባብዛኛው አማራ የሆኑባትን አዲሳባን በፃራማራው በኦነግ ቋንቋ ፊንፊኔ ብሎ በይፋ (officially) የጠራው፣ አነግ የቶሌውን በቦሌ እንዲደግም ለማበርታታ ሲል ብቻ ነው። (በነገራችን ላይ ፋኖ አዲሳባን እንደተቆጣጠረ ይህን አምባሳደር ተብየ ግለሰብ ማቄን ጨርቄን ለማለት ጊዜ ሳይሰጠው በ24 ሰዓት ውስጥ በማባረር ለሌሎች ምዕራባውያን አምባሳደሮች ትምህርት መስጠት አለበት ።)
በነጭ ላዕልተኞች (white supremacist) አንግሎ ሳክሶኖች (Anglo-Saxon) በቀጥታና በተዛዋሪ የሚዘወሩት ያሜሪቃና የንግሊዝ መንግሥታት ጦቢያን የሚመለከቱት፣ ያማራ ብሔርተኝነት ነው የሚባለው የጦቢያ ብሔርተኝነት በተጎናጸፈው በታላቁ ያድዋ ድል አንጀቱ የቆሰለው ነምሳዊው (Austro-Hungarian Empire) የናዚ ባላባት (baron) ሮማን ፕሮቻዝካ (ፕሮሃዝካ) (Roman Prochazka) ጦቢያን በሚመለከትበት መነጽር ነው። በፕሮቻዝካ እይታ መሠረት ደግሞ የጦቢያ ብሔር ብሔረሰቦች ምርጫቸው በነጭ መገዛት ቢሆንም፣ የነጭ ባርያ የመሆን ምርጫቸውን ግን በነጭ ባህል እና ሐይማኖት መቃብር ላይ የጥቁርን ልዕልና ለመገንባት የሚያልሙት አማሮች ነፍገዋቸዋል። (“The numerous tribes who inhabit the Ethiopian state are being forcibly kept from European colonialism by Abyssinian rulers whose aim is to act as champions of all black people so as to attack and destroy Western culture”, Roman Prochazka, Abyssinia: The Powder Barrel, Vienna, 1935).
ስለዚህም አሜሪቃና እንግሊዝ በጭራቅ አሕመድ ላይ ፊታችውን የሚያዞሩበት፣ ጭራቅ አሕመድ ባማራ ሕዝብ ላይ የከፈተው ጦርነት ያማራን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን፣ ምርጫችው የኛ ባርያ መሆን ነው የሚሏቸውን ብሔር ብሔረሰቦች ሲጎዳ ካዩ ብቻና ብቻ ነው። ይህን ማድረግ የሚቻለው ደግሞ የሕልውናውን ጦርነት አድማስ አስፍቶ ጭራቅ አሕመድ የኔ ነው ወደሚለው ቀጠና ውስጥ በማስገባት፣ አስፈላጊውን ጥቃት ባስፈላጊው መንገድ እየፈፀሙ፣ ያማራ ቤት እየፈረሰ የሌላው ቤት ሊበጅ እንደማይችል በተግባር በማሳየት ነው።
ባጭሩ ለመናገር፣ ያማራ ሕዝብ የትግል አድማሱን ወደ ሌሎች ክልሎች ካሰፋው፣ ጭራቅ አሕመድን ለማሰወገድ ምዕራባውያን እንዲተባበሩት አለውዴታቸው ያስገድዳቸዋል። ጭራቅ አሕመድ ከተወገደ ደግሞ ኦነግ እዳው ገብስ ነው። መለስ ዜናዊ ሲሞት ወያኔ እንደተፍረከረከ፣ ጭራቅ አሕመድ ሲወገድ ኦነግም እንደሚፈረካከስ ሳይታለም የተፈታ ነው።
መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com