ዛሬም በሱስና መደመር ተጠምደህ ፋኖን የማትደግፍ ካለህ! ተሱስህ ተላቀህ ወደ ጎበዝ አለቃህ!

December 15, 2023

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

F7wuTWKWUAAd7Ho

ማስታወሻ፡- ይህ ጽሑፍ ከአራት ዓመታት በፊት የቀረበ ነው፡፡

ከሰባ አምስት ዓመታት በፊት አይሁዳንና ሌሎችን በመጨፍጨፍ ከሂትለር ጋር የተሳተፉ የናዚ ፓርቲ አባሎች እስከ አሁን እየታደኑ ለፍርድ እየቀረቡ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ [1-2] ለምሳሌ በአለፈው አመት የ95 ዓመት እድሜ ሽማግሌ ስሙን ለውጦ ከተደበቀበት ተይዞ በ21 ዓመቱ በፈጠመው ወንጅል ችሎት ቀርቧል፡፡ [3] የእኛውን አገር ሂትለር ያገለገሉት ወንጀለኞች ግን በዓለም ሲሸለሙ በአገር ውስጥም የአበባ ጉንጉን ሲጠለቅላቸው ይውላል፡፡ በዚህ መንገድ ነፍሰ-ገዳዮች እየተሸለሙና ሰማእታት ዳግም እየተሰው እግዚአብሄር በየትኛው ንስሃችን ምህረት ሊልክልን ይችላል? በሱስ ነፍዘን ፍትህን እየረገጥንስ እንዴት ሰላም ይሰፍናል?

በለማና አብዮት ሱስ ተመተው እንደ ደነዘዙት መንጋዎች በሲጃራና በአደንዛዥ ዕጥ ደንዝዞ አንዴ ሲዘፍን ሌጋ ጊዜ ሲያለቅስ የማየው አንድ ሱሰኛ ነበር፡፡ ይኸንን ሱሰኛ አንድ ቀን “የያዘህ ሱስ የሚያመጣውን ጠንቅ ትረዳለህን?” ስል ጠየኩት፡፡ ሱሰኛውም “አዎ!” አለና ሱሱ የሚያደርሰውን ጠንቅ ተራ በተራ ዘረዘረልኝ፡፡ እኔም ያንን ሁሉ ማወቁ ገረመኝና “በዚህ ሱስ የሞቱ ሰዎች ታውቃለህን?” ብዬ ስጠይቀው “አባቴ፣ ታላቅ ወንድሜ፣ የአክስቴ ልጅ” እያለ የሞቱትን ሰዎች ደረደረልኝ፡፡ “ያሳዝናል!” በዬ ሀዘኔን ገልጬ “ይኸንን እያወክ ታዲያ ለምን ተዚህ ሱስ መውጣት አልፈለክም?” ብዬ ስጠይቀው የሱሰኛ ነገር የሚመልሰው ግራ ገባውና “በሱስ የተያዝኩት እኮ እነሱ ተሞቱ በኋላ ነው!” አለኝና አረፈው፡፡

ተዚህ ሱሰኛ ጋር በነበረኝ የውይይት ልምድ በለማ በገበያና በአብዮት አመዴ ሱስ አገጫቸው ወደ ጀርባቸው እስቲዞር የተመቱ “የተማርን ነን” ባዮችን ለመፈተሽ ሞከርኩ፡፡ ከንፈራቸው ተአገጫቸው እስቲወድቅ በጀሮ ጠቢዎች ሱስ ሙዝዝ ማለታቸው ገረመኝና “የይህ አድግ የጀሮ ጠቢ መረብ ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ህዝብ ሲጨፈጪፍ፣ ሲገርፍ፣ ሲሰልብ፣ ሲያመክንና እግር ሲቆርጥ እንደኖረ ታውቃላችሁ ወይ” ብዬ ጠየኩ፡፡ ሱሰኞችም ሳያቅማሙ “አዎ እናውቃለን አሉ”። በልቤ ይኸንን ታወቃችሁም ዴግ ነው አልኩና “አብዮትና ለማ የጀሮ ጠቢው ድርጅት መሪዎች ሆነው እንደሰሩም ታውቃላችሁ አይደል?” ስል ሌላ ጥያቄ አስከተልኩ፡፡ አንዴ ወለሉን ሌላ ጊዜ ጣራውን እያዩ ሲያቅማሙ ለሰከንዶች ቆዩና “አዎ አገልግለዋል” ሲሉ መለሱ፡፡ ቀጥየም “ታዲያ ተእንደዚህ ዓይነት የሳጥናኤል ጀሮ ጠቢ መሪዎች ጋር ምነው በሱስ ተጠመዳችሁ?” ብየ ሳፋጥጥ ፊታቸው በዱቄት የተሸፈነውን የአቶ ማሞ እጅጉን ወፍጮ መሰለና “እርሱን እርሳው! ተለውጡ በፊት የሆነ ነው! ያለፈን በይቅርታ ማለፍ ነው! እኛ እምናስበው ለወደፊቱ ነው!” አሉኝና ተነስተው ሄዱ፡፡

ህሊናው እንደ ሎተሪ ካርድ ያልተፋቀና በጨጓራው ብቻ የማያስብ እንደሚረዳው እንደ ጫካ የተጨፈጨፉትን ሰዎች አስመልክቶ “እርሱን እርሳው!” የሚለው ዘግናኝ መልስ ተአሳማ እንኳን መውጣት የሌለበት የአራዊት ቃል ይመስለኛል፡፡ “እርሱን እርሳው!” የሚለው መልሳቸው እስከ ዛሬ አካላቴን እንደ ተሞረደ ጦር ይወጋኛል፡፡ “እርሱን እርሳው!” የሚለው መልሳቸው ይህ አድግ ለአርባ ሁለት ዓመታት በወልቃይት፣ በሁመራ፣ በጠለምት፣ በራያ፣ በአርባ ጉጉ፣ በበደኖ፣ በጋንቤላ፣ በኦጋዴንና ወለጋ የፈጃቸውን ዳግም የመረሸን ያህል ያመኛል፡፡

“እርሱን እርሳው!” የሚለው መልሳቸው አሁን አብዮት አመዴ የሚመራው ይህ አድግ በጎንደር፣ በደብረታቦር፣ በወልድያ፣ በባህርዳር፣ በመተከል፣ በቡሬ፣ በዳንግላ፣ በአጣዬ፣ በባሌ፣ በሲዳሞ፣ በከፋ፣ በኢሊባቦር፣ በቡራዮ፣ በለገጣፎና አዲስ አባባ የፈጃቸውን ህጻናት፣ እናቶች፣ አሮጊቶች፣ ወጣቶችና ጎልማሶች ዳግም የጨረገዳቸውን ያህል ይዘገንነኛል፡፡

“እርሱን እርሳው!” የሚለው ጨካኝ መልሳቸው ህዝብ ለማዳን ህይወታቸውን የገበሩትን እንደ አሰፋ ማሩ፣ አስራት ወልደየስ፣ ሳሙኤል አወቀ፣ ጎቤ መልኬንና ሌሎችንም ሰማዕታት በአደራ በላነት መንፈስ እንዳስባቸው ያደርገኛል፡፡ “እርሱን እርሳው!” የሚለው መልሳቸው ላለፉት አራት ሺህ ዘመናት አገራችንን ለመጠበቅ ከቀይ ባህር እስከ ኦጋዴን ከኦጋዴን እስከ ሞያሌ ከሞያሌ እስክ ጋምቤላ በሌጣ እግራቸውና በባዶ አንጀታቸው እየኳተኑ የተሰውቱን ጀግኖች ሁሉ “እርሳ!” ያሉኝ እየመሰለኝ እንደ መጥፎ ቅዠት ይዘገንነኛል፡፡

እነዚህ የ“እርሱን እርሳው!” ሰባኪዎች ሶስት ወር ሳይሞላ በሱስ ፍቅር ተአገጫቸው የተንከረፈፈው ከንፈራቸው እንደ ቁርባብች ተሸብሽቦና በትካዜ አሞድሙዶ አየኋቸው፡፡ የ“እሱን እርሳው!” ሰባኪዎች የሱስ ጪፈራቸው እንደዚያ የዕጽ ሱሰኛ ወደ ሀዘን ተቀይሮ አየኋቸው፡፡ የሀዘናቸው መንስዔም አብዮትና ለማ የሚጨፍረውን ባስጨፈሩና የሚሰግደውንም ባሰገዱ ማግስት ስልጣኑን ጠራርገው መውሰዳቸው፣ ባንክ ማዘረፋቸው፣ አዲስ አበባን በራሳቸው ሰው መሙላታቸው፤ አገሪቱን ከሞያሌ እስከ ራያና ወልቃት በደም አበላ ማጥለቅለቃቸው፣ ሶስት ሚሊዮን ህዝብ መንገድ ዳር መጣላቸው እንደሆነ ተረዳሁ፡፡

አብዮትና ለማ በወታደር የሚያስጠብቋቸው ወንጀለኞች አከታትለው ቤተክርስቲያኖች ሲያቃጠሉ፣ ምዕመናን ሲያርዱ፣ ተማሪዎችን ተፎቅ ሲወረውሩና ትምህርታቸው ሲያስተጓጉሉ ሱሰኞች “አብይና ለማ ከዱን!” እያሉ መንዘላዘላቸውን ሲያምኑ ሰማሁ፡፡ ዳሩ ግን በዕጸ-በለስ የደነዘዘ ሱሰኛ ተመልሶ ተዚያው እንደሚዘፈቀው እነዚህ ሱሰኞችም የሂትለር ጆሮ ጠቢ ኦስሎ ሌላ የሱስ ንግግር ሲያደርግ ተመልሰው ተሱሷቸው እንደ ጨርቅ ተዘፍዝፈው አየሁ፡፡

የአባቶቻችን አገርና ታሪክ ሲክድና እንደ ሽንኩርት ሲተክትፍ የኖረውን የሂትለር አገልጋይ “የአያቶቻችንን ገድል ተናገረ” ብለው ተፈላ ውሃ እንደ ገባ ጨው ባንዴ ፍርክስክስ ብለው ሲደልቁ ተመለከትኩ፡፡ የሂትለሩ ጀሮ ጠቢ በተሸለመበት ወቅት በመላ አገሪቱ የፈሰሰው የአማራ ደም፣ ወህኒ እሚማቅቁት የአማራ ወጣቶች፣ የታረዱት ክርስቲያች፣ ተቀጥቅጣ ያለፍችዋ የጨቅላ እናት፣ ተሜዳ የፈሰሱት ሴቶችና ህጻናትም በሱስ አብደው ተመጨፈር እንዳላዳኗቸው ተረዳሁ፡፡

የሚገርመው ደሞ ተደላቂዎቹ አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊው ሂትለር በሃያ ሰባት ዓመታት የጨረገዳቸው አማሮች ወገኖች መሆናቸው ነው፡፡ አያቶቻችን መሰሪውን ፈረንጅ ሳይቀር ዓይኑን ተመልክተው የሚያስበውን የመረዳት ጸጋ ነበራቸው፡፡ የእነዚህ የአማራ ሱሰኞች አዳርና ውሎ ግን እንደዚያ የዕጸ-በለስ ሱሰኛ አንዴ ዘፈን ሌላ ጊዜ ለቅሶ መሆኑ የሚያሸማቅቅ ነው፡፡ እነዚህ አሳፋሪ ሱሰኞች በመጀመርያው የሱስ ወረርሽን “አብይ ሙሴ ነውን” ደለቁ፡፡ ሶስት ወር ሳይሞላ አለቀሱ! በሁለተኛው ዙር ወረርሽኝ ደግሞ እስቲያልባቸው “አብይ ኖቤልን” ጨፈሩ፡፡ ይህ አስጨፍሮ የሚያስለቅስ ሱስ ተሱሶች ሁሉ የከፋው ነው፡፡ ተእንደዚህ ዓይነቱ ሱስ መፋታት በእርግጥም ከባድ ነው፡፡ ቢሆንም መዳኛው መፍትሄ ተሱስ መላቀቅ ብቻ ነው፡፡

የአማራ ሱሰኛ ሆይ! ይኸ እንደ ጅል ፍቅረኛ የሚያንዘላዝልህ ሱስ ሊያጠፋህ የሚችል መሆኑ የማይገለጥልህ ለምንድ ነው? በሌሎች እምነት ጥለህና በሱስ ሰክረህ የምትተኛው ስንት ሌሊት ነው? ተድንጋይ ማምረቻው ሳይወቀሩ የወጡ ጀሮ ጠቢዎች የሚያጃጅሉህ እስከ መቼ ድረስ ነው? የአማራን መቃብር የተመኘውን የሂትለር ሎሌዎች እንደ ናዚ ተሳታፊዎች ለፍርድ ማቅረብ ሲገባህ የምታጨበጭብላቸውና የምትሸልማቸው ለሥጋህ ወይስ ለነፍስህ እንዲበጅ ነው?

የአማራ ሱሰኛ ሆይ! እባክህ የሽሮ ፍትፍትህን ጎስጉስና ስካርና ሱስህን ፈውስ! ተክብርህ ለመኖር የሂትለር አገልጋዮችን መመርኮዙን ተውና በራስህ አንገት ጥና! ላንተም ሆነ ለኢትዮጵያ መዳኛ የጎበዝ አለቅነት ሥርዓት ነውና ወደ ጎበዝ አለቃህ አቅና! ተእየሩሳሌም እስከ ማደጋስካር የደረሰውን ግዛትህን የዘረጋው የጎበዝ አለቃ እንጅ መጤው የጥበቃ ጓድ ወይም አውደልዳይ ፖሊስ ሥርዓት እንዳልሆነ ታሪክን መርምር፡፡

አገርህ የተመሰረተችው በጎበዝ አለቆች እንጅ ኮሎኔልና ጀኔራል በሚሉ የተውሶ ማእረጎች እንዳልሆነ ተረዳ፡፡ የቱርክ፣ የግብጥንና የጣሊያንን ወራሪዎች ደንደስ የተሰበረው በሰላም ጊዜ ገበሬ በጦር ወቅት ሰራዊት በሆኑት የጎበዝ አለቃዎች መሆኑን አጢን፡፡ በኢትዮጵያ ሰላምን፣ ሥርዓትን፣ እምነትንና የመንፈስ ልእልናን ሲያስጠብቁ የኖሩት ጎበዝ አለቃዎች መሆኑን እወቅ፡፡

የአማራ ሱሰኛ ሆይ! አገርህ ቁልቁል መንሸራተት የጀመረችው የጎብዝ አለቅነት ሥርዓት መፍረስ ተጀመረበት ጊዜ መሆኑን ተገንዘብ፡፡ ጎበዝ አለቃ እንደ ፖሊስና ካድሬ በነፍሰ-ገዳይዎች እንደ ቀንበር የሚጫንብህ ሳይሆን ከአብራክህ እንደ ምጥ የሚወጣ የሥጋና የመንፈስ ልጅ መሆኑን እመን፡፡ የጎበዝ አለቃ በጀግነቱ፣ በምግባሩና በመንፈስ ልዕልናው ራስህ የምትመርጠው የአገር ደጀን መሆኑን ተረዳ፡፡ የጎበዝ አለቃ ወንበዴ ገዥዎችን ልክ የሚያስገባ የማህበረሰብ ዋስትና መሆኑን አስተውል፡፡

የጎበዝ አለቃ የአካባቢውን ሰላምና ደህነንት የሚያስከበር የተዋጣለት መሪ መሆኑ እወቅ፡፡ የጎበዝ አለቃ ዳር ድንበርህ ሲደፈር ፎክሮ የጠላትን ጉርንቦ የሚያንቅ አንበሳና ነበር መሆኑን ተገንዘብ፡፡  ጎበዝ አለቃ ባንዳን እንደ ጎባጣ ሞፈር አርቆ ልክ የሚያስገባ የእርሻና የጦር ገበሬ መሆኑን እመን፡፡ ጎበዝ አለቃ ባንዳን እንዴት አርቆ እንደሚያስተካክል ለመረዳት ገድለ-በላይ ዘለቀና ገድለ-አበበ አረጋይን ለማንበብ ፈቃደኛ ሁን፡፡

ጎበዝ አለቃ በሱስ ተጠምዶ ለሂትለር ሰላዮች እስክስታ የማይመታ በአካልና በመንፈስ የጠና የህብረተሰብ አለኝታ መሆኑን አጢን፡፡ ጎበዝ አለቃ ለነጻነቱና ለፍትህ ሲል ለልጆቹም የማይሳሳ ባለማተብ ጀግና መሆኑን ተበላይ ዘለቀ ተማር፡፡ ጎበዝ አለቃ ፍትህን ተጀግንነት፤ እምነትን ተሥራ የሚያዋህድ የተባረከ የአማራ እሴት መሆኑን ተረዳ፡፡

ስለዚህ ሱሰኛ አማራ ሆይ! ተሱስህ ተላቀህ ወደ ጎበዝ አለቃህ! አመሰግናለሁ፡፡

 

ዋቢ

  1. 10 Most Wanted Nazi War Criminals, History channel https://www.history.com/news/10-most-wanted-nazis
  2. The last Nazi hunters, https://www.theguardian.com/news/2017/aug/31/the-last-nazi-hunters
  3. Nazi war crimes suspect, 94, faces German youth court trial https://www.theguardian.com/world/2018/sep/21/nazi-war-crimes-suspect-faces-trial-german-youth-court

ታህሳስ ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

 

1 Comment

  1. ጎበዝ ይች ሰውዬ ጭንቅ ላይ ነች፡፡ እበላለሁ ብላ ገብታ ነብስ ከስጋዋ ተላቀቀ በዚህ ላይ በይ ተብላ የሚነገራትን ነው የምታወራው የራሷ ሳትሆን በፋኖ እንክብካቤ ውስጥ እንዳትወድቅ ያሰጋል፡፡ እየሄደች ከተኛች ያለችበትን ጭንቀት መገመት ይቻላል፡፡ እንደ እኔ እንደ እኔ ሽንት ልውጣ ብላ ብር ብላ እጇን ለእስክንድር ብትሰጥ ለቤተሰብዋ ትተርፍ ነበር ያልተቋረጠ እንቅልፍም ይወስዳት ነበር፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

187648
Previous Story

ኦሮሚያ ከእጃችን ይወጣል” ጁላ | “አፈሳ ይጀመር” አብይ | “አየር ኃይል ከአማራ ነጻ አድርገናል” ይልማ | የዶ/ሩ ገዳይ ተያዘ

187653
Next Story

ከግምባር!ፋኖ አስረስ ማረ ከአማራ ድምፅ ጋር!”የብልፅግና ጀምበር ጠልቃለች” The Voice of Amhara Daily News

Go toTop