April 11, 2013
3 mins read

(ሰበር ዜና) ሲአን የፊታችን እሁድ ከሚደረገው ምርጫ ራሱን አገለለ

(ዘ-ሐበሻ) የአዲስ አበባ የድሬዳዋ የክልል የአካባቢ ምርጫ ለማሳተፍ ተመዝግቦ በዝግጅት ላይ የሚገኘው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ /ሲአን/ የሚደርስበትን ጫና ከምርጫው ለመውጣት መገደዱን አስታወቀ። ኢሕ አዴግ ብቻውን በሚወዳደርበት የአካባቢና የከተማ ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ የፊታችን እሁድ እንዲሁም በሳምንቱ ሚያዚያ 13 የሚካሄድ ሲሆን የሲአን ከምርጫው መውጣት ለገዢው መንግስት የፖለቲካ ኪሣራ እንደሆነ የፖለቲካ ተንታኞች ለዘ-ሐበሻ ተናግረዋል።

ፓርቲውም በደረሰበት በደልና ጫና የተነሳ የመጨረሻ እርምጃ ለመውሰድ መቃረቡን ሲገልጽ የከረመው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የፊታችን እሁድ የሚካሄደውን ምርጫ በተመለከተ የሚደርስባቸውን ጫና መታገስ የማይችሉበት ደረጃ በመድረሱ ከምርቻው ሊወጣ ተገዷል። ሲአን “እጩ ተወዳዳሪዎቻችን በገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ይታሰራሉ፤ ይደበደባሉ እንዲሁም የተለያዩ በደል እንደሚፈፀምባቸው” ሲገልጽ ቆይቶ ገዢው መንግስትም ይህን እንዲያስቆም ቢተይቅም ይህ የማሰር እና የማንገላታት ተግባር ጨምሮ በመቀጠሉ ፓርቲው ራሱን ከምርጫ እንዳገለለ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ተናግረዋል።
በዘንድሮው የአካባቢና የከተማ ምክር ቤቶች ምርጫ ዋና ዋናዎቹ ከ30 በላይ የሚሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንሳተፍም በሚለው አቋማቸው በመጽናታቸው ኢሕ አዴግና ተለጣፊዎቹ ፣ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ /ኢራፓ/፣ የኢትዮጵያ ፍትህና ዴሞክራሲ ሃይሎች ግንባር /ኢፍዴሃግ/ እና ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ አንዲሁም አንድ ተወዳዳሪን የመደበው ኢዴፓ ይሳተፋሉ ቢባልም ዋና ዋና ተቃዋሚዎች ቦይኮት ባደረጉት የዚህ ምርጫ በኢሕአዴግ አሸናፊነት እንደሚጠናቀቅ ከወዲሁ የታወቀ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ለዘ-ሐበሻ ይናገራሉ።

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::

የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)  ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር

እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?

ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

January 26, 2025 ጠገናው ጎሹ ከቅኝ አገዛዝ (colonial rule) ነፃ መሆንን ከማወጅ ያለፈ የውስጥ ነፃነት ፣እኩልነት፣ ፍትህ እና እደገት/ልማት እውን ማድረግ ባለመቻል ምክንያት በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የኋላ ቀርነት እና ለመግለፅ

አህጉራችን እና እኛ

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
Go toTop